የኒቂያ ጉባኤ
በቢታንያ አውራጃ፤ ጥቁር ባሕር ወደብ አካባቢ የምትገኘው ኒቂያ በባሕርም ሆነ በየብስ ለሚጓዙ ሰዎች እጅግ ተስማሚ ከተማ እንደነበረች ቅዱሳት መጽሐፍት ይጠቅሳሉ፡፡ የእስክንድርያ ንጉሠ ነገሥታት መናገሻቸውን ወደ ቁስጥንኒያ እስከዛወሩበት ዘመነ መንግሥት ድረስ ከኒቂያ በ፴፪ …
This author has not written his bio yet.
But we are proud to say that Mahibere Kidusan contributed 1043 entries already.
በቢታንያ አውራጃ፤ ጥቁር ባሕር ወደብ አካባቢ የምትገኘው ኒቂያ በባሕርም ሆነ በየብስ ለሚጓዙ ሰዎች እጅግ ተስማሚ ከተማ እንደነበረች ቅዱሳት መጽሐፍት ይጠቅሳሉ፡፡ የእስክንድርያ ንጉሠ ነገሥታት መናገሻቸውን ወደ ቁስጥንኒያ እስከዛወሩበት ዘመነ መንግሥት ድረስ ከኒቂያ በ፴፪ …
የ፳፻፲፫ መስቀል ደመራ በዓል የኮሮና በሽታ ወረርሽኝን ለመከላከል የሃይማኖት አባቶችን ጨምሮ አምስት ሺህ ተሳታፊዎች ብቻ በተገኙበት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ተከብሯል፡፡
ለ፭፼፭፻ ዘመናት የሰው ዘር በኃጢአት ሰንሰለት ታስሮና በጨለማ ተውጦ በነበረበት ዓመተ ፍዳ እግዚአብሔር ወልድ ለዓለም ድኅነት የተሰዋበት ግማደ መስቀሉን ‹‹መስቀል ብርሃን ለኵሉ ዓለም፤ መስቀል የዓለም ብርሃን ነው›› እያልን እንዘክረዋለን፡፡
ሊሄድ በ’ኔ መንገድ
ሊከተል የሚወድ
ራሱን ይካድ…
በቅርብ ጊዜ ከተነሡት ፍልስፍናዎች አንዱና እጅግም የተስፋፋው የኢ-አማንያን አመለካከት ማለትም ‹‹ሃይማኖት የጦርነት ምንጭ ነው፤ ስለዚህ አያስፈልግም›› በሚል ክርስትናን እና ተዋሕዶ ሃይማኖትን በመንቀፍ ለቤተ ክርስቲያን መቃጠልና ለበርካታ ምእመናን ሞት መንሥኤም ሆኗል፡፡ ይህ የምዕራባውያን አስተሳሰብ የቤተ ክርስቲያንን ሕልውና መጋፋትና የተዋሕዶ ሃይማኖት አረንቋ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ ስለሆነም ከምን ጊዜውም የበለጠ ክርስቲያኖች በሃይማኖት እና በእምነት ሊጸኑ እንደሚገባ እንረዳለን፡፡
መጽሔተ ተልእኮ ዘማኅበረ ቅዱሳን መጽሔት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን በሕዝብ ግንኙነት አገልግሎት የተዘጋጅ ነው፡፡ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መጽሔቱን ያግኙ!
እስራኤላውን በግብፅ ባርነት በተገዙበት ዘመን ፈርዖን እስራኤላውያን ወንድ ልጅ ሲወልዱ እንዲገደል በአዋጅ አስነገረ፡፡ የሙሴም እናት ልጇ በፈርዖን ትእዛዝ መሠረት እንዳይገደልባት ስለ ፈርዖን ትእዛዝ ፍራቻ ልጇን በቅርጫት አድርጋ ወንዝ ውስጥ ጣለችው፡፡ …
ዕለታት በወራት ተተክተው፣ አዲስ ዓመት ዘመንን ወክሎ በጊዜ ዑደት ውስጥ ያልፋሉ፡፡ ሰማይና ምድር እያፈራረቁ ቀንና ሌሊትን፣ ፀሐይንና ዝናብን ይለግሳሉ፡፡ ክስተቶቹም አልፈው ዳግም እስኪመለሱ በሌሎች ይተካሉ፤ የእግዚአብሔር ስጦታ ‹‹ጊዜ›› እንደዚሁ እስከ ዓለም ፍጻሜ ይቀጥላል፡፡
በባሕሩ ማዕበል፣ በአውሎ ነፋሱ ውሽንፍር ጊዜ ጭምር ሕይወቱን ለተሳፋሪዎች ደኅንነት አሳልፎ ይሰጣል፤ ሊቀ ሐመር፡፡ ከመርከቡ ርቀው፣ ስፍራቸውንም ትተው ጠፍተውም እንዳይሰጥሙ ይከታተላቸዋል፡፡ እርሱ ጠባቂያቸው ነውና፡፡ ያለ ሥጋት ተጉዘው ወደ ባሕሩ ዳርቻ እንዲደርሱም በሰላም ይመራቸዋል፡፡
የእስክንድርያ ዐሥራ ሁለተኛ ጳጳስ የነበረው ቅዱስ ድሜጥሮስ ባሕረ ሀሳብን ሲደርሰው የቤተ ክርስቲያን ዕውቀት ያልነበረው በግብርና ሥራ የሚተዳደር ሰው ነበር፡፡ ሆኖም ለዘመናት ቤተ ክርስቲያን በዚህ ሥርዓት የተመራችበትን የዘመን አቆጣጣር በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ሊደርሰው ችሏል፤ ታሪኩም እንዲህ ነበር፡፡
