መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
“የእግዚአብሔር ቤት” በሚል ርእስ የተሠራው የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት ፊልም ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጭ እንደሆነ ተገለጠ፡፡
የእግዚአብሔር ቤት /The abode of God/ በሚል ርእስ በጀርመናዊቷ ሚስስ ብሪጅት ማሪያ ማየር ተዘጋጅቶ በተወሰኑ ኢትዮጵያዉያን አርቲስቶች የተሠራው የኢየሱስ ክርስስቶስ የስቅለት ፊልም ከቤተ ክርስቲያን ቀኖና እና ትውፊት ውጭ እንደሆነ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሊቃውንት ጉባኤ ኅዳር 28 ቀን 2004 ዓ.ም የሰጠው መግለጫ ያስረዳል፡፡
ሚስስ ብሪጅት ማሪያ ማቶር የተባለችው ጀርመናዊት በኢትዮጵያውያን የኪነ ጥበብ ሰዎች እንዲሠራ ያዘጋጀችው ፊልም በይምርሐነ ክርስቶስ፣ አሸተን ማርያምና በጉንዳጉንዶ ገነተ ማርያም አብያተ ክርስቲያናት ተቀርጾ ለዕይታ እንዲቀርብ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ያቀረቡት ጥያቄ ጉዳዩ ሃይማኖታዊ ስለሆነና ቀረጻው የሚካሔድበት ቦታ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲየን አብያተ ክርስቲያናት ስለሆነ ጉዳዩ በቤተ ክርስቲያኗ እንዲታይና እንዲፈቀድ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡
ሐመረ ኖህ በቅዱስ ኤፍሬም ክፍል 4.
ኅዳር 28/2004 ዓ.ም ትርጉም በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ ቅዱስ ኤፍሬም በዚህ ቅኔያዊ ድርሰቱ ኖህ ከጥፋት ውኃ የዳነባትን መርከብ በቤተክርስቲያንና በመስቀሉ እንዲሁም በእምነት መስሎ ድንቅ በሆነ መልኩ አቅርቦት እንመለከታለን፡፡ የኖህ ተምሳሌትነት በዘመኑ ከነበሩት ሕዝቦች ጋር ሲነጻጸር እንዴት ታላቅ ነበር፤ ንጽሕናን እንደጥሩር ከለበሰው ኖህ ጋር በፍትሕ ሚዛን ሲመዘኑ እንደማይጠቅሙ እንደማይረቡ ሆነው ተቆጠሩ፤ ፈጽሞ የማይነጻጸሩ ነበሩና በጥፋት ውኃው […]
ቅድስት ድንግል ማርያም በቅዱስ ኤፍሬም ክፍል 3
ኅዳር 28/2004 ዓ.ም በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ በዚህ ክፍል ቅዱስ ኤፍሬም በቅድስት ድንግል ማርያም የተፈጸመውን የተዋሕዶ ምሥጢር በማድነቅና በማመስገን የጻፈውን የቅኔ ድርሰት እንመለከታለን፡፡ ጌታ ሆይ አንተን ምን ብሎ መጥራት እንዳለበት የሚያውቅ ሰው ማን ነው? ጌታ ሆይ እናትህን ድንግል ብለን እንጥራትን? እንዲያ ብለን እንዳንጠራት የአንተ እናት መሆኑዋ ምስክር ይሆንብናል፤ ጌታ ሆይ እናት እንበላትን? እንዲህ እንዳንል ወንድ […]
በግቢ ጉባኤያት ለሚሰጥ የአብነት ትምህርት አገልግሎት ትኩረት እንስጥ
ኅዳር 28/2004 ዓ.ም.
