መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
የጀበራ ማርያም አንድነት ገዳምን ዳግም ለማቋቋም ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑ ተገለጸ
ጥቅምት 29 ቀን 2007 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት በደምቢያ ወረዳ በጣና ሐይቅ ውስጥ በ1335 ዓ.ም. ተገድማ የነበረችው የጀበራ ማርያም አንድነት ገዳም ከፈረሰች ከበርካታ ዘመናት በኋላ ዳግም ለማቋቋም ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገዳሙን መልሶ ለማቋቋም በማስተባበር ላይ የሚገኙት አባ ዘወንጌል ገለጹ፡፡
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በጸሎተ ምኅላ ተጀመረ
ጥቅምት 11 ቀን 2007ዓ.ም. መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ በዓመት ሁለት ጊዜ የሚደረገው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ዛሬ ጥቅምት 11ቀን 2007ዓ.ም. ከቀኑ ዐሥር ሰዓት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በጸሎተ ምኅላ ተጀመረ፡፡ የጥቅምት 2007 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ከጥቅምት 12 ቀን 2007 ዓ.ም. […]
ቅዱሳን ፓትርያርኮችና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትሥርዓተ ጸሎትና ፍትሐት ተፈጸመላቸው
ጥቅምት 10 ቀን 2007 ዓ.ም.
ይብረሁ ይጥና
ከአጸደ ሥጋ ዓለም በሞት ተለይተው በአጸደ ነፍስ የሚገኙ ቅዱሳን ፓትርያኮችና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፤ ጥቅምት 9 ቀን 2007 ዓ.ም በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጸሎተ ፍትሐት ተደረገላቸው፡፡ ሥርዓተ ጸሎተ ፍትሐቱ በተለይ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ፣ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ፣ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖትና ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ፣ ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳትን እንዲሁም ቤተክርስቲያንን አገልግለው ያለፉ አበው የታሰቡበትና በረከታቸው በአጸደ ሥጋ ላለነው እንዲደርስ ጸሎት የተደረገበት ነው፡፡
የ33ኛው ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ባለ 21 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ
ጥቅምት 8 ቀን 2007 ዓ.ም.
መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ
የ33ኛው ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ማጠቃለያ መርሐ ግብር የተጀመረው ከረፋዱ 2፡46 ነበር፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ ፖትርያርክ አቡነ ማትያስ ጉባኤውን በጸሎት ከከፈቱ በኋላ ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ገብርኤል “ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን” በሚል ርዕስ ከምንጊዜውም በላይ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት፣ መጠበቅ እንደሚገባ ሰፋ ያለ ትምህርት ሰጥተዋል፡፡
የ33ኛው ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚገኙ ሀገረ ስብከቶችን ሪፖርት አደመጠ፡፡
ጥቅምት 8 ቀን 2007 ዓ.ም.
መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ
ሦስተኛ ቀኑን የጠናቀቀው የ33ኛው የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚገኙ ሀገረ ስብከቶችና ሪፖርት አድምጦ አጠናቋል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን የጠራው የ”አጋርነት መግለጫ” መርሐ ግብር የለም!
ጥቅምት 8 ቀን 2007 ዓ.ም.
እሑድ ጥቅምት ዘጠኝ ቀን 2007 ዓ.ም ማኅበረ ቅዱሳን እየደረሰበት ያለውን ክስ በመቃወም ለማኅበሩ ያለንን አጋርነት እንግለጽ በሚል ባልታወቁ አካላት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የተጠራውን መርሐ ግብር አስመልክቶ፤ ማኅበሩ መርሐ ግብሩ እንዲደረግ ጥሪ ያላቀረበ መኾኑንና ስለጠራውም አካል ምንም ዓይነት ዕውቀት እንደሌለው የማኅበሩን ሕዝብ ግንኙነት በመጥቀስ መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ ማኅበሩ የሰጠውን አጭር መግለጫ እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን የጠራው ሰልፍ እንደሌለ አስታወቀ
ጥቅምት 7 ቀን 2007 ዓ.ም.
በተለያዩና ባልታወቁ አካላት ለማኅበሩ አጋርነት ለማሳየት በመጪው እሑድ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሰልፍ ለማድረግ በማኅበራዊ ሚዲያው የሚሽከረከረውን አስመልክቶ ከአባላቱ ለቀረበለት ጥያቄ የሚያውቀው ነገር እንደሌለና ማኅበሩም ምንም ዓይነት ጥሪም እንዳላካሔደ የማኅበረ ቅዱሳን የሕዝብ ግንኙነት ክፍል አስታወቀ፡፡
33ኛው አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የሦስተኛ ቀን ውሎ
ጥቅምት 7 ቀን 2007 ዓ.ም. መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ የ33ኛው የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ሀገረ ስብከቶችን የ2006 ዓ.ም. የሥራ ክንውን ሪፖርት አደመጠ፡፡ ሦስተኛ ቀኑን የያዘው ይህ ጉባኤ በሀገረ ስብከቶች አማካኝነት የቀረበውን ሪፖርቶች ያደመጠ ሲሆን በአብዛኛው የሀገረ ስብከቶች ሪፖርት ማኅበረ ቅዱሳን ለቤተ ክርስቲያን የሚያደርገውን ሁለገብ ድጋፍ ከፍተኛ መሆኑን በሪፖርቶቹ የቀረቡ ሲሆን የጉባኤው ታዳሚም አድናቆቱን […]
33ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው እንደቀጠለ ነው፡፡
ጥቅምት 6 ቀን 2007 ዓ.ም.
መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥቅምት 5 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም የተጀመረው የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ቀጥሏል፡፡ በጥቅምት 5 ቀን የከሰዓት ውሎና ጥቅምት 6 ቀን ጠዋት 24 አህጉረ ስብከቶች ሪፓርቶቻቸውን አቅርበዋል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን በ2006 ዓ.ም ከ13,948,984.71 በላይ ወጪ በማድረግ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ደገፈ
ጥቅምት 5 ቀን 2007 ዓ.ም.
መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ
በ33ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ባቀረቡት ሪፖርትና በዐዋጅ ነጋሪ መጽሔት 6ኛ ዓመት ቁጥር 10 ጥቅምት 2007 ዓ.ም ላይ በተገለጸው ሪፖርት ውስጥ የማኅበረ ቅዱሳን የ2006 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ከነጻ ሞያ አገልግሎት ውጭ ከ13,948.984.7 /አሥራ ሦስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ዐርባ ስምንት ሺሕ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ዐራት ብር/ በላይ ወጪ በማድረግ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት መደገፉ ተገልጿል፡፡