• እንኳን በደኅና መጡ !

የማኅበሩ ሰብሳቢ ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም

ቅዱስ ሲኖዶስ ጠንካራ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል

ግንቦት 10/2003 ዓ.ም.

በቤተክርስቲያኒቱ አጠቃላይ ሁኔታ ላይ የሚመክረው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በቀጣይ በቤተክርስቲያኒቱ አገልግሎት መጠናከርና በገጠሟት ችግሮች ላይ መፍትሔን የሚሰጥ ጠንካራ ውሳኔ ያሳልፋል ብሎ እንደሚያምን ማኅበረ ቅዱሳን አስታወቀ፡፡ የማኅበሩ ሰብሳቢ ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም እንዳስታወቁት፤ ዘንድሮ ከግንቦት 10 ቀን ጀምሮ የሚካሔደው ዓመታዊ መደበኛ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በእግዚአብሔር አጋዥነት እና በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ በመሆኑ ጠቃሚ ሀሳቦች የሚነሡበት፤ ለቅድስትቤተክርስቲያን የሚበጁ ጠንካራ ውሳኔዎች የሚተላለፉበት እንደሚሆን ማኅበረ ቅዱሳን በፅኑ ያምናል፡፡

«እርሳቸው የያዙት መንገድ ሙሉ በሙሉ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ማዳከም ነው፡፡ » ማኅበረ ቅዱሳን

 ግንቦት 9/2003ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን ተመሥርቶ በሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር አገልግሎት ከጀመረ አንስቶ ወደ 10 የሚጠጉ የመምሪያ ኃላፊዎች ተፈራርቅዋል፡፡ እስከ አሁን ምንም ያልተባለለት የማኅበሩና ማደራጃ መምሪያው ግንኙነት፣ የአሁኑ የመምሪያው ኃላፊ አባ ሠረቀብርሃን ከመጡ ከ6 ዓመት በፊት ጀምሮ፣ ችግሮች እየገጠሙት እንደሆነ ይነገራል፡፡ ማኅበሩም አሁን ያሉት የመምሪያው ኃላፊ አላሠራኝ አሉ በማለት ይወቅሳል፡፡ ይህንን በተመለከተ ከማኅበሩ ዋና ጸሐፊ ዲ/ን ሙሉጌታ ኃ/ማርያም ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡ መልካም ንባብ፡፡
 

ማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ፕሮግራም ቢሮ ያከናውናቸውን ተግባራት አስታወቀ።

በይብረሁ ይጥና

ሥራዎቹንም የሚያሳይ ዓውደ ጥናት በኢትዮጵያ የስብሰባ ማእከል እንደሚካሔድ ተገልጧል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ  መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን በትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ዋና ክፍል የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ፕሮግራም ማስተባበሪያ ቢሮ እስካሁን ያከናወናቸውንና በቀጣይ ሊሠራ ያቀዳቸውን ተግባራት አስታወቀ፡፡

ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም (ክፍል ሦስት)

ዲ/ን ዮሐንስ ልሳነወርቅ

ግንቦት 4፣ 2003ዓ.ም

ከክፍል ሁለት የቀጠለ

5.የሥጋ(ሰውነት) ክብር (The value of the Body)

ቅዱስ ኤፍሬም የሥጋን ክብር ለመንቀፍ  ከሚሹ ከተወሰኑ የቀድሞ የክርስትና ልማዶች መገለጫ ከሆኑት ከፕላቶናዊ ወይም ከምንታዌ ዝንባሌዎች  ፣  በእጅጉ የራቀ ነው። ለቀና አመለካከቱ መነሻው ነጥብ ሥጋ ከእግዚአብሔር ፍጥረታት መካከል ስለሆነ ሊጠላ አይገባዉም የሚል እውነታ ነው፤ በየትኛዉም መንገድ  ክፉ ተደርጎ ከሚታሰበው አስተሳሰብ  የራቀ ይሁን። ግና በተጨማሪ ቅዱስ ኤፍሬም ሦስት ጠቃሚ ግንዛቤዎች አሉት።

የሆሣዕና ምንባብ17(ዮሐ.5÷11-31)

እርሱም መልሶ÷ “ያዳነኝ እርሱ፡- አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለኝ” አላቸው፡፡ አይሁድም÷ “አልጋህን ተሸክመህ ሂድ ያለህ ሰውዬው ማነው?” ብለው ጠየቁት፡፡ ያ የተፈወሰው ግን ያዳነው ማን እንደ ሆነ አላወቀም፤ ጌታችን ኢየሱስ በዚያ ቦታ በነበሩት ብዙ ሰዎች መካከል ተሰውሮ ነበርና፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ኢየሱስ

የሆሣዕና ምንባብ16(ሐዋ.28÷11-ፍጻ.)

