የጎንደር መካነ ስብሐት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን

ሐምሌ 10 ቀን 2006 ዓ.ም.

እንዳለ ደምስስ

ክፍል አንድ፡-

በጎንደር ከተማ በርካታ ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙ ሲሆን አብያተ ክርስቲያናቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና ደንብ ጠብቀው፣ እንዲሁም በዘመኑ የነበሩ የኢትዮጵያዊያን የሥልጣኔ ደረጃ ከፍተኛ መሆንን የሚያመለክቱ አሻራዎች አርፎውባቸዋል፡፡ ይህንንም አሻራዎቻቸውን ይዘው ዛሬ ድረስ ዓለምን እያስደመሙ ይገኛሉ፡፡ እነዚህም አድባራትና ገዳማት በነገሥታት፤ በባላባቶችና በሀገሬው ሰው የተተከሉ ሲሆኑ፤ በነገሥታቱ ከተተከሉት አድባራት ውስጥ በ1703 ዓ.ም በንጉሡ በዐፄ ዮስጦስ የተመሠረተችው የጎንደር መካነ ስብሐት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን አንዷ ናት፡፡

ደጀ ሰላሙ በድንጋይ ጥርብ እንደተካበ ጥንታዊነቱን ጠብቆ ግርማ ሞገሱን ተላብሶ ይታያል፤ የቤተ ክርስቲያኑ ዙሪያ በድንጋይ ካብ እንደታጠረ ከቅጥሩ ጋር ተያይዞ ነገሥታቱ ፀሎት ያደርጉባቸው የነበሩ በእንቁላል ቅርጽ የታነጹት ማማዎች ቁልቁል gonder ledetaአካባቢውን ለመቃኘት ያስችላሉ፡፡ ወደ ውስጥ ሲዘልቁ ድርቡሽ ጥንታዊውን ቤተ ክርስቲያን ሲያፈርስ ለታሪክ ምሥክርነት የቀሩት የቤተ ክርስቲያኑ ዓምዶች አሁን ያለውን ቤተ ክርስቲያን ዙሪያውን ከበው ይታያሉ፡፡ በግቢውና ውጪ የሚታዩት እድሜ ጠገብ ዛፎች፤ ቤተልሔሙ፤ የዐፄ ዮስጦስ መቃብር . . . ለቤተ ክርስቲያኑ ጥንታዊነት ምሥክርነታቸውን ይሰጣሉ፡፡

ግቢውን እየቃኘን በቤተ ክርስቲያኑ ዙሪያ ለመሥራት ላሰብነው ዘገባ መረጃ ሊሰጡን በቀጠሯቸው ተገኝተው እኛን በመጠበቅ ላይ ወደ ነበሩት አባቶችና ወንድሞች አመራን፡፡ ከቤተ ክርስቲያኗ አገልጋይ አባቶችና ወንድሞች ጋር ቤተ ክርስቲያኗን በሚመለከት ያደረግነውን ቆይታ እንደሚከተለው አጠናቅረነዋል፡፡

አመሠራረት

ዐፄ ዮስጦስ ንግሥናቸው በእናታቸው ወገን በመሆኑ በርካታ ተቀናቃኞች ነበሯቸው፡፡ ተቀናቃኞቻቸውም “ንግሥና በአባት ወገን እንጂ፤ እንዴት በእናት ወገን ይሆናል?” እያሉ በርካታ ሴራዎችን በማሴር ንግሥናቸውን ለመቀማት ጥረት አድርገውባቸው ነበር፡፡ ንጉሡ ግን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የነበራቸው ፍቅር እጅግ ጥልቅ ከመሆኑ የተነሣ ተቀናቃኞቻቸውን በጦርነት ብቻ ሳይሆን በጾምና በጸሎት ድል ያደርጓቸው ነበር፡፡

በአንድ የጾመ ፍልሰታ ለማርያም ወቅት ሱባኤ ላይ እያሉ ከተቀናቃኞቻቸው መካከል አንዱ መንግሥታቸውን ለመቀማት ጦር አዘመተባቸው፡፡ ወታደሮቻቸው በሁኔታው በመደናገጥ “ከሱባኤዎ ይውጡ፤ የመጣውን የጠላት ጦር መክተን እንመልስ ዘንድ ይምሩን፤ በጠላት ከመያዛችን በፊት ድረሱልን” በማለት አስጨነቋቸው፡፡

ዐፄ ዮስጦስ ግን አሻፈረኝ በማለት ከያዙት ሱባኤ እንደማይወጡ ለወታደሮቻቸው ይናገራሉ፡፡ ወታደሮቻቸውም ጥያቄያቸውን በመቀጠል “በሚቀጥለው ዓመት ሱባኤ ይገባሉ፤ ራስዎን፣ እኛንም ለጠላት አሳልፈው አይስጡን፤ እባክዎ ከሱባኤ ወጥተው ጠላቶቻችንን ድል እናድርግ” በማለት ተማጸኗቸው፡፡

የወታደሮቻቸው ጉትጎታ አላሳርፍ ያላቸው ንጉሡ “ጠላትን ድል አድርጌ በሰላም ከተመለስኩ በዚህ ቦታ ላይ የልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያንን እሠራለሁ” ሲሉ ስዕለት ተስለው ወታደሮቻቸውን እየመሩ ወደ ጦርነቱ ዘመቱ፡፡ በጦርነቱም ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ ድል አድርገው ተመለሱ፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ባደረገችላቸው መልካም ነገር በመደሰት ቃላቸውን ጠብቀው የመካነ ስብሐት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያንን ሱባኤ ይዘውበት በነበረበት ቦታ ላይ በ1703 ዓ.ም. ተከሉ፡፡

ቤተ ክርስቲያኗ በንጉሥ ዐፄ ዮስጦስ ስትመሠረት የነገሥታት ትክል በመሆኗ ብዙ ሰው በአጥቢያዋ አልነበረም፡፡ የምትተዳደረውም ሪም በሚባል ሥርዓት ነበር፡፡ /የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ከአለቃው ጀምሮ እስከ ዲያቆናትና ዐቃቢት ድረስ በተዋረድ እንደ አገልግሎታቸው ከቤተ ክርስቲያኗ ጉልት እየተከፈለ መሬት ይሰጣቸዋል፡፡ ይህ ለአገልጋዮቹ የሚሰጣቸው መሬት ሪም በመባል ይታወቃል፡፡ የቤተ ክርስቲያኗ አገልጋዮችም ከተሰጣቸው ሪም ላይ ከሚኖሩ ዜጎች ዓመታዊ ምርት /እህል ብቻ/ ሢሶውን ለመተዳደሪያቸው ይቀበላሉ፡፡/ በጊዜው ቤተ ክርስቲያኗን ለሚያገለግሉ ከ150 በላይ ለሆኑ ሊቃውንት ደምቢያ ከሚባል አገር እህል ይጫንላቸው ነበር፡፡

አድርሺኝ

ከጎንደር መካነ ስብሐት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን መተከል ጋር በተያያዘ በጎንደር ከተማ ውስጥ የሚካሔድ አንድ ሥርዓት አለ፡፡ ይህም ሥርዓት አድርሺኝ በመባል ይጠራል፡፡ ሥርዓቱ የሚከናወነው በፍልሰታ ጾም ወቅት ነው፡፡

ስለ ሥርዓቱ አጀማመር አባቶች ሲናገሩ፣ ዐፄ ዮስጦስ ወደ ጦርነት ሲዘምቱ “ጦርነቱን በልደታ ለማርያም ምልጃ ተደግፌ አሸንፌ ከተመለስኩ በፍልሰታ ለማርያም ሱባኤ ማታ ማታ ካህናቱን፤ መኳንንቱንና ምእመናንን ሰብስቤ ግብዣ አደርጋለሁ” በማለት ብፅዐት ይገባሉ፡፡ እርሳቸውም ድል አድርገው ተመለሱ፤ በቃላቸውም መሠረት ግብዣ አደረጉ፡፡ ሕዝበ ክርስቲያኑም እርሳቸውን ተከትሎ በጾመ ፍልሰታ ወቅት ይህን ሥርዓት ይተገብሩት ጀመር፤ ስያሜውም “አድርሺኝ” ተባለ፡፡

አድርሺኝ በመላው ጎንደር እስከ ዛሬ ድረስ በየቤተ ክርስቲያኑና በየአካባቢው በፍልሰታ ጾም ወቅት ይከናወናል፡፡ ምእመናን ከቅዳሴ መልስ ሱባኤው እስኪያልቅ በመረጡት አንድ ቤት ውስጥ ተሰብስበው ቆሎና ጠላ ተዘጋጅቶ በእመቤታችን ስም ጽዋ ይጠጣሉ። በተለይ መነኮሳያት እናቶች በሚታደሙበት ጽዋ ላይ “ኦ! ማርያም” የሚለውን የተማጽኖ መዝሙር ይዘምራሉ። ይህ መዝሙር በሚዘመርበት ጊዜ እመቤታችን ፊት ለፊት ስለምትቆም በፍፁም ተመስጦና መንበርከክ ያከናውኑታል።

