መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርቶች


“ጾምን ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ”  (ኢዩ.፩፥፲፬)

ስብከት | አጽዋማት | ወቅታዊ ትምህርት


“ጾምን ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ” (ኢዩ.፩፥፲፬)

ከጾም የሥጋ ንጽሕና፣ የነፍስ ቅድስናና ድንግልና ይወለዳሉ።  ይህች ጾምም የጽድቅ ሥራዎች ሁሉ መርከብ ናት፤ በውስጧ የተከበሩ ዕቃዎች ሁሉ ይኖራሉ። ሩቅ ሀገር የሚሄዱት ያለ መርከብ በባሕር ላይ ፈጽሞ መሄድ እንዳይቻላቸው ሁሉ እንዲሁ ስለጽድቅ የሚጓዙትም በመንፈሳዊት ሐመር ካልታሳፈሩ አንዲት እርምጃ ስንኳን መራመድ አይቻላቸውም።" (ርቱዓ ሃይማኖት ገጽ ፺፩-፺፪)




ስብከት | ትምህርተ ሃይማኖት


ሥርዓተ አምልኮ

አምላካችን እግዚአብሔር ዓለምን ሲፈጥር ፍጥረት ሁሉ እንዲያመልከውና እንዲመሰግነው ነው፤ በአርአያውና በአምሳሉ የተፈጠርን ሰዎች ብቻም ሳይሆን በደመ ነፍስ የሚንቀሳቀሱ እንስሳት ሳይቀር ፈጣሪያቸውን ያመሰግናሉ፡፡ በተለይም በክርስቶስ ክርስቲያን ለተባልን ሰዎች የምናመልክበት የቅድስና ሕይወት ሰጥኖናል፡፡ ሕጉን ጠብቀን በሥርዓቱ ለምንኖር ለእኛ እርሱ ምሕረቱ የበዛ በመሆኑ በሕይወታችን ውስጥ ሊኖር ይወዳል፤ በቤቱም ስንገኝ ደስ ይሰኛል፡፡ እርሱን በዓይን…




አጽዋማት | ወቅታዊ ትምህርት


ጾመ ነነዌ

ይህን ቃል የምናገኘው በትንቢተ ዮናስ መጽሐፍ ውስጥ ነው፤ የተናገሩት ደግሞ እግዚአብሔርን የማያመልኩ ይልቁንም ጣዖት አምላኪ ሰዎች ናቸው። በነነዌ ሀገር ንጉሡ ስልምናሶር በነገሠበት ዘመን የነነዌ ሕዝቦች እግዚአብሔርን በደሉ፣ ከሥርዓቱ ፈቀቅ አሉ፤ ጣዖት አምላኪዎች ሆኑ፤ ጩኸትም አበዙ። እግዚአብሔርም ተቆጣቸውና ሊገሥጻቸው ዮናስን “ተነሥና ወደ ነነዌ ሀገር ግባ፤ በድለውኛልና ነነዌ በሦስት ቀን ትጠፋለች ብለህ…




ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን | ትምህርተ ሃይማኖት | ክርስቲያናዊ ሕይወትና ሥነ ምግባር | ወቅታዊ ትምህርት


ሥርዓተ አምልኮ

በዓላት ከማንኛውም ቀናት የበለጠ አምላካችን እግዚአብሔርን የምናመሰገንባቸውና የምናወድስባቸው፣ የተቀደሱትን ዕለታት በማሰብና በመዘከር በዝማሬ፣ በሽብሻቦና በእልልታ የምናከብርባቸው ናቸው፡፡ ታቦታት ከመንበረ ክብራቸው የሚወጡባቸውና ሕዝበ ክርስቲያኑን የሚባርኩባቸው ስለሆኑም በክብርና በድምቀት ይከበራሉ፡፡   





“ተክለ አብ፣ ተክለ ወልድ፣ ተክለ መንፈስ ቅዱስ”

በዓላት | ወቅታዊ ትምህርት | ዝክረ ቅዱሳን


“ተክለ አብ፣ ተክለ ወልድ፣ ተክለ መንፈስ ቅዱስ”

