መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
‹‹ኢየሱስን በማመን የሚጸኑት ቅዱሳን ትዕግሥታቸው ይህ ነው›› (ራእ. ፲፬፥፲፪)
በዮሐንስ ራእይ ላይ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ‹‹ኢየሱስን በማመን የሚጸኑት ቅዱሳን ትዕግሥታቸው ይህ ነው›› በማለት የተናገረው ኃይለ ቃል የመጨረሻውን ዘመን አስጨናቂ እና ፈታኝ መሆን እንዲሁም ክርስቲያኖች ይህን ተረድተው በትዕግሥት መጽናት እንደሚገባቸው ለማስረዳት ነው፡፡ በዚሁ ምዕራፍ ቁጥር ፲፩ ላይ ለአውሬውና ለምስሉ የሚሰግዱ፣ የስሙንም ምልክት የሚጽፉ ሁሉ ቀንና ሌሊት ዕረፍት እንደሌላቸው፣ ሕዝብንና አሕዛብን ስለሚፈትነው፣ በመጨረሻ ዘመን ስለሚነሣው አውሬ እና በእርሱም ምክንያት ብዙዎች ወደ ዘለዓለማዊ እሳት እንደሚጣሉም ይገልጻል፡፡ (ራእ. ፲፬፥፲፪)
ዐቢይ ጾም
ዐቢይ ማለት ታላቅ የከበረ ማለት ሲሆን ዐቢይ ጾም ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ በገዳመ ቆሮንቶስ ዐርባ መዓልትና ዐርባ ሌሊት ከቆመ ሳያርፍ ከዘረጋ ሳያጥፍ በትኅርምት የጾመው ታላቅ ጾም ነው፡፡ በተለይም የዲያብሎስን ሦስቱን ፈተናዎች ውድቅ ያደረገበት፤ በፍቅረ ንዋይ የመጣውን በጸሊዐ ንዋይ በትዕቢት የመጣውን በትሕትና በስስት የመጣውን በቸርነት ድል ያደረገበትም ነው፡፡ (ማቴ. ፬፥፩)
‹‹ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ›› (ሚል ፫፥፯)
የሰው ልጆችን ጥፋት የማይወደው ፈጣሪያችን እግዚአብሔር በንስሓ እንድንመለስ ይሻል፤ ‹‹ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ›› ብሎም ዘወትር ወደ እርሱ ይጠራናል፡፡ (ሚል ፫፥፯)
‹‹በወንድማማችነትም ፍቅርን ጨምሩ›› (፪ ጴጥ. ፩፥፯)
በክርስቲያናዊ ሕይወት ውስጥ ፍቅር ልባዊ መዋደድ ነው፤ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ፍቅር ሲገልጽ እንዲህ ብሏል፤ ‹‹ፍቅር ያስታግሣል፤ ፍቅር ያስተሳዝናል፤ ፍቅር አያቀናናም፤ ፍቅር አያስመካም፤ ፍቅር ልቡናን አያስታብይም፡፡ ብቻዬን ይድላኝ አያሰኝም፤ አያበሳጭም፤ ክፉ ነገርንም አያሳስብም፡፡ ጽድቅን በመሥራት ደስ ያሰኛል እንጂ፥ ግፍን በመሥራት ደስ አያሰኝም፡፡ በሁሉ ያቻችላል፤ በሁሉ ያስተማምናል፤ በሁሉም ተስፋ ያስደርጋል፥ በሁሉም ያስታግሣል፤ ፍቅር ለዘወትር አይጥልም፡፡›› (፩ ቆሮ. ፲፫፥፬-፰)
‹‹አቤቱ፥ እንደ አዘዝህ ዛሬ ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ›› (ሉቃ.፪፥፳፱)
ቅዱስ ስምዖን ይህን ቃል የተናገረው በ፭፻ ዓመቱ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መወለድ በክንዱ ታቅፎ ከመሰከረ በኋላ ከፈጣሪው እግዚአብሔር ዘንድ መኖርንም ተመኝቶ በተማጸነበት ጊዜ ነው፡፡ ይህም የሆነው እንዲህ ነበር፤ …
የነነዌ ጾም
እግዚአብሔር አምላካችን ወዶ እና ፈቅዶ ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ለሆነው የነነዌ ጾም አድርሶናል፡፡ ሦስት ቀናት የሚጾመው ይህ ጾም የነነዌን ሕዝብ ከጥፋት መመለስ፣ የእግዚአብሔርን ምሕረት እንዲሁም የነቢዩ ዮናስን የዋህነት ያስረዳናል፡፡
