መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
እነሆ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀኒት ተወልዶላችኋል ሉቃ.2፥11
ታኅሣሥ 27 ቀን 2005 ዓ.ም.
መጋቤ ብሉይ አእምሮ ዘውዴ
እንኳን ለጌታችን ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ አይደለም፡፡ ከጥንት ከመሠረት ጀምሮ በመላእክት፤ በነቢያት ሲነገር፤ ሲሰበክ የመጣ ነው እንጂ፡፡ ማቴ.1፥18፡፡
ሰው የመሆኑን ምሥጢር ለመጀመሪያ ጊዜ በማእከለ ገነት የተናገረ እርሱ እግዚአብሔር ነው፡፡
አባታችን አዳም ከእግዚአብሔር ትእዛዝ ወጥቶ ዕፀ በለስን በልቶ ከጸጋ እግዚአብሔር በተራቆተ ጊዜ /አዳም ኮነ ከመ አሐዱ እምኔነ/ አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ዘፍ.3፥22 ብሎ ከሦስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው እንደሚሆን ተናግሯል፡፡ በዚህ ቃል መሠረት /መሪነት/ ቅዱሳን መላእክት ምሥጢረ ትንቢት ተገልጾላቸዋል፡፡ እነሱም የተገለጸላቸውን ምሥጢረ ትንቢት ኀላፍያትንና መጻእያትን ለሚናገሩ ነቢያት ነግረዋቸዋል፡፡ ቅዱሳን ነቢያትም ከእግዚአብሔር ያገኙትን ከመላእክት የሰሙትን መነሻ አድርገው በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ምሳሌያት በተለያዩ ዘመናት የወልደ እግዚአብሔርን ሥጋዌ ሰብከዋል /ገልጸዋል/ ዕብ.1፥1፡፡ ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ፥ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፡፡
ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ፡፡
ታኅሣሥ 26 ቀን 2005 ዓ.ም.
በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ
የሕፃኑ የኢየሱስ ልደት /ለሕፃናት/
ታኅሣሥ 26 ቀን 2005 ዓ.ም.
ከወልደ ኢየሱስ /ቤካ ፋንታ/
ልጆችዬ እንደምን ሰነበታችሁ? ዛሬ ስለ ታላቁ ሕፃን ልደት የምነግራችሁ ነገር አለና በማስተዋል ተከታተሉኝ እሺ፡፡ ጎበዞች!
የዛሬ ሁለት ሺ ዓመት ገደማ ነው፡፡ በኢየሩሳሌም ሀገር ንጉሡ ሄሮድስ ሕዝቡን ሁሉ ቤተልሄም ወደምትባል ከተማ ጠራቸው፡፡ እመቤታችንም በዚያ ጊዜ የአሥራ አምስት/15/ ዓመት ልጅ ሆኖ በሚጠብቃት በአረጋዊው /በሽማግሌው/ ዮሴፍ ቤት ትኖር ነበር፡፡ እመቤታችን ድንግል ማርያም ሕፃኑን ኢየሱስ ክርስቶስን ፀንሳ ልትወልድ ደርሳ ሳለ ወደ ቤተልሄም ከተማ ከአረጋዊው ጠባቂዋ ዮሴፍና ከቅድስት ሰሎሜ ጋር ሄደች፡፡
“ወብዙኀን ይትፌሥሑ በልደቱ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል” ሉቃ.1፥14
ታኅሣሥ 25 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ
በስልታዊ ዕቅድ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ
ታኅሣሥ 22 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደጀኔ
ማኅበረ ቅዱሳን ከ2005 ዓ.ም – 2008 ዓ.ም ድረስ የሚተገበረውን የ4 ዓመት ስልታዊ ዕቅድ ዙሪያ በ6 ማእከላት ማስተባበሪያ አማካኝነት ለሁሉም ማእከላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ምክክር መሰጠቱ ተገለጸ፡፡
እኛ የምናመልከው አምላክ ኪሚነደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፡፡ ት.ዳን.3፥17
ታኅሣሥ 18 ቀን 2005 ዓ.ም.