 ከሦስት ወር በኋላም በዚያች ደሴት ወደ ከረመችው ወደ እስክንድርያ መርከብ ወጣን፤ በዚያች መርብ ላይም የዲዮስቆሮስ ምልክት ነበረባት፤ ይኸውም “የመርከበኞች አምላክ” የሚሉት ነው፡፡ ከዚያም ሄደን ወደ ሰራኩስ ደረስን፤ በዚያም ሦስት ቀን ተቀመጥን፡፡ ከዚያም ሄደን ሬቅዩን ወደምትባል ሀገር ደረስን፤ በማግሥቱም ወጣን፤ ከአንድ

የሆሣዕና ምንባብ15(1ኛጴጥ.4÷1-12)

 ክርስቶስ ስለ እኛ በሥጋው ከተሰለቀ÷ እናንተም ይህቺን ዐሳብ ጋሻ አድርጋችሁ ኑሩ፤ በሥጋዉ መከራ የተቀበለ ከኀጢአት ድኖአልና፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ በሥጋው ከሕይወቱ ዘመን የቀረውን÷ በሰው ፈቃድ ሳይሆን በእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲፈጽም ነው እንጂ፡፡ የአሕዛብን ፈቃድ፡- ዝሙትንና ምኞትን÷ ስካርንና ወድቆ ማደርን÷ ያለ ልክ መጠጣትንና

የሆሣዕና ምንባብ14(ዕብ. 9÷11-ፍጻ.)

 ክርስቶስ ግን ለምትመጣይቱ መልካም ነገር ሊቀ ካህናት ሆኖ÷ የሰው እጅ ወደ አልሠራት÷ በዚህ ዓለም ወደ አልሆነችው÷ ከፍተኛዪቱ ወደምትበልጠውና ወደምትሻለው ድንኳን÷ የዘለዓለም መድኀኒትን ገንዘብ አድርጎ÷ በገዛ ደሙ አንድ ጊዜ ወደ መቅደስ ገባ እንጂ በላምና በፍየል ደም አይደለም፡፡ የላምና የፍየል ደም÷ በረከሱትም

የሆሣዕና ምንባብ13(ዮሐ.12÷12-20)

በማግሥቱም ለበዓል መጥተው የነበሩ ብዙ ሰዎች ጌታትን ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚመጣ በሰሙ ጊዜ÷ የዘንባባ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው “ሆሣዕና በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ÷ የእስራኤልም ንጉሥ ቡሩክ ነው” እያሉ ወጥተው ተቀበሉት፡፡ ጌታችን ኢየሱስም የአህያ ውርንጫ አግኝቶ በእርስዋ ላይ ተቀመጠ፡፡ “የጽዮን ልጅ ሆይ÷ አትፍሪ፤

የሆሣዕና ምንባብ12(ሉቃ.19÷28-ፍጻ.)

 ይህንም ተናግሮ ወደ ፊት ሄደ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም ወጣ፡፡ ደብረ ዘይት ወደ ሚባል ተራራ አጠገብ ወዳሉት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረበ ጊዜ÷ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ላከ፡፡ እንዲህም አላቸው÷ “በፊታችሁ ወደ አለችው መንደር ሂዱ፤ገብታችሁም ሰው ያልተቀመጠበት የታሰረ ውርንጫ ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁም አምጡልኝ፡፡

ማስታወቂያ

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria

ስለ ማኅበረ ቅዱሳን መሰረታዊ መረጃዎች

ስያሜ

ማኅበረ ቅዱሳን እግዚአብሔር ያከበራቸው የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት በአጠቃላይ የቅዱሳን ገድል፣ ትሩፋትና አማላጅነት የሚዘከርበት በመሆኑ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን›› የሚል ስያሜውን አግኝቷል፡፡

የማኅበሩ ርእይ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎትና ኢኮኖሚያዊ አቅም ተጠናክሮ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርተ ወንጌል በመላው ዓለም ተስፋፍቶ በሃይማኖት ጽኑዓን የሆኑ ምእመናን በመላው ዓለም በዝተው ማየት፡፡

ተልእኮ

ማኅበሩ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውጤት የሆኑትን የተለያዩ ትምህርተ ሃይማኖት ማስፋፊያ ዘዴዎችን በመጠቀም ግቢ ጉባኤያትና ምእመናን የወንጌልን ትምህርት፣ ሥርዓት፣ ትውፊት፣ እንዲያቆዩና እንዲጠበቁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር እንዲጠናከር አቅሙ እንዲያድግ ማድረግና በየዘመኑ የሚከሰቱ ተለዋዋጭ ሃይማኖታዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች በመቃኘት የቤተ ክርስቲያኒቱን ሐዋርያዊ አገልግሎት ማጠናከር፡፡

