Entries by Mahibere Kidusan

‹‹የእግዚአብሔር ሰው›› (፩ኛሳሙ.፱፥፮)

ውድ የዚህ ጽሑፍ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? ዘመነ ክረምቱን/ዘመነ ጽጌን እግዚአብሔር ረድቶን ብዙ ተምረንበት አልፏል፡፡ከፊታችን ኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ ፳፰/፳፱ ድረስ ደግሞ ዘመነ ነቢያትን የምንዘክርበት፣ ‹‹ጾመ ነቢያት›› ብለን ከጾም ጋር አገናኝተን ስለ ነቢያትና ነቢይነት፣ እንዲሁም ስለ ትንቢት ዓላማና ምክንያቱ  ቤተ ክርስቲያን ብዙ የምታስተምርበት  ወቅት ነው፡፡

አበው ነቢያት!

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች!  እንዴት አላችሁ! መንፈሳዊ ሕይወት እንዴት ነው? በትምህርት ቤት፣ በሠፈር ውስጥ እንዲሁም በተለያየ ቦታ ስትገኙ በሥርዓት እና በአግባብ እንደምትኖሩ ተስፋችን እሙን ነው፤መልካም!!! ለዛሬ የምንነግራችሁ ስለ ቅዱሳን ነቢያት ነው፡፡

‹‹እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ›› (ኢያ.፭፥፲፫)

በቅድስና፣ በውዳሴ፣ በኅብረ ቀለም፣ በመላእክት ዝማሬ በደመቀው በዓለመ መላእክት ውስጥ ቅዱሳን መላእክት በነገድ ተከፍለው ይኖራሉ፡፡ እነርሱም የዘወትር ምግባራቸው እንዲያውም ምግባቸው ፈጣሪን ማመስገን ነው፡፡ ስፍር ቁጥር የሌላቸው መላእክቱም በሦስቱ የመላእክት ከተሞች ኢዮር፣ ራማ እና ኤረር በአላቃቸው ስር ሆነው ዘወትር አምላክን ያገለግላሉ፡፡ በኢዮር ከተማ ደግሞ የኃይላት አለቃ አድርጎ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልን ሾሞታል፤

የእግዚአብሔር ሠረገላዎች (መጽሐፈ ስንክሳር)

እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን በዕለተ እሑድ ሲፈጥር በነገድ መቶ በአለቃ ዐሥር አድርጎ በሦስቱ ሰማያት አስፍሯቸዋል፡፡ከእነዚህ ቅዱሳን መላእክት መካከል ኪሩቤል ይገኙበታል፤ኪሩብ አራት አራት ገጽ ካላቸው ከአራቱ ጸወርተ መንበር አንዱ ሲሆን፣ ፍችው መሸከምን፣ መያዝን ይገልጣል፡፡

በዓለ ደብረ ቁስቋም

በከበረች በኅዳር ስድስት ቀን የምናስበው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከተወደደ ልጇ ከመድኃኒዓለም፣ ከአረጋዊው ዮሴፍ እና ሰሎሜ ጋር ከስደት መመለስ እንዲሁም በቁስቋም ተራራ መገኘት ታላቅ በዓል ነው፡፡

‹‹ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ›› (መሓ.፯፥፩)

አሁን ኢትዮጵያውያ ስደተኛ መቀበል አትችልም ስደተኛ ሆናለችና፤ ሱላማጢስ ሆይ አሁን እነዚያ ደጋግ ሰዎች ለእንግዳ ማረፊያ አይሰጡም፤ እነርሱም ማረፊያ መጠለያ አጥተዋልና፤ አሁን የተራበን ለማብላት አቅም የላቸውም፤ እነርሱም ረኃብተኞች ናቸውና፡፡ እናታችን ሆይ ተመለሽ! ሰላማችን ሆይ ነይ! ወደ ዐሥራት ሀገርሽ ተመለሽ! ቃል ኪዳንሽንም አድሽ! የአዲስ ኪዳን ስደተኞች በኩር ሆይ ተመለሽ! መከራችን ያበቃ ዘንድ፣ እንባችን ይታበስ ዘንድ ተመለሽ!

የጸሎት ጊዜያት

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ? ትምህርት እንዴት ነው!እንግዲህ ልብ በሉ!በመንፈሳዊውም ሆነ በዘመናዊውም ትምህርት ተምራችሁ ማደግ አለባችሁ፤ባለፈው ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አንዱ ከሆኑት ስለ ጸሎት ጥቂት ብለናችሁ ነበር!ለዛሬ ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ ስለ ጸሎት ጊዜያት እንማማራለን!

የምእመናን ድርሻ በቤተ ክርስቲያን

እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰጣቸው ትልልቅ ስጦታዎች መካከል ዋነኛው የንስሓ መንገድ ሲሆን የእግዚአብሔር ቸርነቱ በሰፊው የሚገለጥበት የሕይወት መንገድ ነው። ንስሓ ዘማዊውን ድንግል የምታደርግ ቅድስት መድኃኒት ነች።

ፍቅር ኃያል!

ፍቅር ኃያል ፍቅር ደጉ

ወልድን ሳበው ከጸባኦት ከማዕረጉ
ፍቅር ደጉ ወልድን ሊያነግሥ በመንበሩ

በአንድ ጥለት በየዘርፉ በአንድ ጸና ማኅበሩ

ቃልም ከብሮ የዘውድ አክሊል ተቀዳጅቶ

ከምድር ላይ ከፍ…ከፍ…ከፍ…ብሎ ታይቶ

ተሠየመ በመስቀል ላይ…የነገሥታት ንጉሥ አብርቶ

በዚያች ልዩ ዕለት…ቀን ቡሩክ ቀን ፈራጅ

በዓለ ሢመቱ ሲታወጅ

ኀዘኑም ደስታውም በረከተ

ፍቅር ኃያል ፍቅር ሞተ!

‹‹ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ›› (መሓ.፯፥፩)

ውድ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? ከዚህ በፊት የእመቤታችንን የስደቷን ነገር አንሥተን ‹‹ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ›› በሚል ርእስ ከክፍል አንድ እስከ ሦስት አድርሰናችሁ ነበር፡፡ ጥሩ ትምህርት እንዳገኛችሁበት ተስፋ እናደርጋለን፡፡

የዛሬው ትኩረታችን ያን ሁሉ መከራ የተቀበለችበት የስደቷን ምክንያትና ዓላማ መዳሰስ ነው፡፡