መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
ማኅበረ ቅዱሳን የመኪና ስጦታ ተበረከተለት
ሰኔ 20 ቀን 2004 ዓ.ም. በእንዳለ ደጀኔ ማኅበረ ቅዱሳን የጀመረውን ዓለም አቀፍ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት አጠናክሮ መቀጠል እንዲችል የሚያግዘው የመኪና ስጦታ ተበረከተለት፡፡ መኪናውን ለማኅበሩ ያበረከቱት ዶ/ር አንተነህ ወርቁና ዶ/ር ሰላማዊት እጅጉ ሲሆኑ ያዘጋጁትን ስጦታ በዶ/ር ሰላማዊት ወላጅ አባት በአቶ እጅጉ ኤሬሳ አማካኝነት አበርክተዋል፡፡ የመኪናውን ቁልፍ የተረከቡት የማኅበረ ቅዱሳን ም/ሰብሳቢ አቶ ታደሰ አሰፋ ‹‹ማኅበራችን ማኅበረ ቅዱሳን […]
በዓለ ልደቱ ለዮሐንስ መጥምቅ
ሰኔ 15 ቀን 2004 ዓ.ም በዘሚካኤል አራንሺ
እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በዓለ ልደት አደረሳችሁ::
በዮሴፍ ወልደ ያዕቆብ ዘመን የነበረው ፈርኦንና የመጥምቁ ዮሐንስን አንገት ለዘፋኝ ወሮታ የሰጠው ሄሮድስ የሚያመሳስላቸው አንድ ዓይነት ተግባር ፈጽመዋል:: ይኽውም ሁለቱም ልደታቸውን ያከብሩ እንደነበር በመጽሐፍ ቅዱስ መጠቀሱ ነው:: /ዘፍ.40፥20 ፤ ማቴ.14፥6/:: ታሪካቸውን ስናጠና ደግሞ በርካታ መመሳሰል እንደነበራቸው እንገነዘባለን:: ሁለቱም ነገሥታት ናቸው:: ሁለቱም ንጹሐንን አስረዋል:: ሁለቱም ደም አፍሳሾች ነበሩ:: በልደት በዓላቸውም ነፍስ አጥፍተዋል:: በልደት በዓላቸው ነፍስ ያጠፉ ሰዎች ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ መጻፉ የልደት በዓል ማክበርን ስህተት አያደርገውም:: በጌታችን ልደት መቶ አርባ አራት ሺህ ሕጻናት በሄሮድስ ትእዛዝ ተገድለዋል:: የጌታችንን ልደት ግን እናከብራለን:: መግደል ኃጢአት መሆኑን እንመሰክርበት ካልሆነ በቀር ነፍስ በማጥፋት የሚከበር በዓል የለንም:: የፋሲካን በዓል በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ለማክበር እንገደዳለን እንጂ ዘፋኞች ድግስ ስለሚያዘጋጁበት ማክበሩ ቢቀር ቢባል ሞኝነት ነው:: ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን የቅዱሳንን ልደት በዓል ስታከብር የራሷ ሥርዓትና ባሕል የበዓላት መቁጠሪያ /ሊተርጂካል ካላንደር/ አላት:: የቱ መቼ መከበር እንዳለበትም ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ታስረዳለች:: ጥንታዊት ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን እንደመሆንዋም በርግጥኝነት ዕለታቱን ቆጥራ ትናገራለች:: በነቢይ የአዋጅ ነጋሪ ቃል ተብሎ የተነገረለት የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስን የልደት በዓል የምታከብረው በሰኔ ሠላሳ ቀን ነው::
የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ 397 ደቀ መዛሙርትን አስመረቀ
በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በቀን በማታና በርቀት ትምህርት ያስተማራቸውን ደቀመዛሙርት እሑድ ሰኔ 10 ቀን 2004 ዓ.ም ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት አስመረቀ፡፡ ኮሌጁ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሥር ሆኖ ከተቋቋመበት ከ1953 ዓ.ም ጀምሮ ለቅድስት ቤተክስቲያንና ለሀገራችን ለኢትዮጵያ ከፍተኛ አገልግሎት ያበረከቱ ደቀመዛሙርትን አሰልጥኖ ማውጣቱን የኮሌጁ ምክትል ዲን ዶክተር አባ […]
ሦስት አራተኛው መሬት
በመንበረ ፓትርያርክ አካባቢ ራሳቸውን “ጉባኤ አርድዕት” ብለው የሰየሙ ቡድኖች እየተፈጠሩ መሆናቸው ተገለፀ፡፡
