በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/በሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ -  ማኅበረ ቅዱሳን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ማኅበሩ
    • ማእከላት
      • ሰሜን አሜሪካ
      • አውሮፓ
      • ሩቅ ምሥራቅ
      • ደቡባዊ አፍሪካ
      • የካናዳ ማእከል
      • አዲስ አበባ ማእከል
        • የወርሃዊ አስተዋጽኦ መሰብሰቢያ
    • ኅትመት እና ሚዲያ
      • ሐመር እና ስምዐ ጽድቅ
      • ማኅበረ ቅዱሳን ቲቪ
      • የማኅበረ ቅዱሳን ዩቲዉብ
      • መጽሔተ ተልዕኮ
      • ማእከለ ሥዕላት
        • ካሜራው ምን ይላል
        • የቅዱሳት ሥዕላት ማኅደር
  • ትምህርቶች
    • የርቀት ትምህርት
    • ስብከት
    • መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርቶች
  • ግቢ ጉባኤ
  • ሌሎች ድረ ገጾች
    • በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ የብፁዕ ወቅዱስ ልዩ ጽ/ቤት ድረ ገጽ
    • በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ድረ ገጽ
    • በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ድረ ገጽ
  • ቋንቋ
    • አማርኛ
    • ትግርኛ
    • ወላይትኛ
    • ሲዳምኛ
    • Affan Oromo
    • English
  • ያግኙን
  • Click to open the search input field Click to open the search input field Search
  • Menu Menu

ማኅበረ ቅዱሳን ከቤተ ክርስቲያን ህልውና በላይ የሚያስቀድመው አንዳች ነገር የሌለ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን የገጠማትን ፈተና ለማለፍ የሚጠበቅበትን መንፈሳዊ ግዴታ ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን የካቲት ፲፱/፳፻፲፮ ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

You are here: Home1 / ዜና2 / ማኅበረ ቅዱሳን ከቤተ ክርስቲያን ህልውና በላይ የሚያስቀድመው አንዳች ነገር የሌለ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን የገጠማትን ፈ...

ማኅበረ ቅዱሳን ከቤተ ክርስቲያን ህልውና በላይ የሚያስቀድመው አንዳች ነገር የሌለ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን የገጠማትን ፈተና ለማለፍ የሚጠበቅበትን መንፈሳዊ ግዴታ ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን የካቲት ፲፱/፳፻፲፮ ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

ማኅበሩ በመግለጫው የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን መንፈሳዊ አንድነት የጠየቀ ሲሆን “ቤተ ክርስቲያንን በማይጠቅማት ጉዳይ የግል ፍላጎትንና ምድራዊ ዓላማን መሠረት አድርገው ከቤተ ክርስቲያን ሕግና ቀኖና ውጭ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊን ለመተካት፣ ፓትርያርክ ለመሾምና የመሳሰሉትን ለመፈጸም” የሚንቀሳቀሱ ያላቸውን “አንዳንድ አባቶች” ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በማሳሰብ ጉዳዩንም በመከታተል መረጃውን ለምእመናን አደርሳለሁ ብሏል።፡፡

ይመለከታቸዋል ላላቸው ሌሎች የቤተ ክርስቲያን አካለትም ጥሪውን አስተላልፏል።

፩.  የተከበራችሁ አበው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሆይ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ “በገዛ ደሙ  የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ   ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፡፡ እንዳለ በዚህ ታላቅ የፈተና   ወቅት የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለማስጠበቅ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጣችሁን ኃላፊነት ለመወጣት ምእመናንን አቅጣጫ በመስጠት የቀደሙ አባቶቻችሁን ፈለግ በመከተል ዛሬም በጽናት እንድትተጉ፤ ያከበረቻችሁን ቤተ ክርስቲያን በአንድነት ሆናችሁ እንድትጠብቁ በልጅነት መንፈስ በትሕትና እንጠይቃለን፡፡ በተጨማሪም የአባትነት የዋህ ልቦናችሁን በመጠቀም ያዘኑ፣ የጠቀሙ፣የተቆረቆሩ መስለው ቀርበው የግል ፍላጎታቸውን ለመፈጸም የሚጥሩ ስለሚኖሩ ሁሉንም በጥንቃቄ   እንድትመረምሩ፤ቀኖች ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን በመዋጀት አንድነታችሁን እንድታጠነክሩና በቤተክርስቲያን ዙሪያ ስለሚፈጠሩ ችግሮች በጥልቀት እንድትወያዩና እንድትመካከሩ እናሳሰስባለን።

