መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ደን ቃጠሎ መጥፋቱ ተገለጠ፡፡
መጋቢት 20/2004 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ተከስቶ የነበረው ቃጠሎ መጥፋቱን የገዳሙ አበምኔት አባ ኢሳይያስ ገለጹ፡፡ ገዳሙም ተጨማሪ ርዳታና ድጋፍ እንደሚያስፈልገው አሳስበዋል፡፡
በቅዱስ ያሬድ የዜማ አስተምህሮ ፤ የምዕራፍ ሚናና አጠቃቀም
«በእልቅና ካባ ፓስተር መቅደስ ገባ ?» መጽሐፍ ታተመ
መጋቢት 19/2004 ዓ.ም.
በስንሻው ወንድሙ
ከዓመታት በፊት ፓስተር እንደነበሩ በሚነገርላቸው ግለሰብ ተዘጋጅተው በጀርመን ሀገር ለታተሙት የቅሰጣ መጻሕፍት ምላሽ የሰጠ መጽሐፍ መታተሙ ታወቀ፡፡ ገዳሙ ደምሳሽ በተባሉትና በአሁኑ ወቅት በጀርመን ቪዝባደን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በተሾሙ ግለሰብ ተዘጋጅተው ለታተሙት ሦስት መጻሕፍት ምላሽ የሰጡት መምህር ኅሩይ ኤርምያስ የተባሉ በዚያው በጀርመን የሚኖሩ ሊቅ ሲኾኑ፤ የመጽሐፋቸው ርእስ «መጻሕፍትን መርምሩ በእልቅና ካባ ፓስተር መቅደስ ገባ ?» የሚል እንደኾነ ከቦታው የደረሰን ሪፖርት ያስረዳል፡፡ መጽሐፉ 219 ገጾች ያሉት ሲኾን አዘጋጁ በመጽሐፉ መግቢያ እንደገለጹት መልስ የሰጡባቸው መጻሕፍት “የመናፍቃን ሰፊ የቅሰጣ ማስፈጸሚያ ወጥመዶች አካል፤ በውጭ ሳይኾን በውስጥ ተጠምደው ምእመናንን በገዛ እናት ቤተ ክርስቲያናቸው አደባባይ የሚያጠምዱ ናቸው ” ብለዋል፡፡ አክለውም መልስ የሰጡባቸው መጻሕፍት «ቤተ ክርስቲያንን ይሳደባሉ፣ ይተቻሉ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ያንቋሽሻሉ» ካሉ በኋላ የእሳቸው መልስ የኑፋቄ መጻሕፍቱን ደራሲ ተደራሽ ያደረገ ቢመስልም ዋና «ዓላማው መላው ምእመናን ሃይማኖታቸውን እንዲጠብቁና የተሳሳተ ትምህርት ሰርጎ እንዳይገባ ማንቃትና ማዘጋጀት ነው» ብለዋል፡፡ በመጻሕፍቱ ይዘትና በአዘጋጁ ወቅታዊ አስተምሕሮ በመደናገር ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መፍትሔ እንድትሰጣቸው ከአካባቢው አስተዳደር ጀምሮ እስከ ሊቃውንት ጉባኤና ቅዱስ ሲኖዶስ ድረስ አቤት ሲሉ የቆዩት ምእመናን በመምህር ኅሩይ መጽሐፍ መጽናናታቸውንና መደሰታቸውን ከቦታው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ክርስቲያናዊ ሕይወት
መጋቢት 19/2004 ዓ.ም.
በዲ/ን ኅሩይ ባየ
“ለማኅበረ ቅዱሳን አማርኛ መካነ ድር ዝግጅት ክፍል፡፡ መንፈሳዊ ሰላምታዬ ይድረሳችሁ፡፡ እባካችሁ ወደ ክርስቲያናዊ ሕይወት የሚመልሰኝን ምክር ለግሱኝ?”
