መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
2ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጥናት መጽሔት ተመረቀ
ጥቅምት 8 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
በማኅበረ ቅዱሳን የጥናትና ምርምር ማእከል የተዘጋጀው 2ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጥናት መጽሔት/Journal/ ጥቅምት 3 ቀን 2004 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል ተመረቀ፡፡ በጥናት መጽሔቱ የምረቃ መርሐ ግብር ላይ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ የሰቲት ዑመራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ በማኅበረ ቅዱሳን የጥናትና ምርምር ማእከል አማካሪ ቦርድ ሰብሳቢ፤ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የሰሜን ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ የጥናት መጽሔቱን በማዘጋጀት የተሳተፉ ምሁራን፤ ጥሪ የተደረገላቸው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ምሁራን የተገኙ ሲሆን በብፁዕ አቡነ ሉቃስ ቡራኬ በጸሎት ተከፍቷል፡፡
ማኅበሩ በሬድዮ ማሰራጫው ላይ የአየር ሞገድ ለውጥ አደረገ፡፡
ጥቅምት 8 ቀን 2005 ዓ.ም. በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ በማኅበረ ቅዱሳን ኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ የሬድዮና ቴሌቪዥን ዝግጅት ክፍል ዘወትር አርብ ከምሽቱ 3፡30 እስከ 4፡30 ያሰራጭ የነበረውን ትምህርታዊ የሬድዮ ዝግጅት የአየር ሞገድ ለውጥ በማድረግ በ19 ሜትር ባንድ 15335 ኪሎ ኸርዝ አጭር ሞገድ አማካኝነት በተሻለ ጥራት ከጥቅምት 9/2005 ዓ.ም. ጀምሮ ማስደመጥ እንደሚጀምር በማኅበረ ቅዱሳን የሬድዮና ቴሌቭዥን ፕሮግራም […]
ከሰባት ሺህ በላይ በሌላ እምነት የነበሩ ሰዎች ተጠመቁ
ጥቅምት 8 ቀን 2005 ዓ.ም. በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ባሳለፍነው የ2004 ዓ.ም. ቁጥራቸው ሰባት ሺህ አንድ መቶ አርባ አንድ ሰዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ሃይማኖት በመቀበል መጠመቃቸውን የሀገረ ስብከቱ ሪፓርት አመለከተ፡፡ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ትጉሀን ወንድወሰን ገ/ሥላሌ ለ31ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ባቀረቡት ሪፓርት የሕግ […]
የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የከሰዓት በኋላ ውሎ
ጥቅምት 6 ቀን 2005 ዓ.ም. በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ 31ኛው የመንበረ ፓትርያርክ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ከዛሬው የከሰዓት በኋላ መርሐ ግብሩ ላይ የትግራይ ማእከላዊ ዞን፣ /የአክሱም/፣ የሲዳሞ፣ የሰሜን ጎንደር፣ የምሥራቅ ሐረርጌ፣ የጅማ ዞን፣ የመቀሌ ዞን፣ የኢሊባቡር፣ የድሬዳዋ፣ የጋሞ ጎፋ፣ የሰሜን ወሎ፣ የባሌ፣ የደቡብ ጎንደር የምሥራቅ ወለጋ፣ የአርሲ፣ የትግራይ ምሥራቅ ዞን /የአዲግራት/፣ አህጉረ ስብከቶች የበጀት ዓመቱን ሪፓርታቸውን […]
ቤተ ክርስቲያንን ጠብቋት
ጥቅምት 6 ቀን 2005 ዓ.ም.
አባ ዘሚካኤል
ቅድሚያ ለቤተ ክርስቲያን እንቁም! ምን እንደምትልም እንጠብቃት (እንስማት)!
“ወይእዜኒ ዕቀቡ ርእሰክሙ ዘሎቱ ሤመክሙ መንፈስ ቅዱስ ጳጳሳተ ከመ ትርአዩ ቤተ ክርስቲያኑ ለክርስቶስ እንተ አጥረያ በደሙ፤ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቋት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ” (የሐዋ.20፥28)፡፡
ፓትርያርክ ለመሾም:-
የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ 31ኛ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ጥቅምት 6 ቀን 2005 ዓ.ም. ጧት 3 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጸሎት ተከፈተ፡፡
ጥቅምት 6 ቀን 2005 ዓ.ም.
በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ
ጉባኤው ከዛሬ ጥቅምት 6 ቀን ጀምሮ እስከ ቅዳሜ ጥቅምት 11 ቀን ድረስ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ አማካኝነት አምስት አባላት ያሉበት አርቃቂ ኮሚቴ የተሰየመ ሲሆን፤ ይህንኑ ተከትሎ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዐቃቢ መንበረ ፓትርያርክ የጉባኤው መክፈቻ ቃለ ቡራኬ ሰጥተዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በዚሁ ቃለ ቡራኬያቸው “በዚህ ጉባኤ የታደማችሁ አባቶቼ ወንድሞቼ እንኳን ለዚህ ቀን አደረሳችሁ፡፡” ካሉ በኋላ “ሐዋርያዊት የሆነች የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በቀኖናዋ ቅዱሳን ያሰኘቻቸው ልጆቿ አያሌ ናቸው፡፡ ቅድስናናን የሚያሰጠው የቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ጠብቀን በቤተ ክርስቲያናችን ሊሠራ የሚገባውን ወስነን እንሠራለን” ብለዋል፡፡
የመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ዓመታዊ ጉባኤውን አካሄደ
ጥቅምት 6 ቀን 2005 ዓ.ም.
በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ
የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ዓመታዊ ጉባኤውን ቅዳሜ ጥቅምት 3 ቀን 2005 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው ሀርመኒ ሆቴል አካሂዷል፡፡ በጉባኤው ላይ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል የቅዱስ ሲኖዶስ አባልና የሲዳማ ጌዲኦ ቡርጂና አማሮ ልዩ ልዩ ወረዳዎች ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም ዶክተር አባ ኀይለ ማርያም መልሴ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዲን ጨምሮ ከአብያተ ክርስቲያናት የተወከሉና የማኅበሩ አባላት ተገኝተዋል፡፡
በአባቶች መካከል የተጀመረው የዕርቀ ሰላሙ ውይይት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠየቀ
ጥቅምት 2 ቀን 2005 ዓ.ም.
በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ
የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራርና የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤያት መስከረም 30 ቀን 2005 ዓ.ም. በጋራ ባካሄዱት ስብሰባ በአስተዳደርና በተወሰኑ የቀኖና ቤተ ክርስቲያን አተረጓጎም ልዩነት ምክንያት ለሁለት አሠርት ዓመታት ተለያይተው በቆዩ አባቶች መካከል የተጀመረው የዕርቀ ሰላም ውይይት እስከ መጨረሻው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ “የስብሰባው ዋነኛ አጀንዳ በአገር ውስጥና በውጪ አገር በሚገኙ አባቶች መካከል የተጀመረው ውይይት ከሁሉም ጉዳዮች በፊት ቅድሚያ ተሰጥቶት እንዲሠራና እንዲፈጸም የማኅበሩ ፍላጎት መሆኑን ለማስታወቅና እንደ ጥያቄም ለማቅረብ ነው፡፡” በማለት መስከረም 30 ቀን 2005 ዓ.ም. ስለተካሄደው ስብሰባ መግለጫ የሰጡት የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ ዲ/ን ሙሉጌታ ኀይለ ማርያም ናቸው፡፡
እነሆ ክረምት አለፈ
ጥቅምት 1 ቀን 2005 ዓ.ም.
በመ/ር ምሥጢረ ሥላሴ ማናየ
“እነሆ ክረምት አለፈ ዝናሙም አልፎ ሄደ አበባው በምድር ላይ ታየ የመከር ጊዜ ደረሰ የቁርዬውም ድምጽ ተሰማ በለሱ ጎመራ ወይኖቹም አበቡ” መኀ.2፥11-13
ከዚህ ቀድሞ እንደተመለከትነው ክረምት ወርኀ ማይ/ውኃ/ ወርኀ ልምላሜ ወንዞች የሚሞሉበት ደመናና ጉም የሚሳብበት ሰማይ በደመና ተሸፍኖ የእግዚአብሔርን ጥበብ የሚያስተምርበት በመብረቅ በነጎድጓድ ድምጽ ታጅቦ ኀይለ እግዚአብሔርን የሚያስረዳበት መሆኑን ተመልክተን ነበር፡፡ አሁን ግን መግቦቱን ጨርሶ እነሆ ክረምት አለፈ ጊዜውንም በክረምት ከሚታየው ልምላሜ ቀጥሎ ለሚመጡ ለአበባና ለፍሬ አስረክቦ ከልምላሜ ቀጥለው የምናያቸው አበባና ፍሬ የሚያስተምሩት ቁም ነገር አለና፡፡
የቃለ ዓዋዲው ማሻሻያ ረቂቅ ይመከርበት!
መስከረም 30 ቀን 2005
ሰበካ ጉባኤ በካህናትና በምእመናን ኅብረት ላይ የቆመ መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደራዊና መዋቅራዊ ሥርዐት ነው፡፡ ከመንበረ ፓትርያርክ እስከ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ባሉት መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ በየደረጃው አመራር ይሰጣል፣
ዕቅድ ያወጣል፣ ውሳኔ ያሳልፋል፡፡ ጉባኤው ቤተ ክርስቲያናችን ከመሬት ስሪት ተነሥታ በሕዝብ ባለቤትነት ላይ የተመሠረተችበትና ሕጋዊ ሰውነት ያገኘችበትም የሕግ አካል ነው፡፡