፪.   ከዚህ ውጭ ቤተ ክርስቲያንን በማይጠቅማት ጉዳይ የግል ፍላጎትንና ምድራዊ ዓላማን መሠረት አድርጋችሁ ከቤተ ክርስቲያን ሕግና ቀኖና ውጭ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊን ለመተካት፣ ፓትርያርክ ለመሾምና የመሳሰሉትን ለመፈጸም የምትንቀሳቀሱ አንዳንድ አባቶች ከድርጊታችሁ እንድትታቀቡ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ ማኅበራችን ይህንን ጉዳይ እየተከታተለ መረጃውን ለምእመናን የሚያደርስ መሆኑንም በዚሁ አጋጣሚ እንገልጻለን፡፡

፫. ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ መምህራነ ወንጌል፣ ካህናት ሆይ በጸሎትና በትምህርት ምእመናንን በማጽናናት፤ ከእውነት ጋር በመቆም እውነታውን በማሳየት ምእመናን ለቤተ ክርስቲያን ዘብ እንዲቆሙ በማድረግ ድርሻችሁን እንድትወጡ እናሳስባለን።

፬.     ውድ ምእመናንና የማኅበራችን አባላት የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ በዚህ ዘመን ቤተ ክርስቲያንን ከአሳዳጆቿ የመጠበቁ ዋነኛ ኃላፊነት በዘመኑ ባለን ብፁዓን አባቶች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርሰቲያን፣ ካህናትና ምእመናን ሁላችን እጅ ላይ ወድቆአል፡፡  የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ ለአባቶችና ለካህናት ትተን “እኔ አያገባኝም፤ አይመለከተኝም” ልንል አይገባም፡፡ ሁሉም በየድርሻው ቤተክርስቲያኑን ለመጠበቅ መትጋት አለበት፡፡ በቤተ ክርስቲያን ላይ የደረሰውን ጥፋትና ሊመጣ ያለውን ፈተና አስቀድሞ በመረዳት ቅዱስ ሲኖዶስ ቀደም ሲል በወሰነው መሠረት በየአጥቢያችን፤ በተለያየ መልኩ በመደራጀት፤ በቤተክርስቲያን ላይ ጥፋት ለማድረስ የሚመጡትን በመከላከል የቤተ ክርስቲያንን ስደት ለማስቆም መንፈሳዊ ግዴታችንን እንድንወጣ እንጠይቃለን፡፡

፭.     በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በልዩ ልዩ አገልግሎት እየተሳተፋችሁ ያላችሁ ሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ ማኅበራትና ሌሎችም ሁላችንም አንድነታችንን በመጠበቅ በጋራ አገልግሎቶችን በመፈጸም  ድርሻችንን እንድንወጣ ለተግባራዊነቱ ጥሪ እናቀርባላን፡፡

፮.     ገዳም ድረስ ገብቶ መሣሪያ ያልያዙና: ራሳቸውን  እንደሞቱ ቆጥረው እየኖሩ ያሉ መነኮሳት ላይ  ግድያ የፈጸመ ማንኛውም የታጠቀ ኃይል (መደበኛም ይሁን ኢ-መደበኛ በግልም ይሁን በቡድን: አማኝም  ይሁን ኢአማኝ)  ድርጊቱ ከሰውነት ተፈጥሮ የወጣ ነው፡፡ ምናኔንና የክህነት ክብርን በተቃረነ መልኩ ሰብእና የጎደለው ጥቃት ማድረስ ኢትዮጵያዊ ባህልም አይደለም፡፡ ጥቅም የሌለው ከንቱ ተግባር ነው፡፡ በዚህ የሚገኝ የፖለቲካ ትርፍ ይኖራል ብለን አናምንም፡፡ ጤነኛ በሆነ አእምሮ ታስቦ የተፈጸመ ነው ማለትም አይቻልም፡፡  ማስተዋል ተወስዶባቸው እውቀት ተሰውሮባቸው እንጂ ይህንን ማድረግ ቀርቶ ማሰቡም የሙት ሐሳብ ነው፡፡ ቀድሞ የሞተው ሟቹ ሳይሆን ገዳዩ ነው፡፡ በዚህ መንገድ የቤተ ክርስቲያን አማኞች  ሲበዙ እንጂ ሲያንሱ በታሪክ አልታየም:: ይህ ድርጊት ክርስቲያኖችን ሲያጠነክር እንጂ ሲያዳክም ታይቶ አይታወቅም፡፡ መጽሐፍ “ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንን ቤት ገፋው በዓለት ላይ ስለተመሠረተ አልወደቀም” ባለው መሠረት ቤተክርስቲያን በጽኑ ዐለት ላይ የተመሠረተች ስለሆነ አታሽነፏትም። ዲዮቅልጥያኖስም አላጠፋትም:: ዲያብሎስም ዝናሩን እንዲሁ ጨረሰ:: ስለዚህ አትድከሙ: አትሳቱም እናንተ ሳትወለዱ የነበረች ቤተ ክርስቲያን እናንተ አልፋችሁም እንደ እናንተ ላሉት በስሑት መንገድ ለሚጓዙት ሁሉ እየጸለች ትቀጥላለች:: ሐሳቧም፣ ሥራዋም፣ ዓላማዋም፣ ግቧም ሰማያዊ ነውና።