ውብ አንተ
የተከበርክ ወንድማችን ውብ አንተ ክርስቲያናዊ ሕይወትህ እንዲበረታ መንፈሳዊ ምክር ፈልገህ ስለጻፍክልን እናመሰግናለን፡፡ ክርስቲያናዊ ሕይወት ይህ ነው ወይም ያ ነው ብሎ ቁርጥ ያለ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ጊዜና ቦታ ይገድበናል፡፡
ወደ ክርስቲያናዊ ሕይወት የሚመልሰኝ ምክር እፈልጋለሁ የሚለውን ዐሳብህን ብቻ ነጥሎ ማየት አሁን ያለህበትን የሕይወት ደረጃ ብናውቀው ጥሩ ነበር፡፡ ሆኖም ጥምቀተ ክርስትናን ተቀብለህ በክርስቶስ ክርስቲያን እንደተባልክ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ሆኖም እንደ ክርስቲያን መኖር ያለብህን ሕይወት ስላልኖርክ በውስጥህ የሚወቅስህ ነገር አለ፡፡ ይህ ወቃሽ ኅሊና በልቡናህ ስለተሳለ እግዚአብሔርን አመስግነው፡፡ እንዲህ ዐይነቱ የሚጸጸት፣ የሚጨነቅ የሚተክዝ ልቡና ያለው ሰው የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ያልተለየው ነው፡፡ ሐዋርያው ይህን ሲመሰክር እንዲህ አለ “…መንፈስ ድካማችንን ያግዛል እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይናገር መቃተት ይማልድልናል፡፡ ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ አሳብ ምን እንደሆነ ያውቃል እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ይማልዳልና” ሮሜ.8፥26-27
በዝቋላ ገዳም ደን ላይ ለደረሰው የእሳት አደጋ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ፡፡
መጋቢት 18/2004 ዓ.ም.
በዲ/ን አብርሃም አንዳርጌ
• እሳቱ መጥፋቱ የተገለጠ ሲሆን የእሳት አደጋን ለመከላከል የሚያስችል ቋሚ ጥናትም ተጀምሯል፡፡
ቃጠሎውን ተከትሎ ከአካባቢው በአቅራቢያው ከሚገኙ ከተማዎች ምእመናን ወደ ቦታው በመሔድ እሳቱን ለማጥፋት ጥረት አድርገዋል፡፡ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በቦታው በመገኘት ቡራኬ ሰጥተው ምእመናን የሚያከናውኑትን ሥራ አበረታተዋል፡፡ እንዲሁም በማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ በቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም የተመራ ልዑክ ሰኞ ቃጠሎው እንደተሰማ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት በቦታው በመገኘት ጊዜያዊ የውኃ፣ የዳቦና የገንዘብ ድጋፍ ለገዳሙ እንዲደረግ በማስተባበር እሳቱን የማጥፋቱን ሥራ ለማከናወን ተችሏል፡፡
ጸሎት
መጋቢት 18/2004 ዓ.ም.
በመ/ር ምሥጢረ ሥላሴ ማናየ
ጸሎት ጸለየ፡- ለመነ፣ ጠየቀ አማለደ፣ ማለደ ካለው የግዕዝ ቃል የወጣ ቃል ነው፡፡ ጸሎት ማለት ጠቅለል አድርገን ስንመለከተው ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር እግዚአብሔርን ማመስገን መለመን፣ መጠየቅ፣ መማለድ፣ መማፀን ነው፡፡ “ጸሎት ብሂል ተናግሮ ምስለ እግዚአብሔር፡፡” አባታችን አዳምም ከመላእክት ተምሮ በየሰዓቱ ይጸልይ ያመሰግን ነበር፡፡ ዲያብሎስ በእባብ አድሮ ወደ አዳም በመጣ ጊዜ ጸሎት እያደረገ ስለነበር ዲያብሎስን ድል ነሥቶታል ሔዋንን ግን ሥራ ፈትታ እግሯን ዘርግታ ስለአገኛት ድል ነስቷታል፡፡
በቅዱስ ያሬድ የዜማ አስተምህሮ ላይ ያተኮረ መድረክ ሊዘጋጅ ነው፡፡
መጋቢት 17/2004 ዓ.ም.
