መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ
ስምና የስም ዓይነቶች
የስም ሙያ
ቃላት በዐረፍተ ነገር ላይ ያለ ሙያ ሊገቡ አይችሉም፡፡ ስምም ከቃል ክፍሎች እንደመሆኑ መጠን ያለ ሙያ በዐረፍተ ነገር ውስጥ ሊገባ አይችልም፡፡ ስም በዐረፍተ ነገር ውስጥ ሦስት ሙያዎች አሉት፡፡ እነሱም ባለቤትነት፣ ተሳቢነትና ቅጽልነት ናቸው፡፡
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስደት በወርኀ ጽጌ (ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፭)
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በወርኀ ጽጌ ወደ ግብፅና ኢትዮጵያ ተሰዳ ነበር ፡፡ ጌታን ፀንሳ በነበረች ጊዜ ለዮሴፍ አንዳንድ ጊዜ እንደ ጽጌረዳ አበባ ቀይ ሁና፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ እንደ ሮማን አበባ ነጭ ሁና ስትታየው፤ ቀይ የነበረው መልኳ ተለውጦ እንደ ሮማን አበባ ጸዓዳ ነጭ፣ ነጭ የነበረው እንደ ጽጌረዳ ቀይ ሲሆንና የሚያውቀው መልኳ ሲለዋወጥበት ዮሴፍ እየደነገጠ እርሷ መሆኗን ‹‹ማርያም›› እያለ ያረጋገጠጥ ነበር፡፡
እውነት ከመስቀሉ ጋር እየተጓዝን ነውን?
‹‹ጥልንም በመስቀሉ ገደለ›› ኤፌ.፪፥፲፮
የዓለም ሰላም የተሰበከውና የተረጋገጠው በመስቀል ላይ በተደረገው የክርስቶስ ቤዛነት ነው፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያው ‹‹ጥልን በመስቀሉ ገድሎ ርቃችሁ ለነበራችሁ ሰላምና የምሥራችን ሰበከ›› ያለው….
መስቀል
መስቀል ነገር በመጀመሪያ የተገለጸው በመላእክት ዓለም ነበር፡፡
መስቀል
መስቀል የፍቅር ተምሳሌት
የዓለም ሰላምና አንድነት
ጠላት በቀራንዮ የተሸነፈበት
የሰው ልጅ ድኅነት
መስቀል
መስቀል የሰላም መሠረት ነው
መስቀል የሰላም መሠረት፤ ሰላምም የመስቀል ፍሬ ነው፡፡ በግእዝ ሰላም የሚለው ቃል ትርጉም ‹‹ፍጹም ጤና፣ ዕረፍት፣ እርቅ፣ ሰላምታ፣ የቡራኬና የምርቃት ቃል፣ ሰው ሲገናኝና ሲለያይ የሚናገረው›› ነው፡፡ መስቀልና ሰላም አንዱ የአንዱ መሠረት አንዱ የአንዱ ፍሬ ሆነው የተሳሰሩትም በዚህ ምክንያት ነው፡፡
ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነት
ክርስትና የሕይወት መንገድ ነው፡፡ መንገዱም ደግሞ ወደ ዘላዓለማዊ ክብር የሚያደርስ የሕይወት የድኅነትና የቅድስና መንገድ ነው፡፡ ክርስቲያን ለመሆን በ፵ እና በ፹ ቀን በመጠመቅ የሥላሴ ልጅነትን ማግኘት የቤተ ክርስቲያን አባል መሆን ያስፈልጋል፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ዳግመኛ መወለድ ማለትም ነው፡፡
ዘመነ ፍሬ
ከመስከረም ፱ እስከ ፲፭ ያሉት ዕለታት ዘመነ ፍሬ ተብለው ይጠራሉ፡፡ በእነዚህ ወቅት የሚዘመረው መዝሙርም ሆነ የሚነበቡት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እግዚአብሔር ለምድር ፍሬንና ዘርን የሚሰጥ የዓለም መጋቢ መሆኑን የሚያስገነዝቡ ናቸው፡፡