Entries by Mahibere Kidusan

አርዮስ እና መንፈቀ አርዮሳውያን በቤተ ክርስቲያን ላይ ያደረሱት ችግር – የመጨረሻ ክፍል

ፓትርያርክ አትናቴዎስን በግፍ ወደ ግዞት ቦታ እንዲሔዱ የፈረደባቸው የቂሣርያው ጉባኤ፣ ‹‹አርዮስ ተጸጽቶ ከክሕደቱ መመለሱን የሚያመለክት መጣጥፍ አቅርቧል›› በሚል ሰበብ አርዮስን ከግዝቱ ፈቶ ነጻ አወጣው፡፡ አትናቴዎስ ወደ ግዞት በመላካቸው አርዮሳውያን እና መንፈቀ አርዮሳውያን ምቹ ጊዜ አግኝተው ስለ ነበር አርዮስን ወደ ሀገሩ ወደ እስክንድርያ ለመመለስ ይሯሯጡ ጀመር፡፡ የአርዮስ ነጻ መውጣትም ንጉሡ በሚኖርበት በቊስጥንጥንያ በይፋ እንዲከበር በማሰብ አርዮስ በወዳጆቹና በደጋፊዎቹ ታጅቦ ወደ ቊስጥንጥንያ እንዲሔድ አደረጉ፡፡ በዚያም በሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን ከቊስጥንጥንያው ሊቀ ጳጳስ ጋር እንዲቀድስና ወደ ክርስቲያን አንድነት መግባቱ በይፋ እንዲታወጅ ዝግጅት ተደርጎ ሳለ ሆዱን ሕመም ተሰምቶት ወደ መጸዳጃ ቤት ሔዶ በዚያው ቀረ፡፡ አርዮስ ስለ ዘገየባቸው ደጋፊዎቹ ሔደው ቢያዩት ሆድ ዕቃው ተዘርግፎ ሞቶ አገኙት፡፡ በዚህም ‹‹የእግዚአብሔር ቊጣና መቅሠፍት በአርዮስ ላይ ተገለጠ›› ተብሎ በብዙ ሰዎች ዘንድ ታመነ፡፡ ሆኖም በአርዮስ ሞት የተበሳጩ አንዳንድ የአርዮስ ደጋፊዎች የእግዚአብሔርን ፍርድ አይተው ከክሕደታቸው በመመለስ ፈንታ ‹‹አርዮስ የሞተው በመድኃኒት ተመርዞ ነው›› ብለው ማውራትና ማስወራት ጀመሩ፡፡

አርዮስ እና መንፈቀ አርዮሳውያን በቤተ ክርስቲያን ላይ ያደረሱት ችግር – ክፍል ሦስት

ከአርዮሳውያን ጋር የከረረ ክርክር የተደረገው በሁለት ጉዳዮች ነበር፤ እነዚህም ፩ኛ አርዮስ ወልድን ‹‹ፍጡር ነው›› ለማለት ‹‹ሀሎ አመ ኢሀሎ ወልድ፤ ወልድ ያልነበረበት ጊዜ ነበር›› ሲል ኦርቶዶክሳውያን ወልድን ዘለዓለማዊ ነው ለማለት ‹‹አልቦ አመ ኢሀሎ ወልድ፤ ወልድ ያልኖረበት ጊዜ የለም›› ብለው የአርዮሳውያንን ክሕደት አጥላልተው አወገዙት፡፡ ፪ኛ አርዮስና ደጋፊዎቹ ‹‹ወልድ በባሕርዩ (በመለኮት) ከአብ ጋር አንድ አይደለም፤›› የሚሉትን ጉባኤው ካወገዘ በኋላ፣ ኦርቶዶክሳውያን ወልድን “Omo-ousios” (ዋሕደ ባሕርይ ምስለ አብ ወይም ዘዋሕድ ምስለ አብ በመለኮቱ፤ ወልድ ከአብ ጋር በባሕርዩ በመለኮቱ አንድ ነው)›› አሉ፡፡ የአርዮስ ደጋፊዎች የነበሩትም የአርዮስን የክሕደት ትምህርት ያልተቀበሉ በማስመሰልና ኦርቶዶክሳውያን በመምሰል “Omoi-ousios” (የወልድ ባሕርይ ከአብ ባሕርይ ጋር ተመሳሳይ ነው) ብለው ሐሳብ አቀረቡ፡፡ የእነዚህንም ሐሳብ ጉባኤው ፈጽሞ አልተቀበለውም ነበር፡፡ እነዚህም መንፈቀ አርዮሳውያን (Semi-Arians) ተብለው ተወግዙ፡፡