በእንዳለ ደጀኔ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ጥናትና ምርምር አዘጋጅነት መጋቢት 29 ቀን 2004 ዓ.ም በቅዱስ ያሬድ የዜማ አስተምህሮ ላይ ያተኮረ የጥናት ጉባኤ ሊካሔድ ነው፡፡
በማኅበረ ቅዱሳን የጥናትና ምርምር ማእከል እንዳስታወቀው በዚህ የጥናት ጉባኤ የቅዱስ ያሬድ የዜማ አስተምህሮ ክፍል የሆነው የምዕራፍ ሚናና፣ አጠቃቀም በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ የሚያተኩር እንደሆነ ታውቋል፡፡
ገብርኄር /ለሕፃናት/
መጋቢት 14/2004 ዓ.ም.
በቴዎድሮስ እሸቱ
ደህና ሰነበታችሁ ልጆች? እንዴት ናችሁ? በጾሙ እየበረታችሁ ነው አይደል? ጎበዞች፡፡ ዛሬ ስድስተኛው ሳምንት ላይ ደርሰናል፡፡ ይህ ሳምንት ገብርኄር ይባላል፡፡ ገብርኄር ማለት ልጆች መልካም አገልጋይ ማለት ነው፡፡ በዚህ ሳምንት በቤተ ክርስቲያናችን ክርስቶስ ስለመልካም አገልጋይ ያስተማረው ትምህርት ይነገራል፡፡ ይህን የተመለከተ ምስጋናም ይቀርባል፡፡
አንድ ባለጸጋ አገልጋዮቹን ያስጠራቸውና ለአንኛው 5 መክሊት ለሁለተኛው 2 መክሊት ለሦስተኛው ደግሞ 1 መክሊት ወርቅ ይሰጣቸዋል፡፡ ከዚያም እኔ እስክመጣ በዚህ ወርቅ በመነገድ ተጠቀሙ ብሏቸው ወደሩቅ ሀገር ይሔዳል፡፡ ልጆች መክሊት የወርቅ መለኪያ /መስፈሪያ/ ነው፡፡
ሆሣዕና (የዐቢይ ጾም 8ኛ ሳምንት)
የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ) ወእንዘ ሰሙን በዓለ ፋሲካ ቀርቡ አርዳኢሁ ለአምላከ ጽድቅ ኀበ ደብረ ዘይት ሙራደ ዓቀብ ሀገረ እግዚአብሔር ወተቀበልዎ ሕዝብ ብዙኃን አዕሩግ ወሕፃናት ነሢኦሙ አዕፁቀ በቀልት እንዘ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ተፅዒኖ ዲበ ዕዋል ቦአ ሀገረ ኢየሩሳሌም በትፍሥሕት ወበሐሴት ይሁቦሙ ኃይለ ወሥልጣነ፡፡ ትርጉም: “በፋሲካ በዓል ሰሞን የእውነት አምላክ ደቀ መዛሙርት ወደ ደብረ ዘይት ቀረቡ፤ […]
የትንሣኤ 2 መዝሙርና ምንባባት
የትንሣኤ 2 መዝሙር (ከመጽሐፈ ዚቅ) ትትፌሣሕ ሰማይ ወትታኃሠይ ምድር ወይንፍሑ ቀርነ መሠረታተ ሕምዝ ወይጸውዑ አድባር ወአውግር ወኩሉ ዕፀወ ገዳም ወዮምሰ ዐባይ ፍሥሐ በሰማያት ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐፂባ በደመ ክርስቶስ፡፡ ትርጉም: ሰማይ ይደሰታል ምድርም ትደሰታለች የምድር መሠረቶችም ቀንደ መለከትን ይንፉ /ይደሰቱ/ ተራሮችና ኮረብቶችም /ነገሥታት መኳንንት/ ይጩኹ/ይደሰቱ/ የምድረ በዳ እንጨቶችም ይጩኹ ዛሬ በሰማያት ታላቅ ደስታ ሆነ ምድርም […]