ሰኔ 09 ቀን 2004 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ባለፉት ረጅም ዓመታት በርካታ ፈተናዎችን አልፋ የተጓዘች መሆኗ ይታወቃል፡፡ በተለይም ራሳቸውን ተሐድሶ ብለው የሰየሙ ቡድኖች ተመሳስለው ውስጧ በመግባት ውስጥ ለውስጥ ሲያደሟት ቆይተዋል፡፡ የእነዚህ ድብቅ ቡድኖች አካሄድ ለብዙ ጠንካራ ኦርቶዶክሳውያን ግልፅ የነበረ በመሆኑ ላለፉት ተከታታይ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤያት ማንነታቸው ተገልጾ ውግዘት የተላለፈባቸውና በሕግ የሚጠየቁትም በሕግ እንዲጠየቁ መወሰኑ […]
ዝክረ አቡነ ጎርጎርዮስ ሊካሄድ ነው
ሰኔ 09 ቀን 2004 ዓ.ም
በእንዳለ ደምስስ
የማኅበረ ቅዱሳን ጥናትና ምርምር ማእከል የማኅበሩን 20ኛ ዓመት ምሥረታ በዓል ምክንያት በማድረግ “ዝክረ አቡነ ጎርጎርዮስ” በሚል ርእስ የጥናትና የውይይት መድረክ ሰኔ 16 ቀን 2004 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም አዲሱ አዳራሽ አዘጋጅቷል፡፡
የጥናትና ምርምር ማእከሉ ም/ዳይሬክተር አቶ ሰይፉ አበበ መርሐ ግብሩን አስመልክቶ እንደገለጹት “የጥናት መድረኩ ዋና ዓላማ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በሕይወት ዘመናቸው ለቤተ ክርስቲያን ያበረከቱትን አገልግሎት፣ የሕይወት ልምዳቸውን፣ ወጣቱን ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በአንድ ዓላማ ለማሰለፍ ያደረጉትን ተጋድሎ እንዲሁም ለቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ እድገት የነበራቸውን ርዕይ የሚዘክር ይሆናል” ብለዋል፡፡
ቤተ መጻሕፍቱ የመጻሕፍትና ቁሳቁስ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር አዘጋጀ፡፡
ሰኔ 04 ቀን 2004 ዓ.ም
በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖአምላክ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የማኅበረ ቅዱሳን ቤተ መጻሕፍት እየሰጠ ያለውን አገልግሎት አጠናክሮ ለመቀጠል ይረዳው ዘንድ የመጻሐፍትና ቁሳቁስ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር አዘጋጀ፡፡
በማኅበረ ቅዱሳን ጥናትና ምርምር ማዕከል ሥር የሚገኘው ቤተመጻሕፍት ፡-“ስትመጣ …በርኖሱንና መጻሕፍቱን ይልቁንም በብራና የተጻፉትን አምጣልኝ” (2ኛ ጢሞ.4÷13) በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው በዚሁ የመጻሐፍትና ቁሳቁስ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር፡-
• ሃይማኖታዊ፣ ታሪካዊ፣ ምክርና ትምህርት የሚሰጡ መጻሕፍት፣ መዛግብት፣ መጽሔቶችና ጋዜጦችን፣ የአስኳላ (አካዳሚካል) መጻሕፍት፣
• ጥናታዊ ጹሑፎችን እንዲሁም
• ቤተመጻሕፍቱን ለማደራጀት የሚያግዙ ቁሳቁሶችን በመስጠት ምእመናን የበኩላቸውን እገዛ እንዲያበረክቱ ጠይቋል፡፡
ኢንኅድግ ማኅበረነ
የማኅበሩ 20ኛ አመት ምሥረታ ተከበረ
ግንቦት 28 ቀን 2004 ዓ.ም. በእንዳለ ደምስስ የማኅበረ ቅዱሳን 20ኛ አመት የምሥረታ በኣል በጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ግንቦት 26 ቀን 2004 ዓ.ም. ተከበረ፡፡ ከረፋዱ 4፡ 00 ስኣት ጀምሮ የተካሔደው መርሐ ግብር በብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ ፤ የኢሉባቦርና ጋምቤላ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ መሪነት ጸሎተ ወንጌል በማድረስ ተከፍቷል፡፡ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል የምዕራብ ሐረርጌ […]
አገር አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ እየተካሔደ ነው፡፡
ግንቦት 25 ቀን 2004 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ አስተባባሪነት አገር አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት መሥራች ጉባኤ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ እየተካሔደ ነው፡፡