በዋነኛነት የመካነ ስብሐት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት ይህንን የተቀደሰ ተግባር በማስተባበርና በማስፈጸም እንዲሁም ትውፊቱ እንደጠበቀ ለተተኪው ትውልድ እንዲተላለፍ በማድረግ እየሠራ ይገኛል፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና ዐፄ ዮስጦስ

gonder ledeta 2 ዐፄ ዮስጦስ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የነበራቸው ፍቅር እጅግ ጥልቅ ከመሆኑ የተነሣ በርካታ ታሪኮች እንዳሏቸው ይነገራል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የጥምቀትን በዓል ለማክበር ዐፄ ዮስጦስ ከካህናቱ፤ ከመኳንንቱና ከምእመናን ጋር በመሆን ታቦቱን አጅበው ቀሃ ዳር ወደሚገኘው ጥምቀተ ባሕር በመውረድ ላይ ሳሉ አንዲት ሴት ከታቦቱ አጠገብ ስትጓዝ ይመለከታሉ፡፡ “ከታቦቱ አጠገብ የምትጓዘውን ሴት ከሥፍራው አርቋት፤ ከታቦት አጠገብ እንዴት ብትዳፈር ነው የምትጓዘው?” በማለት ለወታደሮቻቸው ትእዛዝ ያስተላልፋሉ፡፡ ወታደሮቻቸው ግን ንጉሡ ያሏትን ሴት ማግኘት አልቻሉም፡፡ እሳቸውም ሠይፋቸውን መዝዘው ቢሔዱም ከታቦቱ አጠገብ ተሰወረችባቸው፡፡

“ይህ ምሥጢር ሳይገለጽልኝ ወደ ንግሥናዬና ወደ ቤተ መንግሥቴ አልመለስም” በማለት እዚያው ድንኳን አስተክለው ሱባኤ ይገባሉ፡፡ በሦስተኛው ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጻ “ከታቦቱ አጠገብ ያየኸኝ እኔ ድንግል ማርያም ነኝ” በማለት ተናገረቻቸው፡፡ ጊዜ እረፍታቸውንም መች እንደሚሆን አስታውቃና ባርካ፤ በየዓመቱ ኅዳር 21 በአክሱም ጽዮን ማርያም፤ ለአስተርእዮ ማኅደረ ማርያም እንደምገኝ ሁሉ በጥምቀት በጎንደር መካነ ስብሐት ልደታ ለማርያም እገኛለሁ በማለት ቃል ኪዳን ገብታላቸዋለች፡፡

ምእመናን በቤተ ክርስቲያኗ የጥምቀት ዕለት ገንዘብ አዋጥተው ዝክር መዘከር የጀመሩት ከዚህ ቃል ኪዳን ጋር በተገናኘ መሆኑን አረጋውያን ያስረዳሉ።

ለውኃ ለውኃ ምን አለኝ ቀሃ

የቀሃ ወንዝ በጎንደር ውስጥ የጎንደርን ከተማ ለሁለት ከፍሎ ይልፋል፡፡ ቀሃ በጎንደር ውስጥ ታዋቂ ከመሆኑ የተነሣም “ለውኃ ለውኃ ምን አለኝ ቀሃ” እየተባለም ይነገራል፡፡ የጥምቀት በዓል በሚከበርበት ወቅት የልደታ ለማርያም ታቦት በዚሁ አካባቢ ታርፋለች፡፡

gonder ledeta 3 አረጋዊ መንፈሳዊ ስለ እንጦንስ የትውልድ አካባቢ ሲናገር ቀሃ ወንዝን እንደምልክትነት ይጠቀመዋል፡፡ ወንዝ ዳር፤ ወንዝ አካባቢ እንደሆነ ይነግረንና ምን ትመስላለች የሚለውን ሲገልጽ “ቀሃ ዳር ልደታ ማርያም እንዳለች ሁሉ . . . ” እያለ ያብራራል፡፡
የልደታ ውኃበጎንደር ከተማው ውስጥ በዛ ያሉ የጸበል ቦታዎች የሚገኙ ሲሆን ከእነዚህ የጸበል ቦታዎች አንዱ በመካነ ስብሐት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ይገኛል፡፡ የጸበል ቦታውም የልደታ ውኃ በመባል እየተባለ ይጠራል፡፡ በጸበሉ በርካታ ድውያን የሚፈወሱበት ሲሆን እንደ ግሸ አባይ ከምእራብ ወደ ምሥራቅ ይፈሳል፡፡

የልደታ ውኃ በተለያዩ የትርጓሜ መጻሕፍት ውስጥ ትገኛለች፡፡ መምህር ኤስድሮስ ውዳሴ ማርያምን ሲተረጉሙ “ዳዊት ዘነግሠ ለእሥራኤል አመ ይትነሥኡ ላዕሌሁ ዕልዋን ፈተወ ይስተይ ማየ እም ዓዘቅተ ቤተልሔም. . .፤ የሕይወት ውኃነት እንዳላት ከምእራብ ወደ ምሥራቅ እንደምትፈሰው እንደ ልደታ ውኃ” ይላል፡፡

በጸበሏ ዛሬም ድረስ በርካታ ሕሙማን እየተፈወሱ ይገኛሉ፡፡

ይቆየን

የደብረ ሊባኖስ ገዳም አምስቱ ስያሜዎች

 ሰኔ 17 ቀን 2006 ዓ.ም.

የደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንድነት ገዳም ገዳማዊ ሥርዓቱ እንደተጠበቀ ቢሆንም የጎርፍ አደጋ፤ የብዝኅ ሕይወት መመናመን፤ የሕገ ወጥ የመሬት ወረራና ሌሎችም ችግሮች እየተፈታተኑት ይገኛል፡፡ ይህንን ችግር ለመቅረፍና ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት በገዳሙና በማኅበረ ቅዱሳን ባለሙያዎች ፕሮጀክቶች ተቀርጸው ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡ 

ፕሮጀክቶቹንም በተያዘላቸው እቅድ መሠረት ለማስፈጸም በጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ሠኔ 8 ቀን 2006 ዓ.ም. የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ላይ ፕሮጀክቶቹንና ገዳሙን አስመልክቶ የተዘጋጀ መጽሔት ለምእመናን ተሰራጭቷል፡፡ ከመጽሔቱ ያገኘናቸውን ጥቂት መረጃዎች እናካፍላችሁ፡-

የደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃማኖት አንድነት ገዳም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር- ጎጃም መውጫ በ104 ኪሎ ሜትር ርቀት፤ ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ 4.5 ኪሎ ሜትር ተገንጥሎ የሚገኝ የአንድነት ገዳም ነው፡፡
ገዳሙ በጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በ1296 ዓ.ም. የተቆረቆረ ሲሆን፤ 710 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ በገዳሙ አስተዳደር ሥር ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በተጨማሪ የቅዱስ አማኑኤል እና የቅዱስ ፊልጶስ አብያተ ክርስቲያናት ይገኛሉ፡፡

በገዳሙ ውስጥ የሚጎበኙ የተለያዩ የነገሥታት ሥጦታዎች፤ ቅዱሳት መጻሕፍት፤ ንዋየ ቅድሳት፤ የቅዱሳን አጽም፤ ፈውስ የሚገኝባቸው የጸበል ቦታዎችም ይገኛሉ፡፡

የደብረ ሊባኖስ ገዳም አምስቱ ስያሜዎችን ስንመለከት፡-

ምድረ ግራሪያ፡-
ግራሪያ የሚለውን ስያሜ የሰጠችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ምድረ ግብጽ ስትሰደድ በኢትዮጵያ ውስጥ ከቆየችባቸው ቦታዎች አንዱ ይህ ቅዱስ ቦታ ነው፡፡ ለአንድ ሳምንት ቆይታ አድርጋ የቦታውን ስም ምድረ ግራሪያ ስትል ሰይማዋለች፡፡ ግራሪያ ማለት ኩሉ ይገርር ሎቱ፤ ሁሉ ይገዛላታል ማለት ነው፡፡ አንድም ግራር በቁሙ ለሁሉ ጥላ፤ መሰብሰቢያ እንደሆነ ደብረ ሊባኖስም የሁሉ ጥላ መሰብሰቢያ ነውና ምድረ ግራሪያ ተብሏል፡፡

ደብረ አስቦ፡-
ደብረ አስቦ ማለት የዋጋ ተራራ ማለት ሲሆን፤ የሰየመውም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ አባታችን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዚህ ቅዱስ ሥፍራ ሃያ ዘጠኝ ዓመታት ከጸለዩ በኋላ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ቦታውንም ደብረ አስቦ፤ የድካምህ ዋጋ፤ የስምህ መጠሪያ ይሁንልህ በማለት ሰይሞታል፡፡

ኤላም፡-
ኤላም ማለት የእግዚአብሔር ክብር መገለጫ ማለት ነው፡፡ ይህ ቦታ የአባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት አጽም ለአርባ ዓመታት የቆየበት ቅዱስ ሥፍራ ነው፡፡ ስያሜውም የአቡነ ዮሐንስ ከማ ነው፡፡ ዮሐንስ ከማ የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት የመንፈስ ልጅ ናቸው፡፡ ኤላም የበረከት ቦታ፤ የሰላም ሠፈር ነው፡፡ የመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ተሰውሮ ይገኝበታል፡፡

ደብረ ሊባኖስ፡-
ደብረ ሊባኖስ ማለት የሊባኖስ ተራራ ማለት ነው፡፡ ጻድቁ አቡነ ሊባኖስ የተባሉት ሮማዊ አባት ለአርባ ዓመታት የጸለዩበት፤ ብዙ ገቢረ ተአምራት ያደረጉበት፤ ከእግዚአብሔር ጋር የተገናኙበት ነው፡፡ “ትትሌአል ወትከብር እምነ ኲሎን አድባራት ወገዳማት እሞን ለአህጉር፤ ከአድባራትና ገዳማት ትከብራለች፤ ከፍ ከፍም ትላለች፤ ለሀገራትም እናት ትባላለች” ሲል፡፡

አባ ሊባኖስ በጌታ የተወደደውንና የቅዱሳን ከተማ ደብረ ሊባኖስን በጣም ይወዱት ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ይህ ቦታ ከአንተ በኋላ ለሚመጣው ለተክለ ሃይማኖት ነውና አንተ ወደ ትግራይ ሀገር ሒድ፤ እድል ፈንታህ በዚያ ነው አላቸው፡፡ እርሳቸውም አርባ ዓመታት የደከምኩበት ለከንቱ ነውን? አሉት ቅዱሳን አጽንኦተ በዓት ይወዳሉና፡፡ መልአኩም ስለ ድካምህ ይህ ቦታ ደብረ ሊባኖስ ይባላል እንጂ ደብረ ተክለ ሃይማኖት አይባልም አላቸው፡፡ እሳቸውም ፈቃድህ ይሁን ብለው ወደ ትግራይ ሀገር ሔዱ፡፡ እስከ ዛሬም ድረስ ደብረ ሊባኖስ እየተባለ ይጠራል፤ ስመ ተፋልሶም አላገኘውም፡፡

ዜጋዎ አመል፡-
ዜጋዎ አመል ማለት የአየር ንብረቱ የተመቸ፤ የሚያስደስት፤ ተስማሚና ለኑሮ የሚመች ማለት ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ዜጋዎ አመል ተብሏል፡፡

ምንጭ፡- ልሳነ ደብረ ሊባኖስ፤ ቅጽ-1፤ ቁጥር-1፤ ሠኔ 2006 ዓ.ም.

a washa 1

አሰግድመኝ ቅድስት ማርያም ክፍል ሁለት

 ግንቦት 19 ቀን 2006 ዓ.ም.

