በዓይኖችህ ታየዋለህ
በሰማርያ ረኃብ በጸናበት ዘመን የሚቀመስም ጠፋ፤ ከረኃቡ ጽናት የተነሣ እናት ልጇን እስከ መብላት ደረሰች። በእዚያም ሀገር ኤልሳዕ የሚባል የእግዚአብሔር ሰው ነበረ። እንዲህም አለ፤ ነገ በዚህች ከተማ በአንድ ሰቅል አንድ መሥፈርያ መልካም ዱቄት በአንድ ሰቅል ሁለት መስፈርያ ገብስ ይሸመታል። ያኔ ንጉሡ በእግዚአብሔር ላይ ተገዳደረ፤ እንዴት ይቻላልም አለ። የእግዚአብሔር ሰው ኤልሳ እንዲህ አለው፤ “ታየዋለህ እንጅ አትቀምሰውም” ልብን የሚከፍል ንግግር! በረኃብ የቆየች ሀገር ደስ በምትሰኝበት ሰዓት የማይጨበጥ ሕልም ሲሆን ምንኛ ያሳዝናል? የሶርያ ንጉሥ ሲመኘው የኖረውን ነገር በዓይኑ አየው ግን አልቀመሰውም። (፪ኛነገ.፯፥፪)