መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
ዕለተ ዓርብ በሰሙነ ሕማማት
ዕለተ ዓርብ አዳምን ከሰይጣን ባርነት ነፃ ለማውጣትና የእርሱን የበደል ዕዳ ለመክፈል አምላካችን መከራ መስቀሉን የተሸከመበት ዕለት፣ የኀዘን ዕለት፣ የድኅነትም ዕለት ነው፡፡ ዓርብ ማለት ዐረበ ገባ (ተካተተ) ካለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጕሙም መካተቻ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ፍጥረቱን ከእሑድ ጀምሮ በስድስተኛው ቀን ዓርብ አዳምን በመፍጠር ሥራውን ሁሉ አጠናቋልና (አካቷልና)፡፡ በኋላም በኦሪት ሕዝበ እስራኤል ከሰማይ የሚወርድላቸውን መና በሙሴ ትእዛዝ መሠረት ዓርብ ዕለት የቅዳሜን ጨምረው (ቅዳሜ ሰንበት ስለሆነ እህል መሰብሰብ ስለማይገባ) አካተው ይሰበስቡ ነበር፡፡ (ዘፀ.፲፮፥፬)
ሰሙነ ሕማማት
በዚህ ሳምንት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጅ በሙሉ ያደረገውን ትድግና ቅዱሳት መጻሕፍት በተለይም ግብረ ሕማማት የተባለው የቤተ ክርስቲያናችን መጽሐፍ ነገረ ሕማማቱን መከራ መስቀሉን በሰፊው ይናገርለታል፡፡ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችንም መድኃኒታችን ክርስቶስ አንዳች በደል ሳይኖርበት በሰውነቱ የደረሰበትን ሕማሙንና መከራውን ሞቱንም እያሰብን ይህንን የዐቢይ ጾምን መጨረሻ ወቅት ወይም ስምንተኛውን ሳምንት በካህናቱ መሪነት ሁላችን ምእመናን በተረጋጋ ኅሊና አብዝተን በመጾም፣ በመጸለይና በመስገድ እንድናከብር ሥርዓትን ሠርታልናለች፡፡ ለዚህም ነው ዛሬ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ሁሉ ይህንን የጌታን የሕማማት ሰሙን ከተድላ ከደስታ በመራቅ ነገረ መስቀሉን እያሰቡ በኀዘንና በልቅሶ ሆነው የሚያሳልፉት፡፡
ሆሣዕና በአርያም
ሆሣዕና በአርያም . . . ሆሣዕና በአርያም
ለዳዊት ልጅ መድኃኔ ዓለም
በጌታ ስም የሚመጣ
ከምርኮ ሀገር ከባርነት የሚያወጣ
ኒቆዲሞስ
ኒቆዲሞስ ‹‹ቀናዕያንና ወግ አጥባቂዎች›› ከሚባሉት ፈሪሳውያን አለቆች አንዱ ነበር።…
‹‹አቤቱ፥ እስከ መቼ ፈጽመህ ትረሳኛለህ? እስከ መቼስ ፊትህን ከእኔ ትመልሳለህ?›› (መዝ. ፲፪፥፩)
አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር መኖራችንን የረሳን ይመስለናል፤ መከራ ውስጥ ሆነን እንዲሁም ሥቃያችን በዝቶ ልንቋቋመው ከምንችለው በላይ ሲሆንብን እግዚአብሔር እንደረሳን እናስባለን፡፡ ‹‹እግዚአብሔር በእውነት እኔን ያውቀኛል? ያስታውሰኛልን?›› ብለንም በመጠራጠር እራሳችንን እንጠይቃለን፤ ‹‹ዓለም ላይ ከሚኖረው ሕዝብም ለይቶ አያውቀኝም›› ወደ ማለትም እንደርሳለን፡፡ ሆኖም ግን በእግዚአብሔር ዘንድ እንኳን ሰው እንስሳም ይታወቃል፡፡ በሕይወታችን ውስጥም የሚያጋጥሙን ችግርና መከራ እንዲቀርፍልን ለእግዚአብሔር በመስጠት እንጸልይ፤ ከመከራም እንዲያሳርፈን እንማጸነው፡፡
‹‹ጌታውን ደስ ያሰኘ ታማኝና ቸር አገልጋይ ማነው?›› ቅዱስ ያሬድ