በእንዳለ ደምስስ

በካህናቱ መሪነት ከተራራው ሥር ወደምትገኘው ወደ ቀድሞ ዋሻ ቤተ ክርስቲያን ስናመራ፤ ከተራራው አናት ላይ ሆነን ቁልቁል ስንመለከት ትልቅ ወንዝና ደረቱን ለኛ የሰጠ ተራራ ተመለከትን ፡፡ ካህናቱንና ዲያቆናቱን ተከትለን ቁልቁል የሚወስደውንa washa 1 ቀጭን መንገድ ተያያዝነው፡፡ ወንዙ ምን ይባላል አልናቸው ለአንድ አዛውንት “ የማርያም ዥረት ነው የሚባለው” አሉን ፡፡ እንደመቀነት የሚጠማዘዘውን ቀጭን መንገድ እየተከተልን ወደ ዋሻው አፋፍ ደረስን፡፡ ወደ ዋሻው መግቢያ በስተቀኝ በኩል በመጠኑ የጎደጎደ ሥፍራ ይታያል፡፡ ምን እንደሆነ ጠየቅን፡፡ “ከተራራው ሥር እየፈለቀ የሚወርድ ማየገቦ የሚጠራቀምበት ጉድጓድ ነበር፤ (ማየገቦ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ በቦታው ያልነበረው አንድ ዓይና ሌንጊኖስ ከአይሁድ ጋር ለመተባበር ብሎ ኢየሱስ ክርስቶስን በጦር ቢወጋው ውኃና ደም እንደ ለ ፊደል ፈሷል ፡፡ የፈሰሰው ውኃ ማየገቦ ይባላል፡፡) ዋሻው ቤተ መቅደስ ከተደረመሰ በኋላ ደርቋል” አሉን አዛውንቱ፡፡

የተናደው የድንጋይ ክምር አልፈን ወደ ውስጥ ዘለቅን፡፡ ቀድሞ ቅድስትና መቅደስ ሆኖ ሲያገለግል የነበረውን ቤተ ክርስቲያን ለማየት ቻልን፡፡ ቀጥለን በጧፍ ብርሃን እየተመራን ሰፋፊ የዋሻውን ክፍሎች ተመለከትን፡፡ ውስጥ ለውስጥ በሚያስኬደው መንገድ ሽቅብ ወጥተን እንደገና ወደጎን በመሄድ በሌላ መንገድ ከዋሻው ወጣን፡፡

በቀጣይነትም የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ መቅደስ የነበረውን ዋሻ ለማየት ተጓዝን፡፡ ቤተ መቅደሱ መጠነኛ እድሳት ከመፈለግ ውጪ በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ ነው፡፡ ቅኔ ማኅሌቱ፤ ቅድስቱና መቅደሱ በር ቢገጠምላቸው ዛሬም አገልግሎት ሊሰጥ ይችላል፡፡ የጉዶ በረት የቅዱስ ጊዮርጊስ ጽላት ከዚህ ዋሻ መሄዱንም ከካህናቱ ተነገረን፡፡ በገዳሙ ውስጥ 24 የሚደርሱ ጽላት ሲኖሩ፤ በተለያዩ ዘመናት የተጻፉ የብራና መጻሕፍት በብዛት እንደሚገኙም ተገለጸልን፡፡

ይህ የዋሻ ቤተ ክርስቲያን እስከ 1951 ዓ.ም. ድረስ አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበረና በወቅቱ በሥፍራው የነበሩት መምሬ ጥላዬ ስለሁኔታው እንዲህ ይገልጻሉ፡፡ “ሰኔ 21 ቀን 1951 ዓ.ም. ምሽት ወደ ቤተ መቅደስ የምንገባበት ስዓት እስኪደርስ እረፍት ለማድረግ ተኝተን ሳለ ከተራራው የተፈነቀለ ትልቅ ድንጋይ እኛ ወዳለንበት ተምዘግዝጎ በመውረድ ለጥቂት ዳንን፡፡ በሁኔታው ተደናግጥን ቦታ ቀየርን፡፡ ሐምሌ 23 ቀን 1951 ዓ.ም. ተራራው ተንዶ ቅኔ ማኅሌቱ መሉ ለሙሉ ፈርሷል፡፡

a washa 2ዋሻው የተደረመሰበት ዋነኛ ምክንያት እንደሆነ የሚታመነውም በወቅቱ አንዲት ሴት ለአሰግድመኝ ቅድስት ማርያም ገዳም አንድ ጋሻ መሬት ለመገበሪያ ብላ በስጦታ ለግሳ ነበር፡፡ አገልግሎት ሲሰጥ የተወሰኑ ዓመታት እንደተቆጠሩም ሴትየዋ ቃሏን በማጠፍ መሬቱን ከእመቤታችን በመውሰድ ለሌላ ግለሰብ ሰጠችው፡፡ ሴትየዋም ይህንን በማድረጓ ለሰባት ዓመታት በደዌ ዳኛ ተይዛ ስትማቅቅ ቆይታ አርፋለች፡፡ አስከሬኗንም በዚሁ ገዳም አምጥተው ይቀብሩታል፡፡ እመቤታችን ለአባቶች እየተገለጠች “የዚህችን ሴት አስከሬን ከዚህ ቦታ አውጡልኝ፤ ሸተተኝ” እያለች ነግራቸዋለች፡፡ ነገር ግን ተግባራዊ ባለማድረጋቸው ሐምሌ 23 ቀን 1951 ዓ.ም. ዋሻ ቤተ ክርስቲያኑ ሊፈርስ ችሏል፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስም የሴትየዋ ግማሽ አስከሬን ከአንድ ድንጋይ ተጣብቆ ተንጠልጥሎ የነበረ ሲሆን አሁን የት እንደሔደ አይታወቅም በማለት የዋሻውን መደርመስ ምክንያት አወጉን፡፡

ከሁለቱም ዋሻዎች ግራና ቀኝ ተራራው ተቦርቡሮ በድንጋይ የተከደኑ መቃብሮች ይታያሉ፡፡ ከሌሎቹ መቃብሮች ለየት ባለ ሁኔታ በድንጋይ ሳይዘጋ የቀረና በግልጽ የሚታይ የሬሳ ሳጥን ተመለከትን፡፡ ምንድ ነው? ማለታችን አልቀረም፡፡ ለመስዋእት a washa 3የተዘጋጀውን መገበሪያ የበላችው አቃቢት አስከሬን እንደሆነና እንደ ሎጥ ሚስት የጨው አምድ ሆና መድረቋን ነገሩን፡፡ ሳጥኑ በቀላሉ የሚከፈት ሲሆን በአቡጀዲ የተጠቀለለውን አስከሬን ለማየት ቻልን፡፡ አስከሬኑ ሙሉ ለሙሉ አልፈረሰም፡፡

በአካባቢው በርካታ ዋሻዎች እንዳሉ ለማየት ችለናል፡፡ ስንጠይቅም ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ ምእመናን ሱባኤ መያዣ እንደሆኑና በርካታ ዋሻዎች እንዳሉ ተነገረን፡፡

መምሬ ጥላዬ “በግራኝ ወረራ ዘመን ብዙ ታቦታት በዚህ አካባቢ ተሰውረው ተቀምጠው ነበር ሲሉ ሰምቻለሁ” አሉን ፡፡ እውነትም የተዘጉ ዋሻዎች እንዳሉ ተረዳን፡፡ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑን እያስተባበረ የሚያሰራው ወጣቱ አቶ ይስማ “ ይህ ዋሻ እስከ ጅብ ዋሻ ማርያም ይወስዳል አለን፡፡”

jibwasha mariyamትኩረታችንን ሳበውና ጅብ ዋሻ ማርያም የት ነው? ጅብ ዋሻ ለምን ተባለ? ጅብ ዋሻ እንዴት ይኬድ ነበር? በማለት ለጠየቅነው ጥያቅ የጅብ ዋሻ ማርያም የተባለበትንም ምክንያት የቀይት ወረዳ ቤተ ክህነት ሊቀ ካህናት ቀሲስ ብርሃኑ ለገሰ እንዲህ በማለት ያስረዱን ጀመር “ጀብ ዋሻ ማርያም /አሁን ገነት ዋሻ ቅድስት ማርያም ተብሎ ይጠራል/ ከተመሠረተ 620 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ በአካባቢው አንድ ሰው ሞቶ ፍታት ለማድረግ በቤተ ክርስቲያን የነበረውን ከበሮ ወደ ውጪ ወጥቶ ፀሐይ እንዲሞቅ ይደረጋል፡፡

