Entries by Mahibere Kidusan

የአቡነ ተክለ ሃይማኖት በዓለ ዕረፍት

ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሕይወታቸውን ሙሉ ለእግዚአብሔር በመስጠት፣ እንደ በሬ ተጠምደው፣ እንደ ገበሬ ታጥቀው ይህንን ዓለም ንቀው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በብሕትውና ከመኖራቸው ባሻገር እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ወንጌልን በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ የሰበኩ፤ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ድውያነ ሥጋን በተአምራት፣ ድውያነ ነፍስን በትምህርት የፈወሱ ሐዋርያ ናቸው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያችንም ነሐሴ ፳፬ ቀን የዕረፍታቸውን በዓል በትላቅ ደስታ ታከብራለች፡፡

‹‹ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስቡ ብፁዓን ናቸው›› (መዝ. ፵፥፩)

ሰዎች በቅን ልቡና ተነሣሥተው ችግረኞችን መርዳት ይችሉ ዘንድ እነማንን መርዳት እንዳለባቸው ማወቅ ተገቢ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ችግረኞችን ለይተን ማወቅ ካልቻልን የሚለምኑ ሁሉ ችግረኞች እየመሰሉን ርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ነዳያን ተገቢውን ርዳታ ላናደርግላቸው እንችላለን፡፡ ለዚህም መስፈርት አድርገን የምናስቀምጣቸው መሠረታዊ ነገሮች ምግብ፣ አልባሳትና መጠለያ ያልተሟላላቸውን ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የጤና እክል ያለባቸው፣ በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ የተያዙና ባለባቸው ችግር የተነሣ ሠርተው መብላት ያልቻሉ፣ አልባሽ አጉራሽ ቤተሰብም ሆነ ዘመድ የሌላቸውንም ችግረኞች እንላቸዋለን፡፡ በተጓዳኝ ረዳት ያጡ፣ ጠዋሪና ቀባሪ የሌላቸው አረጋውያን፣ ወላጅ አልባ ሕፃናት፣ በተለያዩ ምክንያቶች ቤት ንብረታቸውን አጥተው ከቀዬያቸው የተፈናቀሉትንም መርዳት ያስፈልጋል፡፡

‹‹ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል›› (መዝ. ፹፰፥፲፪)

በትንቢት ‹‹ታቦርና አርሞንኤም በስም ደስ ይላቸዋል›› ብሎ ነቢዩ ዳዊት እንደተናገረው ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን፣ ክብረ መንግሥቱን መግለጡን በማሰብ በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን በዓሉ በድምቀት ይከበራል፡፡ (መዝ. ፹፰፥፲፪)

‹‹ወደ አንተ የጮኹሁትን የልመናዬን ቃል ስማ›› (መዝ.፳፯፥፪)

መሪር በሆነችው በዚህች ዓለም ስንኖር እኛ ሰዎች ብዙ ችግርና ፈተና ሲያጋጥመንም ሆነ ለተለያዩ ሕመምና በሽታ ስንዳረግ እንዲሁም ለአደጋ ስንጋለጥ ስሜታችንን አብዛኛውን ጊዜ የምንገልጸው በዕንባ ነው፡፡ በተለይም አንድ ሰው የተጣለ መስሎ ሲሰማው በኃጢአቱ ምክንያት ቅጣት እንደመጣበት ሲያስብ ያለቅሳል፡፡ ጸጋ እግዚአብሔር እንደተለየው እግዚአብሔርም በጠላቶቹ እጅ አሳልፎ እየሰጠው እንደሆነ ሲያስብ ወደ ለቅሶ የሚያስገቡ መንፈሳዊ ምክንያቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በዚህም እጅግ ያዝናል፤ ያለቅሳልም፡፡ አንዳንዴ በፀፀት እና በንስሓ ውስጥ ሆኖ ያለቅሳል፤ አንዳንዴ ደግሞ እግዚአብሔርን እየወቀሰ ያለቅሳል፡፡

ጽኑ ተስፋ

ተድላ እና ደስታ ከሞላባት ገነት
ሥርዓተ ጾም ነው የተተከለባት
ደግሞም በሌላ መልክ የሞት ሕግ አለባት
የሕጉን ጽንዐት አዳም ጠነቀቀ
ከእባብም ሽንገላ ራሱን ጠበቀ…

