ለአንድ ወር ያክል ሲሰለጥኑ የቆዩ 28 ተተኪ አመራሮች መመረቃቸው ተገለጸ

ለአንድ ወር ያክል ሲሰለጥኑ የቆዩ 28 ተተኪ አመራሮች መመረቃቸው ተገለጸ

ሚያዝያ 20/2018 ዓ.ም

በማኅበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማእከል አባላትና ማስተባበሪያ አገልግሎት ዋና ክፍል ከየካቲት 14 እስከ መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለአንድ ወር ያክል ሲያሠለጥናቸው የቆዩ ተተኪ አመራር ሠልጣኞችን  ሚያዝያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም አስመርቋል።

በመርሐግብሩ  የማእከሉ መዘምራን ያሬዳዊ መዝሙር ያቀረቡ ሲሆን  ትምህርተ ወንጌል በመምህር ወገኔ ማሞ  ተሰጥቷል።

በተጨማሪም ተመራቂ ሠልጣኞች ተግባቦታችን ምን መምሰል አለበት በሚል አጭር ጭውውት ፣ የአመራር ብቃት እና የግጭት አፈታት ላይ ትኩረት ያደረገ ሦስት ጥናታዊ ጽሑፍ የቀረበ ሲሆን በጥናታዊ ጽሑፉ ላይ ውይይት ተካሒዷል።

በመርሐግብሩ ላይ ተገኝተው ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ያስተላለፉትን የማእከሉ ሰብሳቢ ዲ/ን ኃይለማርያም መድኅንን ጨምሮ ሌሎች የማእከሉ አባላት ተገኝተዋል ።

የዋና ማእከሉ የሥራ አመራር አባል የሆኑት አሠልጣኝ ዲ/ን ብርሀኑ ታደሰ በበኩላቸው ተመራቂዎች ለአገልግሎት እንዴት መትጋት እንዳለባቸው፣ በአገልግሎታቸውም በፈተና ሳይረቱ የማኅበሩን ዓላማ እና ርዕይ ተረድተው መቀጠል እንደሚገባቸው አሳስበዋል ።

በመጨረሻም ለተመራቂዎች የምስክር ወረቀት  ተሰጥቶ የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆናኗል ።

መረጃው ፦የማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ ነው

👇👇👇👇👇👇👇
የማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች ይቀላቀሉ
ቴሌግራም፡- http://t.me/mkpublicrelation
የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት፡- http://www.facebook.com/eotcmkidusan/
ድረገጽ፡- http://www.eotcmk.org
ዩ ቲዩብ፡- http://www.youtube.com/user/EOTCMK
:- https://www.youtube.com/@-zemawetibebzmk7905