ከአገልግሎት በኋላ ከበሮው ተረስቶ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሳይገባ ይቀራል፡፡ ምሽት ላይ ጅብ መጥቶ ከበሮውን ይደበድባል፤ በአካባቢው የከበሮው ድምጽ ይሰማል፡፡ በወቅቱ የነበሩት ሰዎች ማነው ከበሮ የሚደበድበው? ብለው ቢወጡ ከበሮውን የሚደበድበው ጅቡ መሆኑን ተረዱ፡፡ በዚህ ጊዜ ኧረ ቦታው የጅብ ዋሻ ሆኗል ብለው በመናገራቸው ጅብ ዋሻ ማርያም ተብሎ ሲጠራ ኖሯል፡፡ አሁን ግን ስሙ ገነት ዋሻ እየተባለ የሚጠራና ብዙ ተአምራት እየተደረገበት የሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ነው” ብለውናል፡፡

አለቃ ተሰማ ወልደ ጊዮርጊስ አሁን የ97 ዓመት አረጋዊ ናቸው፡፡ ቀድሞ በደብረ ሲና መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡ ስለ አስገድመኝ ማርያምና ጅብ ዋሻ ማርያም የሚያውቁትን ንገሩን አልናቸው “ከልጅነቴ ጀምሮ የማውቃት aleka tesemaታቦት ነች፡፡ ስዕለት ሰሚ፤ ተአምር አድራጊ በመሆኗ ወደዚህ ቦታ የማይመጣ ክርስቲያን አልነበረም፡፡ ልጅ ስለነበርን “እስከ ጅብ ዋሻ ማርያም ድረስ ውስጥ ለውስጥ የሚያስኬድ መንገድ አለ፡፡” ሲሉ ሰምተን ከጓደኞቼ ጋር ቅብዓ ኑግ የኑግ ጭማቂ በገል አድርገን እያበራን ውስጥ ለውስጥ ሄደናል፡፡ በጣም ያስፈራል፤ በዋሻው ውስጥ ባህር አለ፡፡ ማን እንዳዘጋጀው ለምን እንደተዘጋጀ ባናውቅም በዋሻው ውስጥ ወደ ጅብ ዋሻ ሄደናል” ሲሉ የቦታዋን ታሪክ ነገረውናል፡፡

የደብረ ብርሃን አውራጃ አስተዳዳሪ በኋላም በደርግ ዘመን የወንበሮና ጠቆ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ሊቀ መንበር የነበሩት አቶ ተሾመ በቀለ መሬት ለአስግድመኝ ማርያም ሰጥተዋል፡፡ ስለ አሰግድመኝ ማርያምና ጅብ ዋሻ ማርያም የነገሩን “ልጅ ሳለሁ ወደ ጅብ ዋሻ የሚወስድ መንገድ መኖሩን ሰምተን በጨለማ ጉዞ ጀምረን ነበር ነገር ግን በጣም ስለሚያስፈራ ተመልሰናል፡፡” በማለት የዋሻውን መኖር ነገሩን፡፡

ከአስግድመኝ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ጀርባ ከተራራው አናት ጀምሮ ቁልቁል በቀጭኑ መስመር ሰርቶ የሚወርደው ጸበል መቀበያ ቀጭን ቱቦ ገብቶለት ያለማቋረጥ ይወርዳል፡፡ ሥፍራው በድንጋይ ተከልሏል፡፡ ገዳሙ ሲመሠረት ጀምሮ ጸበሉ እንደነበር አባቶች የሚገልጹ ሲሆን በፈዋሽነቱም ይታወቃል፡፡

በጸበሉ በርካታ አገልጋዮችና ምእመናን የተፈወሱ ሲሆን ዓይን ከማብራት እስከ ዘመናችን በሽታ በኤድስ የተያዙ ሰዎችን ጭምር ተፈውሰዋል፡፡ ወደዚህ ቅዱስ ቦታ መጥቶ ሳይፈወስ የተመለሰ እንደሌለ በእርግጠኝነት መረጃ በመጥቀስ አገልጋዮቹ ይናገራሉ፡፡

አሰግድመኝ ቅድስት ማርያም ገዳም ለ800 ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ነው፡፡ ነገር ግን የዋሻው ቤተ መቅደስ አገልግሎት ካቆመ 55 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ዋሻ ቤተ መቅደሱን ወደ አገልግሎት ለመመለስ የእድሳትና ጥገና ለማከናወን፤ እንዲሁም ዋሻው ቤተ መቅደስ ከፈረሰ በኋላ የተሰራው መቃኞን ወደ ዘመናዊ ሕንፃ ለመለወጥ ኮሚቴ ተዋቅሮ በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል፡፡

በንቡረ ዕድ አባ ገብረ ሕይወት መልሴ የበላይ ጠባቂነት ሁለቱንም ሥራዎች ለማከናወን የመሠረት ድንጋዩ ከተቀመጠበት መስከረም 21 ቀን 2006ዓ.ም. ጀምሮ አዲስ አበባ፤ ጉዶ በረትና፤ አጥቢያው በተዋቀሩ ኮሚቴዎች አማካይነት አዲሱን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት ርብርቡ ቀጥሏል፡፡ ኮሚቴው ከሌሎች ልምድ ካላቸው መሰል የቤተ ክርስቲያን አሰሪ ኮሚቴዎች ጋር በመወያየትና ልምድ በመቅሰም የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር በማዘጋጀት ሕንፃውን በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡

ቤተ ክርስቲያኑ እስከ 4 ሚሊዮን ብር ሊፈጅ ይችላል ተብሎ ተገምቷል፡፡ ካህናቱና ምእመናን ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑን ለመሥራት ቁርጠኛ ሆነዋል፡፡ ንቡረ ዕድ ግን ፍቅር ሳይኖር ቤተ ክርስቲያን መሥራት ተገቢ አይደለም በማለት፤ የተጣላ አስታርቀው ጉልበታቸውን ሳይቆጥቡ ሌት ተቀን በማስተባበር ሕዝቡም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በመሥራት ላይ ናቸው፡፡ ለሥራው ቀና እንዲሆን ከጉዶ በረት ጀምሮ ያለውን የስድስት ኪሎ ሜትር ጥርጊያ መንገድ ምንም አስቸጋሪ ቢሆንም በመሥራት መኪና እንዲገባ ለማድረግ ችለዋል፡፡

ንቡረ ዕድ አባ ገብረ ሕይወት መልሴ መልእክታቸውን ሲያጠቃልሉ “ሕዝቡ በጉልበቱ ከመሥራት ውጪ አሥራት በኩራት የማውጣት ልምድ የለውም፡፡ ማስተማራችንና መቀስቀሳችንን እንቀጥላለን፡፡ በብዙ ነገር ይረዱናል፡፡ የቤተ ክርስቲያኑ ግንባታ መጀመሩን መረጃ የደረሳቸው ከካናዳ፤ ከአሜሪካና ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚገኙ ልጆቻችን ገንዘብ እየላኩልን ነው፡፡ ስለዚህ የዋሻ ቤተ መቅደሱንም ወደ ቀድሞ ይዞታው ለመመለስና የታሪክ ቅርስነቱን ጠብቆ ለማቆየት እንሰራለን፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ ታንጻ አይቼ መሞት ምኟቴ ነው፡፡ እግዚአብሔር ይህንን ምኟቴን ይፈጽምልኛል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ምእመናንም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ያሉ ሁሉ እንዲረዱን ጥሪዬን ነው የማስተላልፈው” ብለዋል፡፡

addis yemeseraw bete

አሰግድመኝ ቅድስት ማርያም ገዳም

 ግንቦት 11 ቀን 2006 ዓ.ም.

በእንዳለ ደምስስ

addis yemeseraw beteበሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በቀይት ወረዳ ቤተ ክህነት ሥር በጉዶ በረት አካባቢ የምትገኘውን ጥንታዊትና ታምረኛዋን ገዳም እንድንዘግብላቸው በተደጋጋሚ ቢሯችን በመምጣትና ስልክ በመደወል ቀጠሮ ያስያዙንን የርዕሰ አድባራት ወገዳማት ዳግሚት ፅዮን አዲስ ዓለም ማርያም ገዳም አስተዳዳሪ ንቡረ ዕድ አባ ገብረ ሕይወት መልሴ ጋር በነበረን ቀጠሮ መሠረት ሚያዚያ 15 ቀን 2006 ዓ.ም. ከሌሊቱ 12፡30 ወደ አሰግድመኝ ቅድስት ማርያም ገዳም ለመጓዝ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በር ላይ እና ላም በረት አካባቢ ከሚገኘው መናኸሪያ በር ተገናኝተናል፡፡

ሰላምታ ተለዋውጠን ንቡረ ዕድ በመስቀላቸው ባርከውን ጉዟችንን ለመቀጠል ስንዘጋጅ ንቡረ ዕድ “ጸሎት እናድርግ” አሉ፡፡ የዘውትር ጸሎት፣ የዕለቱን ውዳሴ ማርያም በማድረስ ጉዞው ተጀመረ፡፡ ሾፌራችን ኢንጂነር መኮንን ለቤተ ክርስቲያንና ለንቡረ ዕድ ካላቸው ፍቅርና አክብሮት የተነሣ ላንድ ክሩዘር መኪናቸውን ለአገልግሎት ይዘው የመጡ አባት ናቸው፡፡ በተገቢው ፍጥነትና ምቹ አነዳድ በሰሜን ሸዋ ይዘውን እየሄዱ ነው፡፡

leke lekawent astedadaryንቡረ ዕድን በረድእነት እያገለገሏቸው የሚገኙት ታናሽ ወንድማቸውን ቀሲስ እንግዳወርቅ መልሴ ድርሳናትንና ገድላትን እንዲያነቡ አዘዟቸውና እያደመጥን በየመሐሉ አቡነ ዘበሰማያት እየተሰጠን እየጸለይን ደብረ ብርሃን ከተማ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ቤት ደረስን፡፡