በዚህ ዘመን በየትኛውም መንገድ ቢሆን ታማኝነት የጠፋበት፣ እኛ ሰዎች በተለያዩ ነገሮች ራሳችንን በመተብተብ ከእግዚአብሔር ኅብረት ተለይተን ማገልገልን ለተወሰኑ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ብቻ የሰጠን ሁነናል፡፡ በዚህም በቤተክርስቲያንና በአማኞቿ ላይ ብዙ ችግሮች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆነናል፤ አሁንም ቢሆን ከተኛንበት መንቃት ያስፈልገናል፡፡
‹‹ተቈጡ፤ አትበድሉም›› (ኤፌ. ፬፥፳፮)
ቊጣ ተገቢ እንደሆነ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች በጻፈው መልእክቱ ‹‹ተቈጡ፤ አትበድሉም፤ ፀሐይ ሳይጠልቅም ቊጣችሁን አብርዱ›› በማለት ተናግሯል፡፡ ከሰዎች ጋር በሚኖረን ግንኙነት ውስጥ እውነት ሲጠፋ ወይንም ሐሰት ሲንሰራፋ ኃጢአትን በመንቀፍ መቈጣታችን ተገቢ ነው፡፡ ሰዎችን ከስሕተት እና ጥፋት ለመመለስ መቈጣት የተፈቀደ እንደሆነ በዚሁ እንረዳለን፡፡ ሆኖም ግን ከልክ ባለፈ ቊጣ የሰዎችን ስሜት በመጕዳት መበደል ኃጢአት ነው፡፡ ይህም ማለት ትክክል ያልሆነን ነገር ስንመለከትና ስንሰማ ወይንም ስሕተት ሲፈጸም አይተንና ሰምተን ብንቈጣ ተገቢ ሆኖ ሳለ የመቈጣታችን ስሜት ግን ለመፍትሔ እንጂ ለባሰ ጥፋት የሚዳርግ ከሆነ እንዲሁም የተቈጣንበት ነገር አግባብነት ከሌለው የማይገባ ቊጣ እንደሆነ መረዳት ይኖርብናል፤ የሚገባ ቊጣ ሲሆን ግን ትክክል መሆኑን በዚሁ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ (ኤፌ. ፬፥፳፮)
‹‹የዓለሙ ፍጻሜስ ምልክቱ ምንድነው?›› (ማቴ.፳፬፥፫)
በዓለም ፍጻሜ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጻድቃንን በቀኙ ኃጥአንን ደግሞ በግራው ለይቶ እንደየሥራችን ሊፈርድ ይመጣልና ምልክቶቹን እናውቅ ዘንድ በወንጌል ተጽፎልናል፡፡
‹‹እግዚአብሔር መልካም ነው፤ በመከራ ቀን መሸሸጊያ ነው›› (ናሆም ፩፥፯)
እግዚአብሔር አምላክ የሰዎችን ደኅነትን የሚሻ መልካም አባት በመሆኑ ልጆቹን ከመከራ ይሸሽጋል፡፡ በዘመነ ኦሪት እስራኤላውያን በግብፅ በባርነት ሲኖሩ ከመከራ ሠውሯቸዋል፤ ነፃ ሊያወጣቸውም ፈቅዶ ነቢዩ ሙሴን እንዲህ አለው፤ ‹‹እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከግብፃውያንም ተገዥነት አወጣችኋለሁ፥ ከባርነታችውም አድናችኋለሁ፤ በተዘረጋ ክንድ፤ በታላቅ ፍርድም እታደጋችኋለሁ፥ ለእኔም ሕዝብ እንድትሆኑ እቀበላችኋለሁ፥ አምላክም እሆናችኋለሁ፤ እኔም ከግብፃውያን ባርነት ያወጣኋችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ፡፡›› (ዘፀ. ፮፥፮-፯)
መፃጒዕ
በዘመነ ሥጋዌ በኢየሩሳሌም ውስጥ ይኖሩ የነበሩ በተለያየ ሕመም ይሠቃዩ የነበሩ ሰዎች ለመፈወስ የሚሰበሰቡባት ቤተ ሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፡፡ አምስትም መመላለሻ ነበራት፡፡ በዚያም ብዙ ድውያን ይተኛሉ፤ ከእነርሱም ውስጥ የታወሩ፣ አንካሾች፣ የሰለሉ፣ ልምሹ የሆኑ፣ በየእርከን እርከኖች ላይ ይተኙ ነበር፡፡ የእግዚአብሔር መልአክም ውኃውን ለመቀደስ በሚወርድ ጊዜ ድምፁ እስኪያስተጋባ ድረስ ውኃው ይናወጣል፡፡ ድውያኑም በዚያ ሥፍራ ተኝተው የውኃውን መናወጥ ይጠባበቃሉ፡፡ ምክንያቱም በዕለተ ሰንበት (ቀዳሚት) ውኃው ሲናወጥ ቀድሞ ወደ ውኃው የገባ አንድ ሰው ከደዌው ይፈወስ ነበርና፡፡…