ዕንባ በንስሓ ሕይወት

በመንፈሳዊ ሕይወታችን ውስጥ ዕንባ በብዙ ምክንያት ይፈጠራል፤ በየዋህነትና በልብ መነካት፣ የዓለምን ከንቱነት በመረዳት፣ ኃጢአትን በማሰብ፣ በፈተናና በችግር፣ ሞትን በማሰብ፣ በደስታና በስሜት፣ በጸሎት፣ በአቅመ ቢስነት፣ በብቸኝነት ስሜት፣ በሌላ ሥቃይ እና የሚታይ ፈንጠዚያ የተነሣ ሰዎች ያነባሉ፡፡በወንጌል በተጻፈው የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ታሪክ ውስጥ ለመግደላዊት ማርያም የቀረበላት ‹‹ስለምን ታለቅሻለሽ?›› የሚለውን የመላእክት ጥያቄም ሁላችን ልንመልስ ይገባል፤ ዕንባ ሁሉ ዋጋ የሚያስገኝ አይደለምና፡፡ (ዮሐ.፳፥፲፫)

በዚህ ዝግጅታችንም ኃጢአትን በማሰብ ለንስሓ የሚያበቃንን የዕንባ ዓይነት የፀፀትና የንስሓ ዕንባን እንመለከታለን፤ መልካም ንባብ!

‹‹ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም ተሻገረች››(ቅዱስ ያሬድ)

ቅድስት ድንግል ማርያም በምድር ላይ ለ፷፬  ዓመት በሕይወተ ሥጋ ከኖረች በኋላ ቅዱስ ያሬድ እንደተናገረው በጥር ፳፩ ቀን ከሚያልፈው ዓለም ወደ ማያልፈው ዓለም ተሻግራለች፡፡ «ፈለሰት እምዘይበሊ ኀበ ኢይበሊ፤ ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም፣ (ከምድር ሕይወት ወደ ሰማያዊ ሕይወት) ተሻገረች» እንዲል፤  (ዚቅ ዘቅዱስ ያሬድ ነሐሴ ፲፮)…
ከዚህም በኋላ ቅዱሳን መላእክት ክቡር ሥጋዋን በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር አኖራት፤ ከጥር ፳፩ እስከ ነሐሴ ዐሥራ ስድስት ቀን ለሁለት መቶ አምስት ቀናት ቆይታለች፡፡ …

‹‹በማስተዋል ዘምሩ›› (መዝ.፵፮፥፯)

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የምንሰማቸው አንዳንድ የኦርቶዶክሳዊ መዝሙራት  ይዘታቸውን እየለወጡ በመሄዳቸው አንዳንዶቹ እንዲያውም ወደ ዘፈንና ወደ መናፍቃን ዝማሬ ተቀይረው የጠላት ማሳቻ መንገድ እየሆኑ መምጣቸውን ሳንገነዘብ አልቀረንም፡፡ ነቢዩ ዳዊትም ‹‹በማስተዋል ዘምሩ›› ሲል በመዝሙሩ እንደተናገረው ኦርቶዶክሳዊ መዝሙራትን መለየትና በተለይም አምላካችንን የምናመሰግንበት፣ አጽዋማትና ክብረ በዓላትን የምንዘክርበት እንዲሁም በችግርና መከራ ጊዜ የምንማጸንበት የንስሓ መዝሙራትን ማወቅ ይኖርብናል፡፡ (መዝ.፵፮፥፯)

‹‹ባሕርም ሰገደችለት›› (ቅዱስ ያሬድ)

ባሕር በስፍሐቱ መጠን ከማንኛውም የውኃ ሙላት ይበልጣል፤ በተለይም በዘመነ ክረምት የባሕር መሰልጠን (ሙላት) ይሆናል፡፡ ቅዱስ ያሬድም ‹‹ደምፀ እገሪሁ ለዝናም ሶበ ይዘንም ዝናም ይትፌሥሑ ነዳያን፤ ይጸግቡ ርኁባን ምድርኒ ርእየቶ ወአእኰተቶ ባሕርኒ ሰገደት ሎቱ፡፡ የዝናም ድምፅ ተሰማ፤ ዝናብም በዘነበ ጊዜ ድሆች ደስ ይሰኛሉ፤ ረኃብተኞችም ይጠግባሉ፤ ምድር አየችው፤ አመሰገነችውም፤ ባሕርም ሰገደችለት›› በማለት እንደዘመረው በዘመነ ክረምት ባሕር ይሰለጥናል፡፡ (ድጓ ዘክረምት)