አስፈላጊነት

የቤተ ክርስቲያቱ መዋቅር ያልሸፈነችውን ክፍተቶች በመሙላት ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማ የሚገቡትን የዘመኑን ትውልድ ከመንፈሳዊነትና ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትምህርት ጋር በማዋሐድና ከአበው በማቀራረብ ቤተ ክርስቲያን የምትጠብቅበትን ድርሻ እንድንወጣ ለማድረግ የማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎት አስፈላጊ ነው፡፡

ዓላማ

ማኅበሩ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ዐበይት ዓላማች አሉት፡፡

  • በከፍተኛ ትምህርት ተቋማ ውስጥ የሚማሩ ወጣቶችን በማኅበሩ ሥር አደራጅቶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እምነት፣ ሥርዓት እና ትውፊት እንዲማሩ እና የአባቶች ተተኪ እንዲሆኑ ማድረግ፣

  • የቤተክርስቲያን እምነትና ሥርዓት ሳይለውጥ ተጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ይቻል ዘንድ ለዘመኑ ትውልድ ትምህርተ ሃይማኖት እንዲዳረስ ማድረግ፣

  • ከሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት ጋር በመነጋገርና በማስፈቀድ ትምህርተ ወንጌልን በተለያዩ ዘዴዎች በመጽሔት፣ በጋዜጣ፣ በበራሪ ጽሑፎች፣ በካሴት እና በመሳሰሉት እንዲስፋፋ ማድረግ፣

  • የተማረው የኅብረተሰብ ክፍል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በገንዘብ፣ በዕውቀቱና በጉልበቱ እንዲያገለግል አስፈላጊውን ሁሉ ማመቻቸት፣

  • ስለ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥናት የሚያደርጉ ሰዎችን በተለይ ወጣት ምሁራንን ማበረታታና በሚቻለው ሁሉ መርዳት፡፡

አቋም

በማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ምንም ዓይነት ጣልቃ ገብነት የለውም፡፡

አመሠራረት

ስለ ማኅበረ ቅዱሳን አመሠረራት ጥቂት ነጥቦችን እናስታውስ፡፡ በ1980ዎቹ የጋንቤላና የመተከል የሠፈራ ዘመቻ ጥቂቶቹን አገናኘ፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ደግሞ ሌሎችን በጥበቡ እየጠራ በክረምት ጊዜ ዩኒቨርስቲዎቻቸው ሲዘጉ በዝዋይ ገዳም እንዲገናኙ አደረገ፡፡ በመጨረሻም አብዛኛዎቹን ወጣቶች በ1983 ዓ.ም በብላቴ ካምፕ አገናኛቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ መልካም አጋጣሚዎች ሆኑላቸውና የተለያዩ ማኅበራትን እያቋቋሙ ወጣቱ ትውልድ ከቤተ ክርስቲያን ጋር የማስተዋወቁን ሥራ አፋፍመው ቀጠሉበት፡፡ በዚህ የተሰበሰበው ኃይል አሁንም ተደራጅቶ ጠንካራ አገልግሎት የሚሰጥበትን አንድ ማኅበር እየፈለገ መጣ፡፡ በዚህ ምክንያት የተለያዩ ማኅበራትን በመመሥረት የየአቅማቸውን አገልግሎቶች ሲፈጽሙ የቆዩት ወጣቶች በአንድ ማኅበር ቢሰባሰቡ የሚሰጡት አገልግሎት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተገነዘበ፡፡ በዚህ ጊዜ ነበር በመላእክት ስም፣ በእመቤታችን ስም፣ በቅዱሳን ስም የተሰበሰቡት ሁሉ ለመታሰቢያነት የሚጠሯቸውን ቅዱሳን የማያስቀርና ተልእኮአቸውን የማይለውጥ አንድ ማኅበር ለመመሥረት የወሰኑት፤ ወስነውም አልቀሩ መሠረቱት፤ ማኅበረ ቅዱሳንን፡፡

ውኃ ልትቀዳ ወርዳ ጌታችንን አግኝታ እንደተመለሰችው ሰማርያይቱ ሴት፤ ከሄዱበት ምድራዊ ዓላማ ተጨማሪ ሰማያዊ ዓላማን አንግበው መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሰጥ ማኅበር ለመመሥረት ምክንያት የሆኑት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች እንደሙያ ዝግጅታቸውና ስጦታቸው ቤተ ክርስቲያናቸውን ለማገልገል አደራ ተቀበሉ፡፡ /ዮሐ. 4፤7/ ስለዚህም ማኅበሩ ሐዋርያዊ ተልእኮን ለማስፋፋትና ግቦቿን አሳክታ ከችግሮቿ ወጥታ ለሕዝቦቿ ማኅበራዊ ሕይወት ለውጥ የመሪነት ሚና የምትጫወት ቤተ ክርስቲያንን ለማየት የሚያስችል የአገልግሎት ስልት ነድፎ ብቅ አለ፡፡

አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ
የሸዋ ሊቀ ጳጳስ ፲፱፻፴፪-፲፱፻፹፪ዓ.ም.

የማኅበሩ ህንጻ