በአሜሪካ ቦስተን ከተማ የበገና እና የመሰንቆ ተማሪዎች ተመረቁ

ሚያዝያ ፳፰/፳፻፲፰ ዓ.ም

 

በማኅበረ ቅዱሳን አሜሪካ ማእከል ቦስተን ንዑስ ማእከል በገና እና መሰንቆ በተለያየ ዙር ሲማሩ የነበሩትን በቦስተን አካባቢ የሚገኙ ሕጻናት እና አዋቂዎቸን ቅዳሜ ሚያዝያ ፳፬ ቀን ፳፻፲፰  ዓ.ም አስመርቋል።

 

በመርሐ ግብሩ አርባ አንድ የበገና እና ሦሰት የመሰንቆ ተማሪዎች የተመረቁ ሲሆን በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ የበገና እና የመሰንቆ ዝማሬ አቅርበዋል።

 

በመጨረሻም ለተመራቂዎች የምስክር ወረቀት እና የመስቀል ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

 

ዘገባው የአሜሪካ ማእከል ሚዲያ ክፍል ነው።