በዓሉን ለማክበር ርብርቡ ቀጥሏል

ግንቦት 25 ቀን 2004 ዓ.ም

የማኅበሩ 20ኛ ዓመት ምሥረታ በዓል የእግር ጉዞ በማዘጋጀት አዲሱ ገበያ አካባቢ በሚገኘው በመንበረ ክቡር ቅዱስ ሚካኤልና አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ለማክበር ቀደም ብሎ የታቀደ ቢሆንም መርሐ ግብሩ እሑድ ግንቦት 26 ቀን 2004 ዓ.ም. በጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ ለማክበር ተወስኗል፡፡ በዚህም መሠረት መርሐ ግብሩን የተሳካ ለማድረግ የተግባር ቤት (ምግብ ዝግጅት) አገልግሎት እየተቀላጠፈ ይገኛል፡፡ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ ድንኳን በመትከልና ሌሎችም ቅድመ ዝግጅቶች በመካሔድ ላይ ናቸው፡፡

ነገ የሚካሔደውን መርሐ ግብር በማኅበሩ መካነ ድር www.eotcmk.org እና በፌስ ቡክ http://www.facebook.com/mahiberekidusan በቀጥታ ስርጭት የምናስተላልፍ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

{gallery count=1 width=350 height=300 counter=1 links=0 alignment=center animation=3000}mk20th year{/gallery}