መሰረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርቶች
በዓላት ከማንኛውም ቀናት የበለጠ አምላካችን እግዚአብሔርን የምናመሰገንባቸውና የምናወድስባቸው፣ የተቀደሱትን ዕለታት በማሰብና በመዘከር በዝማሬ፣ በሽብሻቦና በእልልታ የምናከብርባቸው ናቸው፡፡ ታቦታት ከመንበረ ክብራቸው የሚወጡባቸውና ሕዝበ ክርስቲያኑን የሚባርኩባቸው ስለሆኑም በክብርና በድምቀት ይከበራሉ፡፡
የካህን ልጅ ካህን፣ ምድራዊ የሆነ ሰማያዊ፣ ሰው ሲሆን መልአክ፣ ከሱራፌል ጋር የእግዚአብሔርን ዙፋን ያጠነ፣ ከመላእክት ጋር የተባበረ፣ ግዙፍ ሲሆን የረቀቀ፣ ባሕታዊ ሲሆን መምህር፣ ኢትዮጵያን በወንጌል ያበራ፣ የምድር ጨው፣ ስለአባታችን ተክለ ሃይማኖት ይህን እወቁ! የፀጋ ዘአብ ዘር ምን ያህል ቡርክት ነች፤ የእግዚእኃረያ ማህፀን ምን ያህል ለምለም ነች!? አንደበቱ ለምስጋና የተፈታ፣ መላእክት…
በጸሎትና በስግደት እንዲሁም በምጽዋት የታገዘ ጾም በእግዚአብሔር ፊት የተወደደ በመሆኑ ድኅነትን ማሰጠት ብቻም ሳይሆን በረከትን ያስገኛል፡፡ በዚህም የተነሣ ሥራችን፣ ትዳራችን እንዲሁም አገልግሎታችን ይባረክልናል፡፡
ሥርዓት “ሠርዐ” ሠራ ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ደንብ፣ አሠራር፣ መርሐ ግብር ማለት ነው። በሃይማኖት ውስጥ የሚፈጸም የመንፈሳዊ አገልግሎትና አሠራር እንዲሁም ክርስቲያናዊ ሥርዓትን ያመለክታል። ሥርዓተ አምልኮት የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ አምልኮት ለአምላካችን እግዚአብሔር የሚቀርብ ሥርዓት ነው፡፡ ይህም ሥርዓተ ጸሎትን፣ ሥርዓተ ጾምን፣ ሥርዓተ ምጽዋት፣ ሥርዓተ ስግደትን፣ ሥርዓተ በዓላትን፣…
ታኅሣሥ በባተ በሦስተኛው ቀን የሚታሰበውና የሚከበረው በዓል ‹‹በዓታ ለማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡ ከእናቷ ከቅድስት ሐና እና ከአባቷ ቅዱስ ኢያቄም በስዕለት የተወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት የከበረ እንደመሆኑ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ታከብረዋለች፡፡
በሀገረ አንጾኪያ ከአሕዛብ ወገን የተለወደው አይሁዳዊው ሉቃስ ከሰባ ሁለቱ አርድእት የተቆጠረ ባለ መድኃኒትና ወንጌልን የጻፈ ቅዱስ ሐዋርያ ነው፡፡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በወንጌል ትርጓሜያቸው ስሙ ‹ዓቃቤ ሥራይ› ወይም ‹ባለ መድኃኒት› የሚል ትርጉም በውስጡ የያዘ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ በላቲን ቋንቋ ‹ሉካስ› ማለት ‹ብርሃናማ፣ ብርሃን የያዘ› ማለት ነው፡፡ መጽሐፈ ስንክሳር ደግሞ ብልህና ጥበበኛ በማለት…
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች እንዴት አላችሁልን? ትምህርት እንዴት ነው? መቼም በክረምቱ የዕረፍት ጊዜያችሁ ትምህርት እስኪከፈት በጣም ጓጉታችሁ እንደነበር እናስባለን! ይኸው ተከፈተላችሁ! እንግዲህ በርትታችሁ ከአሁኑ መማር፣ ማጥናት፣ የቤት ሥራን መሥራት፣ ያልገባችሁን መጠየቅ ይገባችኋል፡፡ ገና ነው እያላችሁ እንዳትዘናጉ ጥናቱን አሁኑኑ ጀምሩ! የጨዋታም ሆነ ቴሌቪዥን የምታዩበት ጊዜ ከትምህርታችሁ ጋር በማይጋጭ መልኩ መሆን አለበት፡፡ ከሁሉም…
ቅድስት አርሴማ
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! ለከበረው ጤንነታችሁ እንዴት አላችሁ! የክረምት ወቅት አልፎ አዲሱን ዓመት ተቀብለናልና ለዚህ ያደረሰንን ፈጣሪያችንን ማመስገን ይገባል! ልጆች! መስቀል በዓል እንዴት ነበር? በሰላም በፍቅር አከበራችሁ አይደል? የእኛን ምክርም ተቀብላችሁ ለመጪው የትምህርት ዘመን ዝግጅት ስታደርጉ እንደቆያችሁ ደግሞ ተስፋችን ነው፡፡ አሁን ደግሞ ትምህርት ስለጀመራችሁ በርትታችሁ መማርን እንዳትዘንጉ! ከአሁኑ ጀምራችሁ መምህራን የሚነግሯችሁን…
ምድር በአበቦችና በዕፅዋቶች ተሞልታ የምታሸበርቅበት ወቅት የጽጌ ወር በክርስቲያናዊ ሕይወታችን ውስጥ ትልቅ ትርጉም አለው፡፡ የመዳኛችን ተስፋ የሆነችውና የዓለምን ቤዛ የወለደችን ቅድስት ድንግል ማርያም አበባውን በሚያስገኙት ዕፀዋትና በምድር፣ የተወደደ ልጇ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ በአበባው እንደሚመሰሉ ቀደምት ነቢያት አስተምረውናል፡፡
ጉባኤ ኒቅያ
ጉባኤ ኒቅያ ቤተ ክርስቲያን አንድነቷን የጠበቀችበት፣ አርዮስና አርዮሳውያን የተወገዙበት፣ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት፣ አዳኝነት፣ ጌትነት፣ መድኃኒትነት የተመሠከረበት፣ ኦርቶዶክስ የሚለው ስም ትምክህት የሆነበት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ይህን ጉባኤ ትቀበላለች፤ ትልቅም ስፍራ አላት፡፡