ስእለት
ስእለት ማለት ልመና፣ ምልጃ፣ ጸሎት፣ ጥየቃ እንደሆነ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመጽሐፈ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት ሐዲስ ገልጸዋል፡፡ ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች ስእለት ይሳላሉ፡፡ ለምሳሌ ‹‹እግዚአብሔር የልቤን ጭንቀት ቢፈጽምልኝ እንዲህ አደርግለታለሁ፡፡ እመቤቴ ማርያም ስእለቴን ወይንም ልመናዬን ብትሰማኝ ለቤተ ክርስቲያን እንዲውል ጃን ጥላ አስገባለሁ›› ብለው ይሳለሉ፤ ወይንም አቅማቸው የፈቀደውን ነገር እንደሚሰጡ ቃል ይገባሉ፡፡ ስእለታቸውም ሲደርስ ‹‹እመቤታችን እንዲህ አድርጋልኛለች›› ብለው ለክብሯ መገለጫ ድባብ ወይንም የተሳሉትን ነገር ለቤተ ክርስቲያን ይሰጣሉ፡፡(ገጽ ፰፻፵፪)
ዶክተር ብርሃኑ ተሾመ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ!
ዶክተር ብርሃኑ ተሾመ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ፵፩ ዓመቱ ጥር ፳፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞተ ተለይተዋል፡፡ ሥርዓተ ቀብራቸውም በደብረ ምጥማቃት ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም እና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል የካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም ተፈጽሟል፡፡
‹‹አሁንስ ተስፋዬ ማነው? እግዚአብሔር አይደለምን?›› (መዝ.፴፰፥፯)
በእግዚአብሔር ተስፋ መኖር በእርሱ ላይ ሙሉ እምነት እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ እግዚአብሔር ከጎናችን ሲሆንም እያንዳንዳችን ከምናስበው ዳርቻ መድረስ እንችላለን፡፡ ስለዚህ ተስፋችን የሚወሰነው በአምላካችን ላይ ባለን የእምነት ጥንካሬ ነው፡፡ ተስፋ በሕይወታችን ውስጥ ወደፊታችን የምንራመድበት መወጣጫ ድልድይ፣ የኑሮአችን መሠረት እንዲሁም የደስታችን መጀመሪያ ነው፤ በተስፋ ኖረን ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት እንሸጋገራለንና፡፡
‹‹ከአነጋገርህ የተነሣ ትጸድቃለህ፤ ከአነጋገርህ የተነሣ በቃልህ ይፈረድብሃልና›› (ማቴ. ፲፪፥፴፯)
በአንደበታችን የምንናገረው ነገር መልካም ሲሆን ጽድቅ ሆኖ እንደሚቆጠርልን ሁሉ መጥፎ ከሆነ ደግሞ ኃአጢት ይሆንና በእግዚአብሔር ፊት ተጠያቂ ያደርገናል፡፡ ኃጢአት በአብዛኛው ከንግግር የሚመነጭ ነው፡፡ በማቴዎስ ወንጌል እንደተጻፈው ‹‹ከአነጋገርህ የተነሣ ትጸድቃለህ፤ ከአነጋገረህ የተነሣ በቃልህ ይፈረድብሃልና።›› ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተራራው ስብከት ውስጥ እንዲህ ሲል ተናግሯል፡፡ ‹‹በወንድሙ ላይ በከንቱ የሚቈጣ ሁሉ እርሱ ይፈረድበታል፤ ወንድሙንም ጨርቅ ለባሽ የሚለው በአደባባይ ይፈረድበታል፡፡›› (ማቴ. ፲፪፥፴፯፣፭፥፳፪)