ብፁዕ አቡነ ኤፍሬምና ንቡረ ዕድ የፍቅርና የአክብሮት ሰላምታ ተለዋውጠው የመጡበትን ሁኔታ አስረዷቸው፡፡ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬምም ጸሎት አድርገው እግዚአብሔር ከእናንተ ጋራ ይሁን ብለው ሸኙን፡፡ ደብረ ብርሃን ከተማ ሲጠብቁን የነበሩትን የቀይት ወረዳ ሊቀ ካህናት ቀሲስ ብርሃኑ ለገሠ እና ጸሐፊያቸውን ይዘን ጉዶ በረት ደረስን፡፡

በጉዶ በረት የሚገኙትን አሰግድመኝ ቅድስት ማርያም የልማት ኮሚቴ አባላት እነ ዲ/ን ይስማን ይዘን ከጉዶ በረት በ6 ኪሎ ሜትር ርቀት ወደምትገኘው አሰግድመኝ ማርያም የአስፋልቱን መንገድ በመልቀቅ የአምስት ቀበሌ ሕዝብ ጉልበቱን ሳይቆጥብ ቆፍሮ ያስተካከለውና አሁንም አስቸጋሪ የሆውን ጥርጊያ መንገድ ተያያዝነው፡፡ ወጣ ገባውን መንገድ ለማለፍና ለመኪናችን ክብደት ለመቀነስ በእግራችን መጓዙን በመምረጥ ከመኪናው ወርደን ተከተልናቸው፡፡

አሰግድመኝ ቅድስት ማርያም ገዳም ስንደርስ የተመለከትነው ሰፊ ሜዳ ላይ በቆርቆሮ የተራች መቃኞ ሆና አገኘናት፡፡ ከአዲስ አበባ ስንነሳ ተነግሮን የነበረው ዋሻ ቤተ ክርስቲያን ስለነበር ግር አለን፡፡ ዋሻ ቤተ ክርስቲያኑን ከማየታችን በፊት መቃረቢያውንና አሁን በመገንባት ላይ የሚገኘውን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን እንድንጎበኝ ተነገረን፡፡ ከመቃኞው አጠገብ መሠረቱ ከፍ በማለት ላይ የሚገኝ ጅምር ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ይታያል፡፡ ይህንን ጅምር ቤተ ክርስቲያን በበላይነት እያስተባበሩ የሚያሠሩት ንቡረ ዕድ መሆናቸውን፤ ከትጋታቸውና የአካባቢው ምእመናን ለንቡረ ዕድ ካለው ከበሬታና ምስክርነት አንጻር ለማወቅ ችለናል፡፡ ግንበኞች ግንባታቸውን ቀጥለዋል፤ እኛም ስለ ቤተ ክርስቲያኑ መጠየቃችንን ቀጠልን፡፡

ንቡረ ዕድ አባ ገብረ ሕይወት መልሴ የገዳሙ የበላይ ጠባቂና ሌሎችም የቤተ ክርስቲያኑ አገልጋዮች ስለገዳሙ መረጃ መስጠታቸውን ቀጠሉ፡፡ ንቡረ ዕድ ርእሰ አድባራት ወገዳማት አዲስ አለም ገደምን በማስተዳደር ፣ደብረ ገሊላ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያንን በማሠራትና በማስተዳደር፣ አሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴና አባ ሳሙኤል ገዳምን በማስተዳደርና አሁንም ከፍተኛ እገዛ በማድረግ፣ሳር አምባ ኪዳነ ምረትን በማራትና እና ሌሎች ገዳማትና አድባራትን በማደራጀትና በማቋቋም የሚታወቁ አባት ናቸው፡፡ የንቡረ ዕድ የመንፈስ ጥንካሬና ትጋታቸውን እያደነቅን ቦታውን እንዴት እንደሚያውቁት ጠየቅናቸው፡፡

“አስግድመኝ ቅድስት ማርያም ገዳምን ከሕፃንነቴ ጀምሮ አውቃታለሁ፡፡ እንደ ጻድቃኔ ማርያም ገዳም ታላቅ በረከት ያላት ቦታ ናት ፡፡ በዚህ ቦታ ሰፊ ጉባኤ ነበር፡፡ ታቦቷም ስዕለት ሰሚና ተአምረኛ መሆኗን አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ከአስፋልት ገባ ያለና መንገዱ ለመኪና አመቺ ባለመሆኑ ምክንያት ማንም አይጎበኛትም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት ታላላቅ ገዳማት አንዷ ናት፡፡ የቀድሞ እውቅናዋን ለመመለስና ታሪኳ ተደብቆ መቅረት የለበትም በሚል ሀሳባችንን ለተለያዩ ሰዎች ስናካፍል እንረዳችኋለን በርቱ አሉን፡፡ ጊዜው ሲደርስ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑን ለመሥራትና ታሪኳን ለማስተዋወቅ ተነሳሳን፡፡” ይላሉ ፡፡

memera telayeመምሬ ጥላዬ በአስግድመኝ ማርያም አካባቢ ተወላጅና ለረጅም ዘመናት ታቦቷን በማገልገል የሚታወቁ የእድሜ ባለጸጋ አባት ናቸው፡፡ ስለ አሰግድመኝ ማርያም የሚያውቁትን እንዲነግሩን ጠየቅናቸው፡፡

“አሰግድመኝ ማለት በሁለት የተለያየ አቅጣጫ እየሄዱ የነበሩ ሰዎች አንድ ሰው ብቻ ማሳለፍ በሚችል ጠባብ ቦታ ላይ ተገናኙ “አሰግድመኝ” – አሳልፈኝ – አሳልፈኝ በመባባል በየተራ ያለፉበት ቦታ ስለሆነ አሰግድመኝ የሚለውን ስያሜውን እንዳገኘ ይነገራል” አሉን መምሬ ጥላዬ፡፡ ንቡረ ዕድም ቀድመው ይህንን ስያሜ ነግረውን ስለነበረ አጠናከሩልን፡፡ አብረውን ያሉ አገልጋዮችም ራሳቸውን በመነቅነቅ በአዎነታ አጸኑልን፡፡

ቀጠሉ መምሬ ጥላዬ “አሰግድመኝ ቅድስት ማርያም ገዳም ከተመሠረተች ከ800 ዓመታት በላይ ያስቆጠረችና ዐፄ ይኩኖ አምላክ እንደመሠረቷት ይነገራል፡፡ ዐፄ ይኩኖ አምላክ ከላስታ ወደ ተጉለት አውራጃ በመምጣት በላስታ የተጀመረውን ፍልፍል ቤተ ክርስቲያን የማነጽ እንቅስቃሴ በዚህም ተግባራዊ አድርገውታል፡፡ በፄ ይኩኖ አምላክ አማካኝነት ፀሐይ ልዳ፤ ልዳ ጊዮርጊስ፤ ብፅዐተ ጊዮርጊስ በተባሉ አባቶች የዋሻ ቤተ ክርስቲያኑ ተፈልፍሎ አገልግሎት መስጠቱን ከአባቶቻችንና ከአያቶቻችን ስንሰማ አድገናል” ይላሉ መምሬ ጥላዬ፡፡

“ለገዳሙ መተዳደሪያ ፄ ይኩኖ አምላክ ሦስት ጋሻ መሬት አንደኛው ጋሻ መሬት መዘዞ ላይ፤ ሁለተኛውን ደግሞ ሞጃና ዳራ ወረዳ ላይ፤ ሦስተኛውን መሐል ተጉለት ላይ ሰጥተው እስከ ደርግ መንግሥት ለውጥ ድረስ ለገዳሙ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል” አሉን መምሬ ጥላዬ፡፡

የቀይት ወረዳ ቤተ ክህነት ሊቀ ካህናት ቀሲስ ብርሃኑ ለገሠ ስለ አሰግድመኝ ማርያም ከተለያዩ መረጃ ምንጮች እንዲሁም ከአባቶች የተረዱትን ሲያጫወቱን፡፡ “አሰግድመኝ ቅድስት ማርያምናkeyet wereda ወንበሮ ኪዳነ ምሕረት በአንድ አቅራቢያ የሚገኙ አድባራት በመሆናቸው አንድ ላይ አገልግሎት ይሰጥባቸው ነበር፡፡ በተለይ በወንበሮ ኪዳነ ምሕረት በርካታ የአብነት ተማሪዎችና መሪ ጌቶች ይገኙ ነበር፡፡ በዚህ ሥፍራም የንባብና የዜማ ትምህርት ሲሰጥበት የቆየ ሲሆን ዛሬም የአገልጋዮቹ ቁጥር ቢቀንስም አገልግሎት እየተሰጠበት ነው፡፡ ድሮ አባቶች አሰግድመኝ ቅድስት ማርያም ቀድሰው እዚያው መክፈልት አይቀምሱም ነበር፡፡ ለቦታው ካላቸው አክብሮት የተነሣ በገዳሙ ዙሪያ ምግብ ስለማይበላ ከቅደሴ መልስ ወንበሮ ኪዳነ ምሕረት እየሄዱ ነበር ምግብ የሚቀምሱት፡፡”

“ገዳሙ ከተመሠረተ በኋላ የፄ ይኩኖ አምላክ ታናሽ ወንድም አባ ሂሩተ አምላክ በምእራብ ጎጃም ዳጋ እስጢፋኖስን ያስተዳድሩ ስለነበር በሀገር እና በህዝቡ ላይ ረሃብ፣ ቸነፈርና ጦርነት ሲከሰት ወደ አሰግድመኝ ማርያም በመምጣት ጸሎት ያደርሱ ነበር፡፡ የመጣውም መቅሰፍት በእመቤታችን ምልጃ በምረት ይመለስ ነበር” አሉን ሊቀ ካህናት፡፡ ሌላም ታሪክ ይነግሩን እንደሆነ ለመረዳት ሌላስ? አልናቸው፡፡

“በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩት ፄ ዘርዓ ያዕቆብ ወደ ጻድቃኔ ማርያም ሲሔዱና ሲመለሱ በአሰግድመኝ ቅድስት ማርያም እረፍት አድርገው ይሄዱ እንደነበር ይነገራል፡፡ እረፍት ያደርጉበት የነበረው ጠፍጣፋ ድንጋይም በአሰግድመኝ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እስከ ቅርብ ዘመን ድረስ ነበር፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ ከፍተኛ ግፍና ጭካኔ በመፈጸም ቀሳውስቱን በማረድ፤ አብያተ ክርስቲያናትን በማቀጠል ከፍተኛ ውድመት ያደረሰው አሕመድ ግራኝ ወደ አካባቢው ሲመጣ ጉልላት ያላቸውንና በግልጽ የሚታዩትን አብያተ ክርስቲያናት ሲያቃጥል አሰግድመኝ ቅድስት ማርያም ገዳም ግን ጉልላት ስላልነበራትና ሊደርስበትም ስላልቻለ ምንም አይነት ዝርፊያና ቃጠሎ ሳይደርሰባት ድናለች” በማለት በዝርዝር አጫወቱን፡፡

የዋሻውን ቤተ ክርስቲያን ማየት ጓጓንና ንቡረ ዕድን ዋሻው ወዴት ነው? አልናቸው፡፡ ንቡረ ዕድም “ እኔ ቁልቁለቱን መውረድ፤ ዳገቱን መውጣት ስለሚያዳግተኝ ካህናቱ ያሳይዋችሁ” ስላሉን ልብሰ ተክህኖ የለበሱና ሌሎች ምእመናን ወደ ዋሻው ይዘውን ሄዱ፡፡

ይቀጥላል

weyenute

በንብና ነብር የምትጠበቀው ሥዕለ ማርያም “ወይኑት”

 ኅዳር 10 ቀን 2006 ዓ.ም. 

በእንዳለ ደምስስ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታላላቅ ገዳማት መካከከል በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ውስጥ የሚገኙት የመርጡለ ማርያም እና ደብረ ወርቅ ገዳማት በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ፡፡ ሁለቱም ገዳማት ጥንት መሥዋዕተ ኦሪት ይከናወንባቸው የነበረና ታላላቅ ታሪካዊ ቅርሶችንም ለትውልድ በማስተላለፍ ረገድ ትልቁን ድርሻ ከያዙት ቅዱሳት መካናት መካከል ይመደባሉ፡፡

መስከረም 29 ቀን 2006 ዓ.ም. በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማርቆስ ጥሪ መሠረት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የሚመራና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የሚገኙበት የልዑካን ቡድን መርጡለ ማርያም ገዳም አዲስ ለሚሠራው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን የመሠረት ድንጋይ ለማኖር፤ እንዲሁም በደብረ ወርቅ ማርያም ገዳም የተገነባውን መንበረ ጵጵስና ለመመረቅና ለዘመናዊ ትምህርት ቤት ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ለማኖር ከሄደው ልዑክ ጋር ተጉዣለሁ፡፡

በመርጡለ ማርያም ገዳም የነበረን ቆይታ አጭር በመሆኑ መረጃዎችን ለማሰባበሰብ የጊዜ እጥረት ስላጋጠመኝ አልተሳካልኝም፡፡ በደብረ ወርቅ ገዳም ቆይታዬ ከቋጠርኳቸው መረጃዎች መካከል ቅዱስ ሉቃስ ከሣላቸውና ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት ቅዱሳት ሥዕላት መካከል በንብና ነብር የምትጠበቀው ሥዕለ ማርያም /ምስለ ፍቁር ወልዳ/ “ወይኑት” ስለተሰኘችው ሥዕል ጥቂት ላካፍላችሁ፡፡ ደብረ ወርቅ ማርያም ገዳምን ላስቀድም፡፡

ደብረ ወርቅ ማርያም ገዳም

ደብረ ወርቅ ማርያም ገዳም በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት በእናርጅና እናውጋ ወረዳ ከአዲስ አበባ 290 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ የኦሪት መሥዋዕት ሲሰዋባቸው ከቆዩት ቅዱሳት መካናት አንዷ ናት፡፡ በተለይም ከ250-351 ዓ.ም. መሥዋዕተ ኦሪት ሲሰዋባት እንደቆየች የጽሑፍ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

የጎጃም አፈ ጉባኤ በነበረው ምሑረ ኦሪት ያዕቆብ አማካይነት መሥዋዕተ ኦሪት ሲሰዋባት የቆየ መሆኑን በገዳሟ የሚገኙ የኦሪት ሥርዓት ማከናወኛ የነበሩ እንደ መቅረዝ፤ ስንና ብርት የመሳሰሉ ቅርሶች ከመመስከራቸውም በላይ በገዳሟ ውስጥ የሚገኘው የቤተ ክርስቲያኗ የታሪክ መዝገብ ያስረዳል፡፡

weyenuteእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ጋር ወደ ምድረ ግብፅ ስትሰደድ ካረፈችባቸው ቅዱሳት መካናት መካከል አንዷ ደብረ ወርቅ መሆኗንም በድርሳነ ኡራኤል ላይ ተጽፎ ይገኛል፡፡ በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያ የነገሡት ወንድማማቾቹ አብርሃና አጽብሃ ክርስትናን እያስፋፉ ከቦታ ቦታ ይዘዋወሩ በነበረበት ወቅት መርጡለ ማርያምን አቅንተው ክርስትናን መሥርተው ወደ ደብረ ወርቅ በመምጣት ከምሁረ ኦሪት ያዕቆብ ጋር ተገናኝተዋል፡፡ ያዕቆብን ክርስትናን አስተምረው የአዲስ ኪዳን ሥርዓትን በመመሥረት “ያዕቆብ ኤጲስ ቆጶስ ዘኢየሩሳሌም ደብረ ወርቅ” ብለው ሾመውታል፡፡

አብርሃና አጽብሃ ደብረ ወርቅ ላይ ቤተ ክርስቲያን ሳይሠሩ ዐረፍተ ሞት ስለገታቸው በእግራቸው የተተካው ዐፄ አስፍሐ ያልዝ በ351 ዓ.ም. ወደ ደብረ ወርቅ በመምጣት ቤተ ክርስቲያኗን አሰርቷል፡፡ የደብረ ወርቅ ማርያም ገዳም በዮዲት ጉዲት በመቃጠሏ በ1372 ዓ.ም. በዐፄ ዳዊት የገንዘብ ድጋፍ አባ ሰርፀ ጴጥሮስ በተባሉ አባት አማካይነት በድጋሚ ተሠርታለች፡፡ ከጊዜ በኋላም ቤተ መቅደሷን ዐፄ ገላውዴዎስ በኖራና ድንጋይ ሲያሠሯት፤ ቅኔ ማኅሌቷ ደግሞ በስክ እንጨት ካለምንም ምሥማር በዐፄ ተክለ ጊዮርጊስ ተሠርታለች፤ በ1963 ዓ.ም. ዐፄ ኃይለ ሥላሴም አሳድሰዋታል፡፡

ቤተ ክርስቲያኗ 44 ቆመብዕሴ/አምድ/፤ የውጪና የውስጥ 11 በሮች፤ 36 መስኮቶች ሲኖሯት የግድግዳ ላይ ሥዕሎቹ ዐፄ ዮስጦስ /1704 ዓ.ም./፤ 1873 ዓ.ም. የንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ልጅ የሆኑት ራስ ኃይሉ አስለውታል፡፡ በቤተ ክርስቲያኗ ዘመናዊ ሙዚየም ውስጥ በርካታ ታሪካዊና ጥንታዊ ቅርሶችም ይገኛሉ፡፡

“ወይኑት” ቅዱስ ሉቃስ የሣላት ሥዕለ ማርያም

ዐፄ ዳዊት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሰቀለበት መስቀል ጋር ወደ ኢትዮጵያ ካመጧቸው የቅዱስ ሉቃስ ሥዕላት መካከል “ወይኑት” የተሠነችው ሥዕል አንዷ ስትሆን ዐፄ ዘርዓweyenute 2 ያዕቆብ ለደብረ ወርቅ ማርያም ገዳም አበርክተዋል፡፡ እስከ ዛሬ ድረስም ተጠብቃ ትገኛለች፡፡ በ1660ዎቹ ዓ.ም. በዐፄ አእላፍ ሰገድ /ፃድቁ ዮሐንስ/ ለወይኑት ማስቀመጫ እቃ ቤት ይሆን ዘንድ ባለ ሁለት ፎቅ ሕንፃ በድንጋይና በኖራ በማስገንባት ጣሪያውን የሣር ክዳን በማልበስ አሠርተውላታል፡፡ ፎቁ ላይ ትናንሽ 8 መስኮቶችም ይገኛሉ፡፡

ሥዕለ ሉቃስ “ወይኑት”ን የሚጠብቁ ነጫጭ ንቦች የሚገኙ ሲሆን ጥቋቁር ንቦቹ ደግሞ ከመስኮቶቹ እየወጡና እየገቡ መመልከት የተለመደ ነው፡፡ ንቦቹ ከሕንፃው መሠራት ጋር እንደገቡ የሚነገር ሲሆን ማሩ እስካሁንም ተቆርጦ አያውቅም፡፡ ወይኑት በዓመት ለሦስት ጊዜያት ሕዝቡን ለመባረክ ወደ ቤተ መቅደስ ትወሰዳለች፡፡ መስከረም 21፤ ጥር 21 እና ነሐሴ 16፡፡ ሥዕሏ ወደ ቤተ መቅደስ ሥትወሰድ ንቦቹ አጅበዋት የሚሄዱ ሲሆን ስትመለስም አብረዋት ይመለሳሉ፡፡ ንቦቹ ሕዝቡን የማይተናኮሉ እንደመሆናቸው በተንኮል ወይም ለሥርቆት የመጣ ሰው ካለ ግን እየነደፉ እንደሚያባርሩ ከዚህ በፊት ከተደረጉት ገቢረ ተዓምራት በመነሳት ይገለጻል፡፡