አርዮስ እና መንፈቀ አርዮሳውያን በቤተ ክርስቲያን ላይ ያደረሱት ችግር – ክፍል ሁለት

ሊቀ ጳጳሱ እለእስክንድሮስም ምእመናን ከአርዮስ የክሕደት ትምህርት እንዲጠበቁ እየዞረ በማስጠንቀቅ ያስተምር ጀመር፡፡ ፓትርያርኩም በ፫፻፲፰ ዓ.ም በእስክንድርያና በአካባቢዋ የሚገኙትን ጳጳሳትና ካህናት ሰብስቦ አርዮስንና ተከታዮቹን በጉባኤ አወገዛቸው፡፡ አርዮስ ግን ከስሕተቱ ባለመመለሱ ፓትርያርክ እለእስክንድሮስ በ፫፻፳፩ ዓ.ም አንድ መቶ የሚሆኑ የእስክንድርያንና የሊብያን ኤጲስቆጶሳት ሰብስቦ ጉባኤ በማድረግ የአርዮስን ክሕደት በዝርዝር አስረዳቸው፡፡ ሲኖዶሱም ጉዳዩን በሚገባ ከመረመረ በኋላ አርዮስን በአንድ ድምፅ አወገዘው፡፡ አርዮስም በበኩሉ እየዞረ ‹‹እለእስክንድሮስ ሰባልዮሳዊ ነው፤ የሰባልዮስን የክሕደት ትምህርት ያስተምራል›› እያለ የሊቀ ጳጳሱን የእለእስክንድሮስን ስም ማጥፋት ጀመረ፡፡ በመሠረቱ ከሰባልዮስ ትምህርት ጋር የሚቀራረበው ‹‹ወልድ ፍጡር ነው›› (ሎቱ ስብሐት) የሚለው የአርዮስ ትምህርት ነው እንጂ ‹‹ወልድ የባሕርይ አምላክ ነው፤ ከአብም ጋር በባሕርይ አንድ ነው (ዘዋሕድ ምስለ አብ በመለኮቱ)›› የሚለው ትምህርት አይደለም፡፡

አርዮስ እና መንፈቀ አርዮሳውያን በቤተ ክርስቲያን ላይ ያደረሱት ችግር – ክፍል አንድ

በአንድ ሌሊት በራእይ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድ ወጣት አምሳል እንደ ፀሓይ የሚያበራ ረጅም ነጭ ልብስ (ቀሚስ) ለብሶ ለቅዱስ ጴጥሮስ ይታየዋል፡፡ ልብሱ ለሁለት የተቀደደ ሆኖ ቢያየው ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ደንግጦ ጌታን ‹‹መኑ ሰጠጣ ለልብስከ፤ ልብስህን ማን ቀደደብህ?›› ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ ጌታም ‹‹አርዮስ ልብሴን ቀደደብኝ›› ብሎ መለሰለት፡፡ ይኸውም በአባቶች ትርጕም ‹‹አርዮስ ከባሕርይ አባቴ ከአብ ለየኝ (አሳነሰኝ)›› ማለት ነው፡፡ ጌታም አርዮስን ከእንግዲህ ወዲያ ወደ ቤተ ክርስቲያን አንድነት እንዳይቀበለው አዝዞት ተሰወረ፡፡ ተፍጻሜተ ሰማዕት ጴጥሮስ ራእዩን ያየው በዲዮቅልጥያኖስ ስደት ጊዜ ተይዞ ለመገደል በእስር ቤት በነበረበት ወቅት ነበር፡፡ አርዮስም ቅዱስ ጴጥሮስ እንደሚገደል አውቆ ከውግዘቱ ሳይፈታው እንዳይሞት ከውግዘቱ እንዲፈታው አማላጆች ይልክበታል፡፡ ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ ግን አርዮስን ‹‹በሰማይና በምድር የተወገዘ ይሁን!›› በማለት ውግዘቱን አጸናበት፡፡ በዚያኑ ቀን ተማሪዎቹን አርኬላዎስን እና እለእስክንድሮስን አስጠርቶ ያየውን ራእይ በመግለጥ አርዮስን እንዳይቀበሉትና ከእርሱም ጋር ኅብረት እንዳይኖራቸው አዘዛቸው፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን አገልግሎት

