መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
ሰሙነ ሕማማት(ዘረቡዕ)
በመምህር ኃይለማርያም ላቀው
በቅዱስ ማቴዎስና በቅዱስ ማርቆስ አዘጋገብ መሠረት ሦስት ነገሮች በዕለተ ረቡዕ ተደርገዋል፤ እነርሱም የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. የካህናት አለቆች÷ የሕዝብ ሽማግሌዎችና ጸሐፍት ፈሪሳውያን በጌታችን ላይ ተማክረዋል፤
2. ጌታችን በስምዖን ዘለምጽ ቤት ሳለ አንዲት የተጸጸተች ሴት ሽቱ ቀብታዋለች፡፡
3. ከዳተኛው ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ለመስጠት ከጸሐፍት ፈሪሳውያንና ከካህናት አለቆች ዘንድ 30 ብር ተመዝኖለታል፡፡
ሰሙነ ሕማማት ( ዘሰሉስ)
ማክሰኞ
በዚህ ዕለት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱሱ ክርስቶስ ስለ ሥልጣኑ ተጠይቋል፡፡ ጠያቂዎቹ የካህናት አለቆችና የሕዝብ አለቆች ናቸው፡፡ ጥያቄውም በማን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን የሰጠህ ማነው? የሚል ነበር፡፡ የካህናት አለቆች ያቀረቡት ጥያቄ ነበር፡፡ ጌታችን ሰኞ ዕለት ሁለት ነገሮችን ማድረጉን ተያይዞ የተነሣ ጥያቄ ነው፡፡ ሰኞ ከቅጠል ብቻ በቀር ፍሬ ያላገኘባትን ዕፀ በለስ ረግሟል፤ በማስከተል ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ የሚሸጡትንና የሚለውጡትን አስወጥቷል፡፡ ማቴ.21:23-25፤ ማር.11:27፣ ሉቃ.20÷1-8፡፡ ከላይ እንደ ተገለጸው ጌታችን ሲያደርጋቸው የነበሩት ተአምራትና የኃይል ሥራዎች የካህናት አለቆችን ስላስቀናቸው ጌታችንን ከሮማ መንግሥት ባለ ሥልጣናት ጋር ለማጋጨት የቀየሱት ስልት ነው፡፡
ሰሙነ ሕማማት
ሚያዝያ 1/2004 ዓ.ም.
መምህር ኃይለ ማርያም ላቀው
ፍቅር የተከፈለ የመሥዋዕትነት ሥራ ስለ ተሠራበት፣ የሰው ልጆች ደኅንነት ስለ ተፈጸመበት፣ መድኀኔዓለም ስለ እኛ ቤዛ ሆኖ ለመስቀል ሞት ታዛዥ ሆኖ ነፍሱን ስለ ካሠልን “ቅዱስ ሳምንት” ተብሏል፡፡ በተጨማሪም “የመጨረሻ ሳምንት” ተብሎ ይጠራል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም በሙዓለ ሥጋዌው ለፈጸማቸው የቤዛነትና የአርአያነት ተግባራት ፍጻሜ በመሆኑ ነው፡፡
ሰሙነ ሕማማት(ለህጻናት)
ሚያዚያ 1/2004 ዓ.ም.
እንደምን ሰነበታችሁ ልጆች? ደህና ናችሁ? እንኳን ለሰሙነ ሕማማት በሰላም አደረሳችሁ፡፡ ልጆች ሰሙነ ሕማማት ምን ማለት እንደሆነ ታውቃላች? ሰሙነ ሕማማት ከትንሣኤ በፊት ያለውን ሳምንት ሲሆን በዚህ ሳምንት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን የሰው ልጆች ለማዳን ሲል የተቀበለውን መከራ ከሌላ ጊዜ በተለየ መልኩ የምናስብበት ሳምንት ነው፡፡ ጌታችን በዚህ ሳምንት ውስጥ ባሉት ቀናት ውስጥ የተለያዩ ተግባራት አከናውኗል፡፡ እስኪ ልጆች ቀናቱንና በቀናቱ ውስጥ የተፈጸሙትን ተግባራት በዝርዝር እንመልከት፡-
የቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያንን ዳግም ለማነጽ የገቢ ማሰባሰቢያ ተካሔደ
መጋቢት 28/2004 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
በቅርቡ በአክራሪ ሙስሊሞች ሙሉ ለሙሉ ወደተቃጠለው በስልጤና ሃዲያ፣ ጉራጌ ከንባታ ሀገረ ስብከት ጋራሬ ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን መጋቢት 23/2004 ዓ.ም. መንፈሳዊ ጉዞ ተካሔደ፡፡ የጉዞው ዓላማ በቃጠሎው ምክንያት የተጎዱትንና ተስፋ በመቁረጥ ላይ የሚገኙትን የአካባቢውን ምእመናንን በቃለ እግዚአብሔር ለማጽናናት ቤተ ክርስቲያኑን ዳግም ለማነጽ እንዲረዳ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ለማካሔድ ታስቦ የተዘጋጀ ነበር፡፡
ድንቅ ቀን /ለሕፃናት/
መጋቢት 28/2004 ዓ.ም.