ወይኑትን የሚጠብቁ ከንቦቹ በተጨማሪ ነብሮችም በሕንፃው ጣሪያ ላይ ይገኛሉ፡፡ ቀን እዚያው ተኝተው የሚውሉ ሲሆን ምሽት ላይ ምግብ ፍለጋ እንደሚወጡ ይነገራል፡፡ በአካባቢው የሚገኙ በጎች ወደ ቤተ ክርስቲያኗ ቅጥር ከገቡ ከነብሮቹ ጋር እንደሚጫወቱና እንደማይተናኮሏቸው የዓይን እማኞች ያስረዳሉ፡፡

የዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ወታደር ሥዕለ ሉቃስ /ወይኑትን/ ለመሥረቅ ሞክሮ ንቦቹ ነድፈው እንዳባረሩት፤ እንዲሁም ዐፄ ዮሐንስ ከደርቡሽ ጋር ባደረጉት ጦርነት ሥዕለ ማርያምን /ወይኑት/ ይዘው ለመዝመት ባደረጉት ጥረት ንቦቹ ወታደሮቻቸውን- በመንደፍ አስጥለዋታል፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዳልሆነ የተረዱት ዐፄ ዮሐንስ ሥዕሏን ወደነበረችበት መልሰው እንደዘመቱ የቤተ ክርስቲያኗ የታሪክ መዝገብ ያስረዳል፡፡ የፋሺስት ኢጣሊያ ጦር ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት የደብረ ወርቅ ማርያም ገዳምን ለመዝረፍ ዕቃ ቤቱን ሰብረው ለመግባት ያደረጉት ጥረት እንዳይሳካ በማድረግ ጠባቂ ንቦቹ ወታደሮቹን በመንደፍ እንዳባረሯቸው መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ 

ይቆየን

የአዲስ ዘመን ቆይታችን

ግንቦት 9 ቀን 2005 ዓ.ም.

በእንዳለ ደምስስ

ጸበል ጸዲቅ /ክፍል ስድስት/
የማኅበሩ ጋዜጠኞች ቡድን ወደ ሰሜን ጎንደር፤ ደቡብ ጎንደር፤ ምእራብ ጎጃምና አዊ ዞን የሚገኙ ቅዱሳት መካናትንና የሀገረ ስብከቶቹን የሥራ እንቅስቃሴ ለመዘገብ ከሚያዚያ 3 -20 ቀን 2005 ዓ.ም. ያደረገውን ጉዞ አጠናቅቆ ተመልሷል፡፡ በዚህም መሠረት በጉዟችን ያሰባሰብናቸውን መረጃዎች አቀናጅተን በድረ ገጻችን ማቅረባችንን እንቀጥላለን፡፡

በጉዟችን ወቅት እየዳሰስናቸው የነበሩትን መረጃዎች “ጸበል ጸዲቅ” በሚል ርዕስ ክፍል አምስት ድረስ ማቃመሳችን ይታወቃል፡፡ ከክፍል ስድስት ጀምሮ ያሉትን ደግሞ እነሆ፡-

የጋዜጠኞቹ ቡድን ከዚህ በፊት ብዙም ትኩረት ያልተሰጣቸውና በዝዋይ ሐይቅ  የሚገኙትን የቅዱሳን አበው የሃይማኖት ፍሬ የሆኑት ገዳማትን ቃኝተን ፤ የሰሜን ጎንደር ቆይታችንን በማጠናቀቅ ወደ ደቡብ ጎንደር በማቅናት ሥራችንን ከአዲስ ዘመን ለመጀመር ወስነናል፡፡

አዲስ ዘመን ከተማ የደረስነው በምሽት ስለነበር የወረዳ ማእከሉ ወንድሞችና እህቶች ተቀብለውን፤ ማረፊያ አዘጋጅተው፤ እግራችንን አጥበው፤ ምግብ እያቀረቡልን በጥሩ መስተንግዶ ተንከባክበውናል፡፡

ጉዟችንን ከጀመርንበት ቀን ጀምሮ በየቀኑ ምሽት ከማረፋችን በፊት ውሏችንን በተመለከተ እያንዳንዱ ጋዜጠኛ ለቡድኑ የቃል ሪፖርት ያቀርባል፡፡ ከሪፖርቱም በመነሳት ውይይት በማድረግ ስህተቶች ካሉም ወደፊት በሚሰራው ሥራ ላይ እንዲስተካከል በመመካከር በቀጣዩ ቀን የሚዘገቡ ሥራዎችን እንከፋፈላለን፡፡

በዚህም መሠረት አዲስ ዘመን ውስጥ ለመሰራት ከታቀዱት ቤተ ክርስቲያናትና ገዳማት መካከል ዜና ማርያም፤ ዋሻ አቡነ እንድርያስ፤ ወይን ዋሻ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፤ ጣራ ገዳም፤ ሊቦ ቅዱስ ጊዮርጊስንና ሐና ማርያምን ለማዳረስ ቡድኑ ጥረት አድርጓል፡፡

ዜና ማርያም ለመዘገብ ዲያቆን ቴዎድሮስ ኃይሉና መንገዱን ከሚመራው የአዲስ ዘመን ወረዳ ማእከል ወንድም ጋር ለአራት ሰዓታት የእግር መንገድ ቢጓዙም ሳይሳካላቸው ተመልሰዋል፡፡ የጉዟቸውን ሂደትና ያጋጠማቸውን ውጣ ውረድ እንዲህ ነበር የገለጸው፡-

ዜና ማርያም የትውልድ አገሯ ጎጃም ሲሆን በአገራችን ጽላቷ በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት በአዲስ ዘመን ከተማ አቅራቢያ ብቻ ይገኛል፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያኗ ለመድረስ የፈለገ ሰው ከአዲስ ዘመን ከተማ ከሦስት ሰዓት እስከ አራት ሰዓት የእግር ጉዞ ማድረግ ግድ ይለዋል፡፡

ገዳሟ ተራራ ጫፍ ላይ የተመሠረተች በመሆኗ ገና ከአዲስ ዘመን ከተማ እግራችን መውጣት ሳይጀምር ነው በርቀት የተመለከትናት፡፡ በመንገድ ላይም ጥንታውያን የሆኑ ሁለት አብተ ክርስቲያናትን የደሪጣ መድኀኔዓለምን ደብር እና ደሪጣ ማርያምን ተሳለምን፡፡

እነዚህን አብያተ ክርስቲያናትን ተሳልመን ሜዳማ መንገዱን ጨርሰን ቀጥ ብሎ ከሩቅ ቆሞ ይጠብቀን ወደ ነበረው ተራራ አመራን፡፡ ተራራውን በእጅና በእግር ከመቧጠጥ ባልተናነሰ ሁኔታና ዐሥር ጊዜ እያረፍን ወጣነው፡፡

ወደ ገዳሟ ስንቀርብ መንገድ የሚመራው ዲ/ን ኀይለሚካኤል ጥቅጥቅ ያለውን ጫካ እያመለከተ “እዚህ ተራራ ሥር የዜና ማርያም ጸበል አለ” አለን፡፡ አያይዞም “ጸበሉ በፈዋሽነቱ ስለሚታወቅ በቅርብ ርቀት የሚያውቁት ሁሉ እየመጡ ከተለያዩ ደዌያት እየተፈወሱ ይገኛሉ” በማለት ምስክርነቱን ሰጠን፡፡

እኛም የጸበሉን ቦታ አልፈን ተራራ ለተራራ እየተጓዝን ከገዳሟ መግቢያ በር ደረስንና “በሰላም ከደጅሽ ያደረስሽን” በማለት ጸሎት አደረግን፤ በዙሪያችን ባሉ ድንጋዮች ላይ ቁጭ ስንል ገዳሟ ተራራ ጫፍ ላይ ያለች እንደመሆኗ መጠን ዙሪያ ገባውን ቁልጭ አድርጋ አሳየችን፡፡

ከገዳሙ አባቶች አንድ አባት አገኘንና የሚበላውንና የሚጠጣውን ቀምሰን፤ ከሀገረ ስብከት የተጻፈልንን ደብዳቤም አሳየናቸው፤ የመጣንበትን ዓላማም አወጋናቸው፡፡ እኒህ አባት ደብዳቤውን ደጋግመው አነበቡት፡፡ አብራቸው የነበረች አንዲት እኅትም በርቀት አሻግራ ደብዳቤውን ከጥግ እስከ ጥግ አነበበችውና “እኔ የሚገርመኝ” በማለት ንግግሯን ጀመረች “እኔ የሚገርመኝ ለምንድነው ይህችን ገዳም ሁሉ የሚፈልጋት? ገድሏን እንመልከተው? የሚሉት” በማለት ተናደደች፡፡ እኛም ቅርሶችን ለመጠበቅ መንፈሳዊ ቅንዓት ሊሆን ይችላል በማለት የመገናኛ ብዙኀንን ጥቅም ለማስረዳት ሞክረን ደብዳቤውን ወደ ያዙት አባት ፊታችንን ዘወር አደረግን፡፡ እኒህም አባት “ልጆቼ እዚህ ድረስ በመምጣት ይህችን ታላቅ ገዳም ለማስተዋወቅ መሞከራችሁ የሚያስመሰግናችሁ ነው፤ ነገር ግን ዜና ማርያም እንዲህ ዓይነት ነገር አትወድም፡፡ ከዚህ በፊትም የገዳሟን ታሪክ ለመዘገብ የመጡ ሰዎች ነበሩ፡፡ ግማሾቹ ዐይናቸው ታውሮ ወደ ገዳሙ መግባት ሲያቅታቸው፤ ሌሎቹ ደግሞ ያለእርሷ ፈቃድ ታሪኳን ዘግበው ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ በመንገድ ላይ በመኪና አደጋ ዐረፉ” አሉን፡፡ አያይዘውም “ባህታውያን በየዓመቱ ወደዚህች ቦታ እየመጡ ታሪኳን ለማንም አትንገሩ ብለው አውግዘውናል” በማለት ለሰሚ ግራ የሆነ ንግግር አሰሙን፡፡ እሳቸው እኔ ብቻ የከለከልኳችሁ አይምሰል በሚመስል ሁኔታ “ኑ ወደ አስተዳዳሪው ቤት ልውሰዳችሁና እርሳቸውም የሚሉትን ስሙ” አሉን፡፡

