‹‹ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም ተሻገረች››(ቅዱስ ያሬድ)
ቅድስት ድንግል ማርያም በምድር ላይ ለ፷፬ ዓመት በሕይወተ ሥጋ ከኖረች በኋላ ቅዱስ ያሬድ እንደተናገረው በጥር ፳፩ ቀን ከሚያልፈው ዓለም ወደ ማያልፈው ዓለም ተሻግራለች፡፡ «ፈለሰት እምዘይበሊ ኀበ ኢይበሊ፤ ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም፣ (ከምድር ሕይወት ወደ ሰማያዊ ሕይወት) ተሻገረች» እንዲል፤ (ዚቅ ዘቅዱስ ያሬድ ነሐሴ ፲፮)…
ከዚህም በኋላ ቅዱሳን መላእክት ክቡር ሥጋዋን በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር አኖራት፤ ከጥር ፳፩ እስከ ነሐሴ ዐሥራ ስድስት ቀን ለሁለት መቶ አምስት ቀናት ቆይታለች፡፡ …