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አባታዊ መመሪያ ሰጭነት አስፈላጊ ቅድመ ኹኔታዎችን በሟሟላት፣ ተደጋጋሚ ውይይቶችንና ዓለም አቀፍ ዳሰሳዎችን በማድረግ ለሥርጭቱ ያመነበትን የሳተላይት ጣቢያ አወዳድሮ በመምረጥና የውል ስምምነት በማዘጋጀት በአፋጣኝ የሥርጭት አገልግሎቱን ጀምሯል፡፡ በኢየሩሳሌም ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት ጋር በተደረገ ስምምነት መሠረትም የቴሌቭዥን መርሐ ግብራቱ በአገር ውስጥ ተዘጋጅተው ኢየሩሳሌም በሚገኘው የሳተላይት ድርጅት አማካይነት ይሠራጫሉ፡፡ የቴሌቭዥን ጣቢያው የሥርጭት አድራሻም የሚከተለው ነው፤

Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Television (EOTC TV)

Satellite: Eutelsat/Nilesat (ኢትዮጵያ)

Frequency …. 11353 (5) Vertical

Symbol rate …. 27500/FEC…5/6

Satellite: Galaxy 19 (G-19) (ሰሜን አሜሪካ)

Frequency …. 11960/Vertical

Symbol rate …. 22000/FEC…3/4

ዘመነ ጽጌ

ሰዓታት የሚያደርሱ ካህናትም፡- ‹‹ትመስሊ ምሥራቀ፤ ወትወልዲ መብረቀ፤ ወታገምሪ ረቂቀ፡፡ ትመስሊ ፊደለ፤ ወትወልዲ ወንጌለ፤ ወታገምሪ ነበልባለ፡፡ ትመስሊ ጽጌ ረዳ፤ ወትወልዲ እንግዳ፤ ወታድኅኒ እሞተ ፍዳ … ሐረገ ወይን ሐረገ ወይን ዐፀደ ወይን አንቲ ማርያም›› ማለት፡- ‹‹በምሥራቀ ፀሐይ የምትመሰየሚው፤ እንደ መብረቅ ኃያል የሆነውን ጌታን የወለድሽ፤ ረቂቅ ምሥጢርን የምትችዪ፤ እንደ ፊደል ባለ ብዙ ዘር (ሆሄያት) የሆንሽ፤ ወንጌልን የወለድሽ፤ ነበልባለ እሳትን (ክርስቶስን) የተሸከምሽ፤ በጽጌ ረዳ አምሳል የምትመሰየሚው ቅድስት ማርያም ሆይ! የዓለሙን እንግዳ ፈጣሪን የወለድሽ፤ ከፍዳ ሞት የምታድኚ፤ የወይን ሐረግ የወይን ዐፀድ (ተክል) አንቺ ነሽ …›› እያሉ ያመሰግናሉ፡፡

የጥቅምት ወር ፳፻፲ ዓ.ም ምልዓተ ጉባኤ መጠናቀቁን ተከትሎ ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

በጋሻው ደሳለኝ የተባለ ግለሰብ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ለበርካታ ዓመታት ለምእመናን ሲያስተላልፍ የነበረው የክህደት ትምህርት በመረጃ ተስብስቦ ችግሩ ለቅዱስ ሲኖዶስ ከቀረበ በኋላ ከ15/02/2010 ዓ.ም. የክህደት ትምህርቱን በማውገዝ ከቤተ ክርስቲያናችን እንዲለይ ተደርጓል፣ በቤተ ክርስቲያናችን ስም እንዳያስተምር ተወግዟል፡፡

በተመሳሳይ መልኩም በአሜሪካን ሀገር በዋሽንግተን ዲ.ሲ. የሚያገለግሉት አባ መዓዛ ክርስቶስ በየነ እያስተማሩ ያለው የክህደት ትምህርት ለቅዱስ ሲኖዶስ በመረጃ ቀርቦ የተረጋገጠባቸው ስለሆነ ሥልጣነ ክህነታቸው ተይዟል፤ ያሉበትን ቤተ ክርስቲያን ጨምሮ በማናቸውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንዳይሰጡ ታግደዋል፡፡

ወልደ አብ በሚል ርእስ፤ ገብረ መድኅን በተባለ ግለሰብ የተጻፈው የክህደትና የኑፋቄ ትምህርት የቅብዓትንና የጸጋን የክህደት ትምህርት የሚያስፋፋ በመሆኑ ካህናትን ከካህናት ምእመናንን ከምእመናን የሚያጋጭ ከመሆኑ ጋር፤ ከቤተ ክርስቲያናችንም አልፎ በሀገራችን ሁከት ለማስነሣት ታስቦ የተዘጋጀ ሆኖ ስለተገኘ፣ መጽሐፉ ከማናቸውም አገልግሎት እንዲለይ ተወግዟል፡፡

በኬንታኪ የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር መካሔዱን የአሜሪካ ማእከል አስታወቀ