የአብነት ትምህርት የቤተ ክርስቲያናችን አገልግሎትና የአገልግሎት ሥርዓት መሠረት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህ የአብነት ትምህርት የኢትዮጵያ የትምህርት ታሪክ መሠረትና አንድ አካል ሆኖ ቆይቷል፡፡ የዘመናዊ ትምህርት በሀገራችን መስፋፋቱን ተከትሎ ግን የአብነት ትምህርት ቤቶች ሚና ቤተ ክርስቲያን ለምትፈልገው አገልግሎት በሚያበረክተው ድርሻ ብቻ ተወስኖ እንዲቀር ሆኗል፡፡ ከዚያም አልፎ ቤተ ክርስቲያን የነበራትን የመተዳደሪያ ሀብት ንብረት ማጣቷ በአብነት ትምህርት ቤቶች ጥንካሬ ከዚያም አልፎ በህልውናቸው ላይ ፈተኝ ሁኔታዎች ጋርጧል፡፡
ሥጋ ለነባቢት ነፍስ እንድትታዘዝና የፈቲው ፆርም እንዲደክም- ጾም
በፍትሐ ነገሥት መንፈሳዊ አንቀጽ 15 እንደተገለጸው ቅዱሳን አባቶቻችን ሥጋ ለነባቢት ነፍስ እንድትታዘዝና የፈቲው ፆርም እንዲደክም የሚያደርግ የሰውን ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲገናኝ የለመነውም ልመና መልስ እንዲኖረው የሰይጣንን ፍላጻ ለመስበር የሚያስችል ኃይል ያለው መሣሪያ ጾም ነው ብለው ጽፈዋል፡፡
ቅርሶችን በተመለከተ ዐውደ ጥናት ተካሔደ
ኅዳር 22/2004 ዓ.ም
የማይዳሰሱ ባሕላዊ ቅርሶች አያያዝ /አተገባበር/ ስምምነት በሀገር አቀፍ ደረጃ /Implementation of the Intangible cultural Heritage convention at national level/ በሚል ርዕስ ዐውደ ጥናት ተካሔደ፡፡ ዐውደ ጥናቱ የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ከተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም /UNESCO/ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሲሆን፤ ከኅዳር 4-8/2004 ዓ.ም ድረስ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ለመካሔድ ችሏል፡፡ በዐውደ ጥናቱ ላይ የዩኒስኮ ተወካይ በሆኑት በፕሮፌሰር አማርሰዋር ጋላ እና በቅርስና ጥበቃ ባለስልጣን ባለሙያዎች ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
የፍትሕ ነፃነትን የሚያስከብር የመንፈሳዊ ፍርድ ቤቶች ማጠናከሪያ ሕግ በቅዱስ ሲኖዶስ ጸደቀ
ኅዳር 22/2004 ዓ.ም
የፍትሕ ነፃነትን የሚያስከብር የመንፈሳዊ ፍርድ ቤቶች ማጠናከሪያ ሕግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በሙሉ ድምጽ ማጽደቁ ተገለጸ፡፡
ሕጉ የጸደቀው የሲኖዶሱ ምልዓተ ጉባኤ ጥቅምት 23 ቀን 2004 ዓ.ም ባደረገው ዓመታዊ የምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ሲሆን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ፣ 30ኛውን ዓመታዊ አጠቃላይ ሰበካ ጉባኤ ሲከፍቱ በአስተላለፉት ቃለ በረከት “ውኃው ከአጠገባቸው እያለ ተጠምተው የሞቱ ብዙ ናቸው” ብለዋል፡፡ አያይዘውም የሕግ ምንጭ የሆነችው የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ፍትሕ ፍለጋ የዓለማዊውን ፍርድ ቤት ሲናፍቁና ሲያጨናንቁ ማየት ችግር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ መፍትሔውም የዳኝነት ነፃነትን የሚያስከብረውን የሕግ ረቂቅ ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ማቅረብና ማጽደቅ በመሆኑም ይህንኑ ማድረግ መቻሉም በማኅበረ ክርስቲያኑ ፍትሕን ለማስፈን የቆመ የመሠረት አለት ነው ብለዋል፡፡
