ክርስቲያናዊ ሕይወትና ምግባር (ሦስተኛ መጽሐፍ)

በሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ
 
አንድ ሰው የሚያንበትን እምነት ፣ የሚመራበትን ሕግ ፣ የሚያልመውን ተስፋና የሚወደውን ነገር ተከትሎ ከግቡ ለማድረስ ማድረግ ያለበትን በማድረግ ማድረግ የሌለበትን በመተው በነፃ ፈቃዱ ወስኖ በሙሉ ልቦናው በሙሉ ኃይሉ የሚያደርገው የውስጥና የውጭ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ፣ ጥረትና ትግል ነው፡፡