መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
ክብረ በዓላት በመጽሐፍ ቅዱስ
አሁን አሁን ግን በብዙዎቻችን ዘንድ እንደሚስተዋለው የበዓላት አከባበር ሥርዓት እየተጣሰ ይገኛል፡፡ በበዓላት ቀን ሥራ መሥራት እየተለመደ መጥቷል፡፡ ይህ ልማድ ሊስተካከልና ሊቀረፍ ይገባል፡፡ ከዚሁ ዅሉ ጋርም እንደ በዓለ ጥምቀት ባሉ የዐደባባይ በዓላት ወቅት የሚታየው የሥጋዊ ገበያ ግርግር ክርስቲያናዊ የበዓላት አከባበር ሥርዓትን እንዳያጠፋብን ልንጠነቀቅ ያስፈልጋል፡፡
ነቢዩ ዮናስ ክፍል ሁለት
የነነዌ ሰዎች ከበደላቸው ተጸጽተው፣ ንስሐ ገብተው በመጾማቸውና በመጸለያቸው እግዚአብሔር ከጥፋት አድኗቸዋል፡፡ ልጆች! እኛም ዛሬ እግዚአብሔርን ብንበድለውና እርሱ የማይወደውን ክፋት ብንፈጽም እንደ ነነዌ ሰዎች ተጽጽተን ንስሐ ከገባን አምላካችን ቸር፣ ታጋሽ እና ይቅር ባይ አምላክ ስለኾነ ኀጢአታችንን ይቅር ብሎ ከጥፋት ያድነናል፡፡
ነቢዩ ዮናስ ክፍል አንድ
ልጆች! ባሕሩ ሲናወጥ የነበረው ለምን እንደኾነ ተረዳችሁ? ዮናስ እግዚአብሔር ያዘዘውን ትቶ ለመሸሽ በመርከቡ በመሳፈሩ ነው! እግዚአብሔርን ሳንታዘዝ ያሰብንበት ቦታ መድረስ የምንችል ይመስላችኋል ልጆች? አንችልም አይደል? አዎ፤ አንችልም፡፡ ምክንያቱም ዓለሙን ዅሉ የፈጠረ እግዚአብሔር ነውና በባሕርም ኾነ በየብስ (በደረቅ መሬት) ብንጓዝ ከእርሱ መሰወር ፈጽሞ አይቻለንም፡፡
ጾመ ሰብአ ነነዌ
ሕጉ የተዘጋጀልን እንደ ነነዌ ሰዎች እኛም ጾመን፣ ጸልየን ከኀጢአታችን እንነጻ ዘንድ ነው፡፡ ዛሬ ዓለማችን በኀጢአት ማዕበል እየተናወጠች ባለችበት ወቅት እኛም እንደ ነነዌ ሰዎች ከበደላችን ብንመለስ እና ንስሐ ብንገባ ቸሩ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ይቅርታና ምሕረት የባሕርይ ገንዘቡ ስለ ኾነ ‹‹ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ይቅር እላችኋለሁ፤›› ይለናል፡፡
ኢትዮ አሜሪካውያን ሕፃናት መዓርገ ዲቁና ተቀበሉ
ብፁዕነታቸውም ‹‹በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ›› በሚል ኃይለ ቃል ትምህርተ ወንጌል ሲሰጡ ማኅበረ ቅዱሳን ከመነሻው ጀምሮ ዓላማውና ተልእኮው ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተተኪዎችን ማፍራትና ስብከተ ወንጌልን ማስፋፋት መኾኑን እንደሚያውቁ ገልጸው አሁንም ማኅበሩ እየሰጠ የሚገኘውን መንፈሳዊ አገልግሎት አድንቀዋል፡፡
አስደናቂው የድንግል ማርያም ሞት
‹‹ለምንት ይዜኃር ኃያል በኃይሉ ወባዕል በብዝኃ ብዕሉ ኢያድለወ ሞተ ክርስቶስ ለሥጋ አባሉ ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐፅብ ለኵሉ፡፡ ኃይለኛ በኃይሉ ለምን ይታጀራል? ባለ ጸጋም በሀብቱ ብዛት፡፡ ክርስቶስ ለአካሉ አላደላም፤ ሞትስ ለሟች ይገባዋል፡፡ የእመቤታችን የቅድስት ማርያም ሞት ግን አስደናቂ ነው፡፡››
ዘመነ አስተርእዮ
በአስተርእዮ ሌሎች በዓላትም ይጠሩበታል፡፡ ለምሳሌ ድንግል ማርያም ጥር ፳፩ ቀን ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይቶ በደመና ተነጥቃ ወደ ገነት በመግባት ለጻድቃን እና ለመላእክት በሰማይና በምድር የተሰጣት ጸጋ፣ ክብር የተገለጸበት ዕለት ስለኾነ በዓሉ ‹‹አስተርእዮ ማርያም›› ይባላል፡፡
ዝክረ በዓለ ጥምቀት
ለታቦተ ሕጉ ምንጣፍ በዘረጉ እጆቻችን የሰው ንብረት እንዳንወስድ፤ የሰው ባል ወይም ሚስት እንዳናቅፍ፤ ሰውን እንዳንደበድብ፤ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በተሸቀዳደምንባቸው እግሮቻችን ወደ ኀጢአት መንገድ እንዳንሔድባቸው፤ ደሃ ወገኖቻችንን እንዳንረግጥባቸው እግዚአብሔር የዅላችንንም መጨረሻ ያሳምርልን፡፡
‹‹ጌትነቱን ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ፤›› /ዮሐ. ፪፥፲፩/፡፡
እመቤታችን ‹‹የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም›› በማለት መናገሯ ሕዝብህን (ምእመናንን) ‹‹ደምህን አፍሰህ፣ ሥጋህን ቈርሰህ አድናቸው›› ማለቷ ሲኾን፣ ይህም ‹‹ወይን›› በተባለው የልጇ የክርስቶስ ደም ቤዛነት ዓለም ይድን ዘንድ እመቤታችን ያላትን የልብ መሻት ያስገነዝባል፡፡
ጥምቀተ ክርስቶስ
ወንዶች በዐርባ ቀን፣ ሴቶች በሰማንያ ቀን በዕለተ ዓርብ ከቀኝ ጎኑ በፈሰሰው ማየ ገቦ ተጠምቀን ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ሁለተኛ የምንወለድበት ምክንያትም አዳም በዐርባ ቀኑ፣ ሔዋን በሰማንያ ቀኗ ከሥላሴ ያገኙትን ልጅነት መሠረት በማድረግ ነው፡፡