- (፩ኛ ቆሮ. ፩፥፳፫) -
"ወንሕነሰ ንሰብክ ክርስቶስሃ ዘተሰቅለ"
እኛስ የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን

- (ሉቃ ፩፥፳፰) -
"ተፈሥሒ ፍሥሕት ኦ ምልዕተ ጸጋ እግዚአብሔር ምስሌኪ "
መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ። ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት።

ቅዱሳን አባቶች






ሥራህን ሥራ
ጌታ ለእያንዳንዱ ሰው ሥራ ሰጥቶታል ያንን መራት የእሱ ፈንታ ነው። ቢቻለው እሱን ማገድ የዲያብሎስ ሥራ ነዉ።በእርግጥ ሥራውን እግዚአብሔር እንደሰጠህ ያህል ሰይጣን ሊያግድህ ይሞክራል። ሌላ ነገር በበለጠ ደስ የሚያሰኝ ሊያቀርብልህ ይጥራል። በዓለማዊ ተስፋዎች ያባብልሃል የሐሜት ጎርፍ ያስወርድብሃል። ደራሲያን ኦንዲጠይቁህ እጅግ
ስመ ጥሩ ሰዎችም በክፋ እንዲናገሩብህ ይጠቀምባቸዋል። ጲላጦስ፥ሄሮድስ፥ሐናንያ፥ቀያፋ ሁሉም በአንተ ላይ ያድማሉ . . . አንተ ግን በጸና ውሳኔ በማያወላውል ቅናት በመጨረሻ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈፀምኩ ሃይማኖቴንም ጠበቅሁ ለማለት እስክትችል ድረስ የሕይወትህን ዓላማ እና የተፈጠርክበትንም ግብ ተከተል።

አባ ጎርጎርዮስ ካልዕ
የሸዋ ሊቀ ጳጳስ ፩፱፫፪፡፩፱፰፪ ዓ.ም.
አዳዲስ ዜናዎች እና ክንውኖች
፭፻ ዓመታት ገደማ በእስራኤል ብዙ ገቢረ ተአምራትን ስታደርግ የነበረችዋ በሙሴ የተቀረጸች ታቦት በቀዳማዊ ምኒልክ በኩል ለኢትዮጵያ ተሰጠች።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ ኅዳር ፳፩ ቀን በታላቅ ክብር ታከብረዋለች፡፡ካህናቱም ከዋዜማው ጀምረው በከበሮና በጸናጽል ስብሐተ እግዚአብሔር ያደርሳሉ፡፡በጽዮን ፊት እንደ የመዓርጋቸው ቆመው ‹‹እግትዋ ለጽዮን ወህቀፍዋ፤ ጽዮንን ክበቧት፥ በዙሪያዋም ተመላለሱ›› እያሉ ይዘምራሉ፡፡
የእግዚአብሔር ሰዎች ትክክለኛና እውነተኛ ሰዎች በመሆናቸው የተናገሩት ሁሉ የሚፈጸም ነው፡፡ በአንደኛ ሳሙኤል መጽሐፍ ላይ እንዲህ የሚል ቃል አለ፤ ‹‹…እነሆ አንድ የእግዚአብሔር ሰው በዚህች ከተማ አለ፤ እርሱም የተከበረ ሰው ነው፤ የሚናገረውም ሁሉ በእውነት ይፈጸማል …፡፡›› (፩ኛሳሙ.፱፥፮)
ውድ የዚህ ጽሑፍ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? ዘመነ ክረምቱን/ዘመነ ጽጌን እግዚአብሔር ረድቶን ብዙ ተምረንበት አልፏል፡፡ከፊታችን ኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ ፳፰/፳፱ ድረስ ደግሞ ዘመነ ነቢያትን የምንዘክርበት፣ ‹‹ጾመ ነቢያት›› ብለን ከጾም ጋር አገናኝተን ስለ ነቢያትና ነቢይነት፣ እንዲሁም ስለ ትንቢት ዓላማና ምክንያቱ ቤተ ክርስቲያን ብዙ የምታስተምርበት ወቅት ነው፡፡
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ! መንፈሳዊ ሕይወት እንዴት ነው? በትምህርት ቤት፣ በሠፈር ውስጥ እንዲሁም በተለያየ ቦታ ስትገኙ በሥርዓት እና በአግባብ እንደምትኖሩ ተስፋችን እሙን ነው፤መልካም!!! ለዛሬ የምንነግራችሁ ስለ ቅዱሳን ነቢያት ነው፡፡
በቅድስና፣ በውዳሴ፣ በኅብረ ቀለም፣ በመላእክት ዝማሬ በደመቀው በዓለመ መላእክት ውስጥ ቅዱሳን መላእክት በነገድ ተከፍለው ይኖራሉ፡፡ እነርሱም የዘወትር ምግባራቸው እንዲያውም ምግባቸው ፈጣሪን ማመስገን ነው፡፡ ስፍር ቁጥር የሌላቸው መላእክቱም በሦስቱ የመላእክት ከተሞች ኢዮር፣ ራማ እና ኤረር በአላቃቸው ስር ሆነው ዘወትር አምላክን ያገለግላሉ፡፡ በኢዮር ከተማ ደግሞ የኃይላት አለቃ አድርጎ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልን…
እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን በዕለተ እሑድ ሲፈጥር በነገድ መቶ በአለቃ ዐሥር አድርጎ በሦስቱ ሰማያት አስፍሯቸዋል፡፡ከእነዚህ ቅዱሳን መላእክት መካከል ኪሩቤል ይገኙበታል፤ኪሩብ አራት አራት ገጽ ካላቸው ከአራቱ ጸወርተ መንበር አንዱ ሲሆን፣ ፍችው መሸከምን፣ መያዝን ይገልጣል፡፡
በከበረች በኅዳር ስድስት ቀን የምናስበው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከተወደደ ልጇ ከመድኃኒዓለም፣ ከአረጋዊው ዮሴፍ እና ሰሎሜ ጋር ከስደት መመለስ እንዲሁም በቁስቋም ተራራ መገኘት ታላቅ በዓል ነው፡፡
አሁን ኢትዮጵያውያ ስደተኛ መቀበል አትችልም ስደተኛ ሆናለችና፤ ሱላማጢስ ሆይ አሁን እነዚያ ደጋግ ሰዎች ለእንግዳ ማረፊያ አይሰጡም፤ እነርሱም ማረፊያ መጠለያ አጥተዋልና፤ አሁን የተራበን ለማብላት አቅም የላቸውም፤ እነርሱም ረኃብተኞች ናቸውና፡፡ እናታችን ሆይ ተመለሽ! ሰላማችን ሆይ ነይ! ወደ ዐሥራት ሀገርሽ ተመለሽ! ቃል ኪዳንሽንም አድሽ! የአዲስ ኪዳን ስደተኞች በኩር ሆይ ተመለሽ! መከራችን ያበቃ ዘንድ፣…
እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰጣቸው ትልልቅ ስጦታዎች መካከል ዋነኛው የንስሓ መንገድ ሲሆን የእግዚአብሔር ቸርነቱ በሰፊው የሚገለጥበት የሕይወት መንገድ ነው። ንስሓ ዘማዊውን ድንግል የምታደርግ ቅድስት መድኃኒት ነች።
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።

በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።

ወንህነሰ ንሰብክ ክርስቶስሃ ዘተሰቅለ፣ እኛስ የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን
