መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
ኒቆዲሞስና አዲሱ ልደት
መጋቢት 20 ቀን 2007 ዓ.ም.
በዲ/ን ታደለ ፈንታው
በቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል በምዕራፍ ሦስት ብዙ አሕዛብ ወደ ክርስትና እምነት የተቀላቀሉበት ምዕራፍ ነው፡፡ድኅነትን በትጋት ለመፈጸም የሚታገሉ ክርስቲያኖች ይሄንን ምዕራፍ ሲያነቡ ከኒቆዲሞስ ጎን መቆማቸው የሚያጠራጥር አይሆንም፤ ከጌታ ጋር ምስጢራዊ የሆነ ውይይትን መቀጠል ይፈልጋሉ፡፡ በሕይወታቸው የተከፈተ የአዲስ ኪዳን መንገድን እንዳለ ሲገነዘቡም ጌታን ይከተላሉ፡፡ ከእርሱ ጋር ከቅዱስ መንፈሱም ጋር አንድ ይሆናሉ፡፡ አዲስ ልደትን ያገኛሉ ፤ይህም በጥምቀት የሚገኝ ልጅነት ነው፡፡
የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር ቅድመ ዝግጅት በኦሎንኮሚ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን
⢠መርሐ ግብሩ በማኅበሩ ድረ ገጽ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ ይተላለፋል፡፡
መጋቢት 11 ቀን 2007 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
በአሰቦት ገዳም ደን ተቀስቅሶ የነበረው እሳት ሙሉ ለሙሉ ጠፍቷል
መጋቢት 11 ቀን 2007 ዓ.ም. በእንዳለ ደምስስ በአሰቦት ገዳም ደን ላይ ተቀስቅሶ የነበረው እሳት ሙሉ ሙሉ መጥፋቱን ከገዳሙ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ማኅበረ መነኮሳቱ፤ የፌደራል ፖሊስ አባላት እና ምእመናን ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት በአሁኑ ስዓት ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት በመቻሉ በገዳሙ ውስጥ ማኅበረ መነኮሳቱ የተለመደውን አገልግሎታቸውን ቀጥለዋል፡፡ÂÂ
የመምህር አካለ ወልድ የሐዲስ ኪዳን የመጻሕፍት ትርጓሜ ት/ቤት የበግ ማድለብ ፕሮጀክት ተግባራዊ ሊደረግ ነው
መጋቢት 9 ቀን 2007 ዓ.ም
ከደሴ ማእከል
በዝቋላ ገዳም የተቀሰቀሰው እሳት ለማዳፈን ጥረት እየተደረገ ነው
የካቲት 26 ቀን 2007 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ምኩራብ(የዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት)
የካቲት 20 ቀን 2007 ዓ.ም.
የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ)
ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ ወመሐረ ቃለ ሃይማኖት ወይቤሎሙ ምጽዋተ አበድር እመሥዋዕት አነ ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት እግዚኣ ውእቱ ለሰንበት ወልደ እጓለ እመሕያው ኢትግበሩ ቤተ አቡየ ቤተ ምስያጥ ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ይሰመይ ቦአ ምኩራቦሙ ወገሠፆሙ ያርምሙ አንከሩ ምህሮቶ ሞገስ ቃሉ ወጣዕመ ነገሩ ወሣዕሣዓ አፉሁ፡፡
በዝቋላ ገዳም የኢሬቻ በዓል እንደሚከበር በሚዲያ የተሰራጨው ዜና ማረሚያ እንዲሰጥበት ቅዱስ ፓትርያርኩ አሳሰቡ
የካቲት 14 ቀን 2007 ዓ.ም.
የዐቢይ ጾም ሳምንታት
የካቲት 12 ቀን 2007 ዓ.ም.
ቅድስት(የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት)
የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ)
ግነዩ ለእግዚአብሔር ወጸውዑ ስሞ ወንግርዎሙ ለአሕዛብ ምግባሮ ሀቡ ስብሐተ ለስሙ አክብሩ
ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ ዝግቡ ለክሙ መዝገበ ዘበሰማያት ኅበ ፃፄ ኢያማስኖ ወኢይረክቦ ሰራቂ ድልዋኒክሙ ንበሩ ዘበላዕሉ ጸልዩ ኀበ ሀሎ ክርስቶስ፡፡
ኩኑ ቅዱሳን እስመ ቅዱስ አነ” ዘሌ.19፡2
የካቲት 12ቀን 2007 ዓ.ም.
፲ቱ ማዕረጋት
ቅዱሳን ማለት የተቀደሱ፣ የከበሩ፣ የተመሰገኑ፣ የተለዩ፣ የተመረጡ፣ ንጹሐንየሆኑ፣ የጠሩ….. ወዘተ ማለት ነው፡፡ ቅዱሳን በዚህ ስም የሚጠሩበት ከሰው ወይም ከምድራዊ ባለሥልጣን የተቸሩት አይደለም፡፡ በሃይማኖት ጸንተው በምግባር ጐልምሰው የሥጋ ምኞታቸውን ጥለው አፍርሰው ሲገኙ የቅድስና ባለቤት ቅዱስ እግዚአብሔር እነሱን /ቅዱሳንን/ መሣሪያ አድርጐ ኃይሉንና ሥልጣኑን ቢገልጽባቸው ማኅደረ እግዚአብሔር መሆናቸው ይገለጻል፡፡ በዚህ ጊዜ ቅዱሳን ይባላሉ፡፡
የሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ባለ 4 ፎቅ ሁለገብ ህንጻ እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት አስመረቀ
የካቲት 09ቀን 2007ዓ.ም.
ዲ/ን ያለው ታምራት