የመነኮሳት አባቶች የጋራ መኖሪያ ቤት ተመረቀ

This author has not written his bio yet.
But we are proud to say that Mahibere Kidusan contributed 1445 entries already.
ክፍል አራት
በጸጋ እግዚአብሔር አምላኩ የከበረ ይህ ሐዋርያው ጳውሎስ ትምህርቱን የበለጠ ተቀባይነት ያለው ለማድረግ ብርሃነ እግዚአብሔር ኦሪትን ለሐዲሱ ምስክር እያደረገ ያስተማምናል፡፡ስለሆነም «ነሥአ መሬተ ወገብሮ ለእጓለ እመሕያው ወነፍሐ ላዕሌሁ መንፈሰ ሕይወት፤እግዚአብሔር አዳምን ከምድር ዐፈርን ወስዶ ፈጠረው፡፡ የሕይወትንም እስትንፋስ አሳደረበት፡፡»ብሎ መጽሐፍ እንደተናገረ በዚች ነፍስ ሕይወትነት የሚኖር ሥጋ አስቀድሞ መፈጠሩን ይገልጽና፤ከትንሳኤ ዘጉባኤ በኋላ ግን መንፈስ ቅዱስ ሕይወት ሆኖት የሚኖር ሥጋ እንደሚገኝ /እንደሚነሳ/ ለአጽንዖተ ነገር ደጋግሞ ይናገራል፡፡ ዘፍ 2÷7
ኅዳር 20 ቀን ከዋዜማው ጀምሮ መከበር የጀመረው የኅዳር ጽዮን በዓል ዛሬም ቀጥሎ በድምቀት ተከብሮ ውሏል።
ከትናንትና ማታ 2፡00 ደወል ከተደወለበት ጀምሮ፥ ሊቃውንት ካህናትና ዲያቆናት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በስብሐተ ማኅሌት በማድረስ ሌሊቱን አሳልፈዋል።
በሰሙነ ሕማማት ጠቅለል ባለ መልኩ የምናስባቸው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማማት አሥራ ሦስት ናቸው፡፡ እነርሱም አሥራ ሦስቱ ሕማማተ መስቀል ይባላሉ፡፡ ለክርስቲያኖች እነዚህን ሕማማተ መስቀል ማወቅና ዘወትር ማሰብ ተገቢ በመሆኑ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡
መግቢያ
ቤተ ክርስቲያን ለብዙ ዘመናት የፈተና ገፈታ ቀማሽ በመሆን፣ ልጆቿን እያበረታታች ለሀገራዊ ሀብት መጠበቅም እስከ ሰማዕትነት እያበረከተች በየአድባራቱና ገዳማቱ ጠብቃ አሳድጋ ለዚህ ትውልድና ዘመን ካቆየቻቸው ዕሤቶች አንዱ ግእዝ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ቤተ መዘክር፣ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት ቤት፣ ቤተ ክርስቲያን ግምጃ ቤት፣ ቤተክርስቲያን የሥልጣኔ ማዕከል፣ ቤተ ክርስቲያን ከተማ ሀገር በመሆን ስታገለግል ቆይታለች፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በበሳል ትምህርቱ በመንፈሳዊ ጥብዐቱና በፍጹም መንፈሳዊ ሕይወቱ በቤተ ክርስቲያናችን የታወቀ አባት ሲሆን ኑሮውም የብህትውና ነበር። ካስተማራቸው በርካታ ትምህርቶቹ መካከል ውስጥ አንድ ክርስቲያን በምድር ሲኖር ሰማያዊውን ሕይወት እንዲኖር ነው። ይህንንም ያስተማረበትን ትምህርት እንዲህ አቅርበነዋል፡፡