በስልጤና ሀድያ፣ ጉራጌ፣ ከንባታ ሀገረ ስብከት በፖሊሶች የፈረሰው የጋራሬ ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን በአክራሪ ሙስሊሞች ፍርስራሹ ተቃጠለ፡፡
ኅዳር 21/2004 ዓ.ም
፠በቃጠሎው ወንጀል የስልጤ ቲትጎራ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የስልጢ 2ኛ ደረጃ ተማሪዎች ተሳትፍበውታል፡፡
፠የስልጢ አረጋውያን ሙስሊሞች ድርጊቱን ተቃውመዋል፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስልጤና ሀድያ፣ ጉራጌ፣ ከንባታ ሀገረ ስብከት በስልጤ ደብረ ስብሐት ቅድስት ማርያምና ቆቶ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ስር የተመሠረተው የጋራሬ ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ኅዳር 19 ቀን 2004 ዓ.ም ረፋድ ላይ በአክራሪ ሙስሊሞች ሙሉ ለሙሉ መቃጠሉን ለመረዳት ተችሏል፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና ታቦተ ጽዮን
ኅዳር 20/2004 ዓ.ም
እግዚአብሔር አምላክ ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ካወጣቸው በኋላ የአምልኮ ሥርዐታትን ይፈጽሙበት ዘንድ የምስክሩን ድንኳን፣ የቃል ኪዳኗ ታቦትንና ለአምልኮ ሥርዐቱ ማከናወኛ የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ ንዋያተ ቅድሳትን እንዲሠሩ በሙሴ በኩል ታዘው ነበር፡፡ ከቃል
ኪዳኗ ታቦት ውስጥም በእግዚአብሔር ጣት ዐሥርቱ ትእዛዛት የተጻፉበት የሕጉ ጽላት፣ አርባ ዓመት ሙሉ እስራኤላውያን በሲና ምድረ በዳ የተመገቡትን መና የያዘች መሶበ-ወርቅ፣ አሮን ለክህነት አገልግሎት ስለመመረጡ ምስክር የሆነችው ለምልማና ፍሬ አፍርታ የተገኘችው የአሮን በትር ይገኙባታል፡፡(ዕብ.9፡4)
በስልጤና ሀድያ ጉራጌ ሀገረ ስብከት የጋራሬ ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን በወረዳው ፓሊስ አባላት እንዲፈርስ መደረጉ ተገለጠ፡፡
ኅዳር 19/2004 ዓ.ም
• ቤተ ክርስቲያኑ የፈረሰው እኩለ ሌሊት እንደሆነም ታውቋል፡፡
• የስልጢ 2ኛ ከፍተኛ ደረጃ ተማሪዎች በቤተ ክርስቲያኑ መፍረስ እንዲተባበሩ እየተቀሰቀሱ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስልጤና ሀድያ ሀገረ ስብከት በስልጤ የጋራሬ ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ኅዳር 15 ቀን 2004 ዓ.ም ዓርብ ለቅዳሜ አጥቢያ እኩለ ሌሊት ላይ በወረዳው የፓሊስ አባላት የመፍረስ አደጋ እንደተጣለበት ከክልሉ የደረሰን ማስረጃ አረጋገጠ፡፡
በስልጤ ዞን በስልጢ ወረዳ በቆቶ ባለሦ ቀበሌ በቆቶ መንደር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም የይዞታ ቦታው በሰነድ እንዲረጋገጥ የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ለደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ለግብርና ገጠር ልማት ቢሮ ለተፈጥሮ ሀብትና የገጠር መሬት አስተዳደር ዘርፍ ባቀረበው ጥያቄ አግባብነት ያለው የመንግሥት የሥልጣን አካል በቀን 15/04/2003 ዓ.ም የይዞታ ማረጋገጫ ሰነዱን ለደብሩ ሰበካ ጉባኤ መስጠቱን መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