ስምና የስም ዓይነቶች
ዲያቆን ዐቢይ ሙሉቀን የተከበራችሁ አንባብያን ባለፈው ትምህርታችን ላይ የቤት ሥራ የሰጠናችሁ መሆኑ ይታወሳል፡፡ በመሆኑም መልሱን እንደሚከተለው እንሥራ፡፡ ፩. ምት፡- ሠናይት ብእሲት ታቀርብ ማየ እግር ለምታ፤ መልካም ሴት ለባሏ የእግር ውኃ ታቀርባለች፡፡ ፪. ብእሲት፡- ብእሲ ወብእሲት አሐዱ አካል እሙንቱ፤ ባልና ሚስት አንድ አካል ናቸው፡፡ ፫. ሥእርት፡- ሥዕርት ይትረከብ እምላዕለ ርእስ፤ ፀጒር ከራስ ላይ ይገኛል፡፡ ፬. […]