በመጨረሻም ማኅበረ ቅዱሳን ከቤተ ክርስቲያን ህልውና በላይ የሚያስቀድመው አንዳች ነገር የሌለ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን የገጠማትን ፈተና ለማለፍ ከሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያን አካላት ጋር በመናበብ የሚጠበቅበትን መንፈሳዊ ግዴታ ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን በዚሁ አጋጣማ እያሳወቅን፥ የሁላችንም የመሰባሰብና የአገልግሎት ማእከል ቤተ ክርስቲያን በመሆኗ ከሁሉም ነገር በፊት ቅድሚያ ሰጥተን ሊመጣ ካለው አደጋ ቤተ ክርስቲያናችንን የመጠበቅ ኀላፊነት በትጋት እንወጣ ሲል ማኅበረ ቅዱሳን በመግለጫው ጥሪ አቅርቧል፡፡

በፌስቡክ የትስስር ገጽ ያግኙን

Search Search

አዳዲስ ጽሑፎች

  • “ደቀ መዛሙርት የቤተ ክርስቲያን ደጀን ናቸው።” ሲሉ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ ተናገሩ።
  • በዓለ ደብረ ታቦር
  • የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ቀኖና በማስጠበቅ ሥርዓቷን ለትውልድ እናስተላልፍ !(መልእክት ዘማኅበረ ቅዱሳን )
  • ቅዱስ ፓትርያርኩ ጾመ ፍልሰታ ለማርያምን ምክንያት አድርገው መልእክት አስተላለፉ።
  • የሰማዕተ ጽድቅ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ እና የብፁዕ  አቡነ ጎርጎርዮስ መታሰቢያ መርሐ ግብር ተካሄደ
  • ቅድስት ኢየሉጣና ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ
  • እስመ ለመላእክቲሁ ይኤዝዞሙ በእንቲአከ/ መላእክቱን ስላንተ ያዛቸዋል. (መዝሙር ፺፥፲፩)
  • በተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች መመረቃቸው ተገለጸ።
  • መጽሔተ ተልእኮ
  • ማኅበረ ቅዱሳን በተለያዩ ቋንቋዎች የመዝሙር አልበሞችን በማዘጋጀት ተደራሽ እያደረገ እንደሚገኝ ገለጸ
  • አብርሃም ርእየ ፫ተ እደወ፤ በዛቲ ዕለት ምሥጢረ ሥላሴ ዜነወ።
  • በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
  • ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
  • ዘመነ ክረምት
  • “መሠረተ ሃይማኖት” የተባለ የልጆች መጽሐፍ የፊታችን እሑድ እንደሚመረቅ የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ገለጸ

የጽሑፎች ማውጫ – በወራት

© Mahibere Kidusan - All Rights Reserved. Website by MK-IT
  • Link to Facebook
Link to: “ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል፤ ድል ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው” (ምሳሌ ፳፩÷፴፩) Link to: “ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል፤ ድል ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው” (ምሳሌ ፳፩÷፴፩) “ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል፤ ድል ግን ከእግዚአብሔር... Link to: አድዋን ያለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ማሰብ ትርጉም አልባ ነው! Link to: አድዋን ያለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ማሰብ ትርጉም አልባ ነው! አድዋን ያለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ማሰብ ትርጉም...
Scroll to top