የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል

በንጉሥ ናቡከደነፆር ዘመነ መንግሥት እስራኤላውያንን በባቢሎናውያን ቅኝ ግዛት ሥር በወደቁበት ጊዜ ከአይሁድ ወገን የሆኑ አዛርያ፣ አናንያ እና ሚሳኤል የተባሉ ሦስት ሕፃናትም ተማርከው በባርነት ተወሰዱ፡፡ ንጉሡም መልካቸው ያመረ፣ የንጉሣዊና የመሳፍንት ልጆች የሆኑትን መርጦ ሥነ ጥበብ፣ የመንግሥት አስተዳደርና የባቢሎናውያን ቋንቋዎችን እንዲሠለጥኑ ለማድረግ በቤተ መንግሥቱ አስቀመጦ ይቀልባቸው ጀመር፡፡…

‹‹አባታችሁ አብርሃም የእኔን ቀን ያይ ዘንድ ተመኘ፤ አይቶም ደስ አለው›› (ዮሐ. ፰፥፶፮)

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልን በሰበከበት በዘመነ ሥጋዌ እርሱ የሚያስተምረውን ትምህርት እና የሚያደርገውን ገቢረ ተአምራት ወመንክራት ሰምተውና አይተው አይሁድ ቅናት አደረባቸው፡፡ ጌታችንንም በክፋት በሚከታተሉበት ጊዜ የእርሱን ጌትነትና የባሕርይ አምላክነት በትምህርት እየገለጠ ብዙ ተአማራት ቢያሳያቸውም በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ እንዲሁም በሥጋ ተገልጦ ሲመላለስ ስላዩት አምላክነቱን ተጠራጥረው እንዲህ አሉት፤ ‹‹በውኑ ከሞተው ከአባታችን አብርሃም ትበልጣለህን? ነቢያትም ሞቱ፤ ራስህን ማን ታደርጋለህ?›› (ዮሐ. ፰፥፶፫-፶፱)…

‹‹መገሠጽስ እግዚአብሔር ገሠጸኝ፤ ለሞት ግን አሳልፎ አልሰጠኝም›› (መዝ. ፻፲፯፥፲፰)

ተግሣጽ የሚለው ቃል እንደየገባበት ዐውድ እና እንደየተነገረበት ዓላማ የተለያየ ፍቺ ቢኖረውም በመዝገበ ቃላት ደረጃ ቤተ ክርስቲያናችን ካፈራቻቸው ሊቃውንት አንዱ የሆኑት አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት ሐዲስ በተሰኘ መጽሐፋቸው (ገጽ ፫፻፳፯) ‹‹ተግሣጽ›› ማለት ትምህርት፣ ብርቱ ምክር፣ ምዕዳን፣ ኀይለ ቃል፤ እና ቁጣ ብለው ተርጉመውት ይገኛል፡፡

ዘመነ ስብከት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዘመን አከፋፈል መሰረት ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በፊት ከታኅሣሥ ፯ ጀምሮ እስከ ፳፱ ያለው ወቅት ዘመነ ስብከት ይባላል፡፡ እያንዳንዱ ሳምንታትም ስብከት፣ ብርሃን እና ኖላዊ በሚል ስያሜ ይታወቃሉ፡፡ በዚህም ወቅት ስለ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር መምጣት መወለድ ነቢያት የተናገሩት ትንቢት በስፋት ይነገርበታል፡፡

በአታ ለማርያም

ጥንትም ስትታሰብ በአምላክ ኅሊና

ትታወቅ ነበረ በሥሉስ ልቡና

በአቷን አደረገች የአርያም መቅደስ

የዓለሙን ፈጣሪ ዘወትር ለማወደስ…

‹‹ወደ ጠባቡ በር ትገቡ ዘንድ በርቱ›› (ሉቃ. ፲፫፥፳፬)

በምድራዊ ሕይወት ሰዎች የሥጋ ፈቃዳቸውን ብቻ መፈጸማቸው ለኃጢአታቸው መብዛት መንሥኤ ይሆናል፤ በጾም በጸሎት እንዲሁም በስግደት ስለማይተጉና በመከራ ስለማይፈተኑም እንደፈለጉ በመብላት በመጠጣት፣ ክፋት በመሥራት እንዲሁም ሰውን በመበደል በድሎት እንዲኖሩ ዓለም ምቹ ትሆንላቸዋለች፡፡ ዓለማዊነት መንገዱ ሰፊ በመሆኑ የሥጋ ፈቃዳችን የምንፈጽምበት መንገድም በዚያው ልክ ብዙ ነው፡፡

ክርስቲያናዊ አንድነት

ክርስቲያናዊ አንድነት በእምነት አንድነትና በአስተምህሮ ስምምነት የሚገለጥ ነው፡፡ በዚህም በክርስቶስ ክርስቲያን የተባልን ሰዎች የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት በማመን፣ ከሀብተ መንፈስ ቅዱስ በመወለድ፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን በመቀበል በአጠቃላይ ለሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን በመገዛት መኖር ማለት እንደሆነ እንረዳለን፡፡