በዲ/ን ኀይለ ኢየሱስ ቢያ
ንጉሡ ናቡከደነጾር በዱራ ሜዳ ላቆምኩት የወርቅ ምስል ካልሰገዳችሁ ከእጄ የሚያድናችሁ አምላክ ማን ነው? ብሎ በኀይልና በዛቻ በጠየቃቸው ጊዜ ሠለስቱ ደቂቅ በልበ ሙሉነት፥ በፍጹም እምነት፥ መልስ የሰጡበት ኀይለ ቃል ነው፡፡ ከኀይለ ቃሉ ቅዱስ ዳዊት አመንኩ በዘነበብኩ /በተናገርሁት አመንሁ፤ እንዳለ መዝ.115፥1 ፍጹም እምነታቸውንና ታማኝነታቸውን፣ ጽናታቸውን እንረዳለን፡፡ ዛሬ የምናከብረው የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤል በዓል ሠለስቱ ደቂቅን ከባቢሎን እሳት ያዳነበት ነው፡፡ ታሪኩ የተፈጸመው በብሉይ ኪዳን ዘመን ከ605-562 ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በነገሠው በናቡከደነጾር ዘመን ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘመን ከጣዖት አምላኪና አስመላኪ ኀያላን ነገሥታት መካከል አንዱ ናቡከደነጾር ነበር፡፡ ምስሉ የቆመው በ587 ቅ/ል/ክ እንደሆነ መተርጎማን ያስረዳሉ፡፡ ዳን.3፥1 ናቡከደነጾር እስራኤላውያንን በማረከበት ዘመን ዳንኤልንና ሦስቱን ሕፃናት በልዩ ሁኔታ አክብሯቸው ነበር፡፡
የጥናትና ምርምር ማእከሉ ያዘጋጀው የጥናት ጉባኤ ተራዘመ
ታኅሣሥ 17 ቀን 2005 ዓ.ም. በማኅበረ ቅዱሳን የጥናትና ምርምር ማእከል ታኅሣሥ 20 ቀን 2005 ዓ.ም. “በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የፓትርያርክ ምርጫና የአባቶች እርቀ ሰላም” በሚል መሪ ቃል አዘጋጅቶት የነበረው የጥናት ጉባኤ ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ ሲሆን የሚካሄድበትን ጊዜ ወደፊት የምናሳውቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የልምድ ልውውጥ አደረጉ
ታኅሣሥ 17 ቀን 2005 ዓ.ም.
በዲ/ን ኅሩይ ባየ
ከታኅሣሥ 11-15 ቀን 2005 ዓ.ም. ለአምስት ተከታታይ ቀናት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የልምድ ልውውጥ አደረጉ፡፡ የልምድ ልውውጡ የተከናወነው በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ሲሆን በአምስቱ ዕለታት በየቀኑ እስከ አንድ ሺሕ ለሚሆኑ የተለያዩ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች መካፈላቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ሥልጠናው የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ
ታኅሣሥ 17 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ማኅበረ ቅዱሳን ከታኅሣሥ 6-11 ቀን 2005 ዓ.ም. ከ65 በላይ ለሚሆኑ የገዳማት አበመኔቶች፣ እመምኔቶችና ተወካዮች “የቤተ ክርስቲያንን ተልእኮ ለማሳካት የገዳማት ድርሻ” በሚል መሪ ቃል የግማሽ ቀን ዐውደ ጥናትና በዩኒቨርስቲ ምሁራን፤ በቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የገዳማት መምሪያ እንዲሁም በተጋባዥ ምሁራን ለአምስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና ተጠናቀቀ፡፡
ከልቼ ቤተመንግሥት እስከ ታዕካ ነገሥት ኢየሱስ
ታኅሣሥ 15 ቀን 2005 ዓ.ም.
በመ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ
በአብዛኛው ኢትዮጵያውን ዘንድ የሚወደዱትና “እምዬ” በሚል ቅጽል የሚጠሩት ዐፄ ምኒልክ ለሀገሪቱም ሆነ ለቤተ ክርስቲያን ባለውለታ ነበሩ፡፡ “እምዬ” የሚለውን ቅጽል ሕዝቡ የሰጣቸው፤ የተራበውን ሕዝብ ግብር የሚያበሉ፤ ያለ ፍርድ ሰው የማይቀጡና ደግ ስለሆኑ ነው፡፡
ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ከአባታችው ከሸዋው ንጉሥ ኃይለ መለኮት ሣህለ ሥላሴና ከእናታቸው ወይዘሮ እጅጋየሁ ለማ አድያም ነሐሴ ፲፪ ቀን ፲፰፻፴፮ ዓ.ም. ደብረ ብርሃን አካባቢ አንጎለላ ከሚባል ሥፍራ ተወልደው፤ በአንጎለላ መቅደላ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ክርስትና ተነሡ። አያታቸው ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ የምኒልክን መወለድ ሲሰሙ “ምን ይልህ ሸዋ” በሉት ብለው ስም አወጡ። እሳቸው “…ምኒልክ በሚል ስም የሚነግሥ ንጉሥ ኢትዮጵያን ታላቅ ያደርጋታል” የሚል ትንቢት ስለነበር ‘ምኒልክ’ የኔ ስም ነው ብለው ነበር። ሆኖም፣ በህልማቸው ከልጁ ጋር አብረው ቆመው ከሳቸው ጥላ የልጁ ጥላ በልጦ፤ በእግር የረገጡትን መሬት ሲያለካኩ እሳቸው ከረገጡት ልጁ የረገጠው ረዝሞ አዩ። ከዚህ በኋላ “ምኒልክ የኔ ስም አይደለም። የሱ ነው። ስሙን ምኒልክ በሉት” ብለው አዘዙ። ጳውሎስ ኞኞ “አጤ ምኒልክ” በተባለው መጽሐፍ ።