በልያ አበበ
ልጆች የዕረፍት ጊዜያችሁ ወይም የጨዋታ ሰዓት ሲደርስ በጣም ትደሰታላችሁ አይደል? እኔና ዘመዶቼ ደግሞ ዓመቱን ሙሉ ሰዎችን በማገልገል እነርሱንና ዕቃዎቻቸው ከቦታ ቦታ ለማጓጓዝ ስንለፋ እና ስንደክም የምንኖር ቢሆንም በዓመቱ ውስጥ ግን ልክ እንደሰዎች እጅግ ተደስተንባቸው የምናሳለፋቸው በዓላት አሉ፡፡
አንደኛው በዓል የሁላችን ፈጣሪ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ነው ለዚያ ቀን እርሱ ቤተልሔም በሚገኝ የዘመዶቻችን ቤት /በሰዎች አጠራር በረት/ ውስጥ ሲወለድ አንደኛ በትሕትና በእንስሳት ቤት ለመወለድ በመምረጡ ሁለተኛ እጅግ ብርዳማ በነበረው የልደቱ ዕለት የእኛ ዘመዶች የሰው ልጆች እንኳን ያላደረጉትን በትንፋሻቸው እንዲሞቀው ስላደረጉ በጣም ደስተኞች ነን፡፡
ከ175 በላይ በገና ደርዳሪዎች ይመርቃሉ፡፡
መጋቢት 26/2004 ዓ.ም.
በእንዳለ ደጀኔ
በማኅበረ ቅዱሳን ልማት ተቋማት አስተዳደር የአቡነ ጎርጎርዮስ የትምህርትና ሥልጠና ማእከል ከ175 በላይ በገና ደርዳሪዎችን መጋቢት 29 ቀን 2004 ዓ.ም. እንደሚያስመርቅ አስታወቀ፡፡
የዐብይ ጾም ስብከት /ክፍል 7/
መጋቢት 26/2004ዓ.ም.
በአያሌው ዘኢየሱስ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤
ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ የከምባታ፣ ሀድያ፣ ጉራጌና ስልጢ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤በአዲስ አበባ የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የበላይ ኃላፊ፤ቀደም ሲል በዚሁ ደብር አስተዳዳሪ ሆነው ባገለገሉባቸው ዓመታት ውስጥ ለማጠቃለያ ከሰበኳቸው በርካታ የወንጌል ስብከቶች መካከል የተወሰደ፡፡/መጋቢት 21 ቀን 1985 ዓ.ም./
እውነት እውነት እልሃለሁ፡- ሰው ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ የእግዚአብሔርን መንግሥት አያይም፡፡ ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህንን የተናገረው ለኒቆዲሞስ ነው፡፡
‹‹ትእዛዝህ ከጠላቶቼ ይልቅ አስተዋይ አደረገኝ›› መዝ 118፥98 ፤ በእንተ ቅዱስነታቸው አቡነ ሲኖዳ
መጋቢት 25/2004 ዓ.ም.
በአያሌው ዘኢየሱስ
/ይህ ጽሑፍ ካይሮ በሚገኘው የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር አቶ ሜናርደስ “የግብጽ የሁለት ሺህ ዓመት ክርስትና” በሚል ርዕስ ካዘጋጁት መጽሐፍ የተወሰደ ሲሆን የጽሑፍን የአርትኦት ሥራ ያከናወኑት አባ አውጉስጢኖስ ሐና ናቸው፡፡ የዘመን አቆጣጠሩ እንደ አውሮፓውያን ቀመር ነው፡፡/
ሀገር ዕርቃኗን እንዳትቀር
መጋቢት 25/2004 ዓ.ም.
ከጥቂት ዓመታት በፊት በታተመ አንድ የተባበሩት መንግሥታት ጥናት፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2020 ሙሉ በሙሉ ደን አልባ አገር ትኾናለች፡፡ እንደ ጥናቱ ከ40 ዓመታት በፊት የሀገሪቱ 40 በመቶ መሬት በደን ተሸፍኖ ነበር፡፡ ጥናቱ በታተመበት ዓመት ግን ወደ 2.7 በመቶ አሽቆልቁሏል፡፡ ጥናቱ ማስረጃን በመጥቀስ እንዳስቀመጠው ቁጥሩ በሚያስደንቅ ሁኔታ እንዲህ ያሽቆለቆለው በሀገሪቱ 200,000 ሄክታር መሬት በልዩ ልዩ መንገድ ስለሚወድም ነው፡፡ የዚህን ጥናት ግኝት ሌሎች ጥናቶችም ይጋሩታል፡፡ ይህ መረጃ አስደንጋጭ ነው፡፡ በልምላሜና ልምላሜው በሚያመጣው በረከት ለሚኖር እንደኛ ዓይነት ሕዝብ ደግሞ ሁኔታው አስጨናቂ ነው፡፡