የኢንዲያና ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል እና የኬንታኪ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል አብያተ ክርስቲያናት ሰበካ ጉባኤያት እንደዚሁም ሰንበት ት/ቤቶቹ ከኢንዲያና ግንኙነት ጣቢያ ጋር በአንድነት መሥራታቸው ለሐዊረ ሕይወቱ በስኬት መከናወን የላቀ ሚና የነበረው ሲኾን፣ በመርሐ ግብሩ ማጠቃለያም የግንኙነት ጣቢያው ሰብሳቢ ዶክተር በላይነህ ደስታ ለሐዊረ ሕይወቱ በስኬት መከናወን ትልቅ አስተዋጽዖ ላበረከቱ አካላት ዅሉ በማኅበረ ቅዱሳን ስም መንፈሳዊ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በመጨረሻም ከምእመናኑ የተገኘው $1747 (አንድ ሺሕ ሰባት መቶ ዐርባ ሰባት ዶላር) መርሐ ግብሩ ለተካሔደበት ለኬንታኪ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ገቢ ከተደረገ በኋላ መርሐ ግብሩ በአባቶች ጸሎት ተፈጽሟል፡፡

ከመናፍቃን ስውር ደባ ራሳችንን እንጠብቅ

ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮዋን የምታስፋፋባቸው ብዙ መንገዶች አሏት፡፡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ የጻፏቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ተጠቃሽ የአስተምህሮ ማስፋፊያ መንገዶች ናቸው፡፡ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት የምንላቸው የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ የሚያስጠብቁ ናቸው፡፡ እነዚህ መጻሕፍት የቤተ ክርስቲያን መሆናቸውን ማወቅ የምንችለው ያለንን ዕውቀትና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን በመጠቀም ነው፡፡ ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን ከሌሎች ለመለየት የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ማወቅ ግድ ይሆናል፡፡ ይህም በአንድ ጀንበር የሚሳካ ቀላል ተግባር ባይሆንም መፍትሔው ግን ከባድ አይደለም፡፡ መጻሕፍትን ለመግዛት፣ የምናነባቸውን ለመምረጥ፣ ስናነብ ያልገባንን ለመረዳት፣ ትክክል መስሎ ያልታየን ወይም ያደናገረን ነገር ሲኖር ለማጥራት የቤተ ክርስቲያንን ሊቃውንት እና ከእኛ የተሻለ መንፈሳዊ ብስለት ያላቸውን መምህራን መጠየቅ መልካም ይሆናል፡፡

“ሊሆን ይችላል” ወይም “ለእኔ ተስማምቶኛል” በሚል ሰበብ ሳይገባንና በግል ፍላጎታችን ላይ ተመሥርተን የምንቀበለው “ትምህርት” ሊኖረን አይገባም፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን ጠያቂ መሆንና ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ዕድገት ምክር የሚሰጡን መሪዎችን መፈለግና ምክራቸውን መተግበር ተገቢ ነው፡፡ ከዚሁ ሁሉ ጋርም ለትምህርት የምንፈልጋቸውን የኅትመትም ሆነ የምስል ወድምፅ ውጤቶች ስንገዛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡ በራሳችን ገንዘብ የመናፍቃንን ትምህርት ገዝተን ወደቤታችን ማስገባት የለብንም፡፡ ከመግዛታችን በፊት የጸሓፊውን ማንነት፣ የመጽሐፉን ይዘት ማወቅ፤ ካላወቅነውም መጠየቅ አስፈላጊ ነው፡፡ በስሕተት ገዝተናቸው ያነበብናቸውና ጥያቄ የፈጠሩብንም ካሉ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን በመጠየቅ መልስ ማግኘት አለብን፡፡

ከሁለት ሺሕ በላይ አዳዲስ አማንያን የሥላሴን ልጅነት አገኙ

ከተጠማቂዎቹ መካከል አንዱ የኾኑት በዝጊቲ ባቆሌ ቀበሌ ነዋሪና የሌላ እምነት ተከታይ የነበሩት አቶ ዘሪኹን ቱሎ ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ አምላክነት የሚሰበክባት፣ በጠበልና በእምነት ከሕመም መዳን የሚቻልባት እውነተኛ ሃይማኖት እንደኾነች በእኛ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ይነግሩኝ ነበር፡፡ ይህ ነገር ምን ያህል እውነት ነው እያልኹ ከራሴ ጋር ስሟገት ዓመታት ቢያልፉም ባለቤቴ ‹ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን ተመለሱ› የሚል መልእክት በራእይ በመስማቷ ማንም ወደ ጥምቀቱ ሳያመጣን አምነን ተጠምቀን በዛሬዋ ዕለት የሥላሴን ልጅነት አግኝተናል›› በማለት የቤተ ክርስቲያን አባል የኾኑበትን ምሥጢር አስረድተዋል፡፡