የካህን ልጅ ካህን፣ ምድራዊ የሆነ ሰማያዊ፣ ሰው ሲሆን መልአክ፣  ከሱራፌል ጋር የእግዚአብሔርን ዙፋን ያጠነ፣ ከመላእክት ጋር የተባበረ፣ ግዙፍ ሲሆን የረቀቀ፣ ባሕታዊ ሲሆን መምህር፣ ኢትዮጵያን በወንጌል ያበራ፣ የምድር ጨው፣ ስለአባታችን ተክለ ሃይማኖት ይህን እወቁ! የፀጋ ዘአብ ዘር ምን ያህል ቡርክት ነች፤ የእግዚእኃረያ ማህፀን ምን ያህል ለምለም ነች!? አንደበቱ ለምስጋና የተፈታ፣ መላእክት…




ስብከት | ትምህርተ ሃይማኖት | ወቅታዊ ትምህርት


ሥርዓተ አምልኮ

በጸሎትና በስግደት እንዲሁም በምጽዋት የታገዘ ጾም በእግዚአብሔር ፊት የተወደደ በመሆኑ ድኅነትን ማሰጠት ብቻም ሳይሆን በረከትን ያስገኛል፡፡ በዚህም የተነሣ ሥራችን፣ ትዳራችን እንዲሁም አገልግሎታችን ይባረክልናል፡፡




ትምህርተ ሃይማኖት


ሥርዓተ አምልኮ

ሥርዓት  “ሠርዐ” ሠራ ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ደንብ፣ አሠራር፣ መርሐ ግብር ማለት ነው። በሃይማኖት ውስጥ የሚፈጸም የመንፈሳዊ አገልግሎትና አሠራር እንዲሁም ክርስቲያናዊ ሥርዓትን ያመለክታል።  ሥርዓተ አምልኮት የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ አምልኮት ለአምላካችን እግዚአብሔር የሚቀርብ ሥርዓት ነው፡፡ ይህም ሥርዓተ ጸሎትን፣ ሥርዓተ ጾምን፣ ሥርዓተ ምጽዋት፣ ሥርዓተ ስግደትን፣ ሥርዓተ በዓላትን፣…





በዓታ ለማርያም

በዓላት | ወቅታዊ ትምህርት


በዓታ ለማርያም

ታኅሣሥ በባተ በሦስተኛው ቀን የሚታሰበውና የሚከበረው በዓል ‹‹በዓታ ለማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡ ከእናቷ ከቅድስት ሐና እና ከአባቷ ቅዱስ ኢያቄም በስዕለት የተወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት የከበረ እንደመሆኑ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ታከብረዋለች፡፡





ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ

ምንባባት | በዓላት | ወቅታዊ ትምህርት


ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ

በሀገረ አንጾኪያ ከአሕዛብ ወገን የተለወደው አይሁዳዊው ሉቃስ ከሰባ ሁለቱ አርድእት የተቆጠረ ባለ መድኃኒትና ወንጌልን የጻፈ ቅዱስ ሐዋርያ ነው፡፡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በወንጌል ትርጓሜያቸው ስሙ ‹ዓቃቤ ሥራይ› ወይም ‹ባለ መድኃኒት› የሚል ትርጉም በውስጡ የያዘ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ በላቲን ቋንቋ ‹ሉካስ› ማለት ‹ብርሃናማ፣ ብርሃን የያዘ› ማለት ነው፡፡ መጽሐፈ ስንክሳር ደግሞ ብልህና ጥበበኛ በማለት…





ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ

ለሕፃናት | በዓላት | ወቅታዊ ትምህርት


ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች እንዴት አላችሁልን? ትምህርት እንዴት ነው? መቼም በክረምቱ የዕረፍት ጊዜያችሁ ትምህርት እስኪከፈት በጣም ጓጉታችሁ እንደነበር እናስባለን! ይኸው ተከፈተላችሁ! እንግዲህ በርትታችሁ ከአሁኑ መማር፣ ማጥናት፣ የቤት ሥራን መሥራት፣ ያልገባችሁን መጠየቅ ይገባችኋል፡፡ ገና ነው እያላችሁ እንዳትዘናጉ ጥናቱን አሁኑኑ ጀምሩ! የጨዋታም ሆነ ቴሌቪዥን የምታዩበት ጊዜ ከትምህርታችሁ ጋር በማይጋጭ መልኩ መሆን አለበት፡፡ ከሁሉም…