የአስተዳዳሪው ቤት ለመድረስ ተጨማሪ ከዐሥራ አምስት ደቂቃ ያላነሰ መንገድ መሄድ ግድ ሆነብን፡፡ አስተዳዳሪው ይገኙበታል ወደተባለው ቤት ተጉዘን ሳንደርስ በመንገድ “እናንተ እዚህ ጋር ዐረፍ በሉና አስተዳዳሪው ካሉ ጠይቄ ልምጣ” ብለው ይዘውን የመጡት አባት በመንገድ ትተውን ሄዱ፡፡

ብዙ ታሪክ እንዘግባለን፤ ለምዕመናንም እናስተዋውቃለን ብለን ተስፋ ጥለን የመጣንበትን ነገር አንድም ሥራ ሳንሠራ እየመሸ በመሆኑ ተጨነቅን፡፡ እኚህን አባት በዐይናችን ስንከተላቸው በአካባቢው ከሚገኙ የሣር ጎጆዎች ወደ አንዲ ዘለቁ፤ ብዙም ሳይቆዩ ፈጥነው ተመለሱና “ዛሬ ዕድለኞች አይደላችሁም አስተዳዳሪው ስብሰባ ሄደዋል” አሉን፡፡ እኛም “ታዲያ ምን ይሻላል? እርሳቸው የሚፈቅዱልን ከሆነ እዚሁ እናንተ ዘንድ አድረን ጠዋት እናነጋግራቸው” አልናቸው፡፡ እርሳቸው ግን “እዚህ ብታድሩም አሁን ከነገርኳችሁ ውጪ የምትሰሙት ነገር የለም፤ ፈቃድ ለማግኘት የሚቻለው ከአስተዳዳሪው ወይም ከሰበካው ሳይሆን ሕዝቡ ሲፈቅድ ነው፡፡ የሕዝቡን ፈቃድ ለማግኘት ደግሞ ጊዜ ያስፈልጋል፤ ሳይመሽባችሁ ሂዱ” ብለው መንገድ አመላክተው ሸኙን፡፡

እኛም ዝናብና ጨለማ ሳያገኘን አዲስ ዘመን ለመግባት የደከመ ጉልበታችንን ማንቀሳቀስ ጀመርን፡፡ ነገር ግን እግራችን በፈለግነው ፍጥነት መጓዝ ባለመቻሉ ሊወርድ ካለው በረዶና ከሚያስፈራው ጨለማ ማምለጥ ሳንችል ቀረን፡፡ 

እነ ዲያቆን ቴዎድሮስ ኀይሉ የዜና ማርያምን ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ለመዘገብ ሄደው ያጋጠማቸውን ነበር ያወጉን፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንንና የቅዲሳን አባቶቻችን እንዲሁም እናቶቻችን ታሪክና ገድል እንዳይታወቅ በስመ ውግዘት አፍኖ ማስቀረቱ ማንን ነው የሚጠቅመው? ማውገዝ የሚችለውስ ማነው? የውግዘት ምክንያቶች ምን ምን ናቸው? ምላሽ የሚፈልጉ ጥያቄዎች ናቸው፡፡

ወደ ሊቦ ቅዱስ ጊዮርጊስ የተጓዘው ዲያቆን ታደለ ሲሳይና መንገዱን ከሚመራው ወንድም ጋር ከአምስት ሰዓታት በላይ የእግር ጉዞ ወስዶባቸው ነው ቦታው የደረሱት፡፡ በእለቱ መመለስ ባለመቻላቸው አዳራቸውን እዚያው አድርገው በማግስቱ ሲመለሱ መንገድ ተሳስተው ተንከራትተው ነው አዲስ ዘመን የገቡት፡፡ ማካካሻ ይሆናቸው ዘንድ ግን የሚፈለገውን መረጃ ይዘው መምጣታቸው አስደሳች ነበር፡፡

ይቆየን

1024×768

ቅድስት ቤተ ክርስቲያንንና የቅዱሳን አባቶቻችን እንዲሁም እናቶቻችን ታሪክና ገድል እንዳይታወቅ በስመ ውግዘት አፍኖ ማስቀረቱ ማንን ነው የሚጠቅመው? ማውገዝ የሚችለውስ ማነው? የውግዘት ምክንያቶች ምን ምን ናቸው? ምላሽ የሚፈልጉ ጥያቄዎች ናቸው፡፡

ወደ ዲቦ ቅዱስ ጊዮርጊስ የተጓዘው ዲያቆን ታደለ ሲሳይና መንገዱን ከሚመራው ወንድም ጋር ከአምስት ሰዓታት በላይ የእግር ጉዞ ወስዶባቸው ነው ቦታው የደረሱት፡፡ በእለቱ መመለስ ባለመቻላቸው አዳራቸውን እዚያው አድርገው በማግስቱ ሲመለሱ መንገድ ተሳስተው ተንከራትተው ነው አዲስ ዘመን የገቡት፡፡ ማካካሻ ይሆናቸው ዘንድ ግን የሚፈለገውን መረጃ ይዘው መምጣታቸው አስደሳች ነበር፡፡

እኔና የቴሌቪዥን ክፍል አዘጋጁ ቶማስ በየነ ከቪዲዮ ካሜራ ባለሙያው ሙሉጌታ ቢሆነኝ ጋር በሊቀ መንኮራኩራችን /ሾፌራችን/ ነብያት መንግስቴ አብራሪነት ወደ አቡነ እንድርያስ ዋሻና ወይን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዋሻ ገሰገስን፡፡ መኪና መንገዱን ትተን ጥቂት ወደ ቀኝ እንደታጠፍን ትልልቅ ድንጋዮች አጋጠሙን፡፡

ነብያት መኪናውን አቁሞ “እንዴት በዚህ መንገድ ሂድ ትሉኛላችሁ፤ ለመኪናው አስቡ እንጂ!” በማለት ወርዶ በኩርፊያ ድንጋይ ላይ ቁጭ አለ፡፡

ያለን አማራጭ ለቪዲዮ ቀረጻ የሚያገለግሉንን መሳሪያዎች ከመኪናው ላይ አውርደን በመከፋፈል   ተሸክመን ጉዟችንን ቀጠልን፡፡ ከአርባ ደቂቃ የእግር ጉዞ በኋላ አቡነ እንድርያስ ዋሻ ደረስን፡፡

አቡነ እንድርያስ ገዳም/አቡነ እንድርያስ ዋሻ/፤-

የአቡነ እንድርያስ ገዳም ከአዲስ ዘመን ከተማ በስተሰሜን አቅጣጫ ከተራራ ሥር የሚገኝ የዋሻ ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ በአካባቢው በተለምዶ እንድርያስ ዋሻ በመባል ይታወቃል፡፡

ገዳሙ አራት በሮች ሲኖሩት እያንዳንዳቸው ከአንድ  ወጥ እንጨት ተጠርበው የተሰሩ ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ደረጃና የበሩ መቃን በጣና ደሴት ውስጥ ከሚገኙት ከደብረ ሲና ማርያም፤ ከደብረ ገሊላ ኢየሱስ አቡነ ዘካርያስ ገዳም፤ ማን እንደ አባ ያሳይ መድኀኔዓለም ገዳም፤ . . . ጋር ተመሳሳይነት አላቸው፡፡ ገዳሙ ምንም ዓይነት እድሳት ያልተደረገለት ሲሆን ጥንታዊነቱን ጠብቆ የሚገኝ የዋሻ ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡  

ቀሲስ ቢራራ በላቸው ይባላሉ፡፡ የገዳሙ አገልጋይና ቁልፍ ያዥ ናቸው፡፡ ስለ ገዳሙ ካጫወቱንና በገዳሙ ውስጥ ከሚገኘው ከአቡነ እንድርያስ ገድል ካገኘነው በጥቂቱ ላቅርብላችሁ፡፡

ቦታው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ899 ዓ.ዓ. በአፄ ባዚን ዘመነ መንግስት የተመሠረተና የአካባቢው ሰዎች በእንጨት ምስል ቀርጸው ጣኦት እያመለኩ ቆይተውበታል፡፡ ለ440 ዓመታትም የኦሪት መስዋዕት ሲሰዋበት የነበረ ሲሆን፤ የአካባቢው ነዋሪዎች ዋሻው ውስጥ የሚኖሩ ሁለት ባልና ሚስት  ዘንዶዎችን እርጎ እየመገቡ ያመልኳቸው እንደነበር በገዳሙ ውስጥ የሚገኘው ገድለ አቡነ እንድርያስ ይገልጻል፡፡

በሩን ከፍተው ወደ ውስጥ ሲዘልቁ ሰፊውን ቅኔ ማኅሌት ያገኛሉ፤ ከፊት ለፊት ቅድስትና መቅደሱ፤ እንዲሁም በትልቁ የተሳሉ የአቡነ እንድርያስ ስእሎች ጎልተው ይታያሉ፡፡ በቤተ መቅደሱ ግራና ቀኝ ሰልፋና ደፈር በተባሉ ሰዎች በጥርብ ድንጋይ የተከለሉ ቦታዎች አሉ፡፡ /ሰልፋና ደፈር የዘንዶዎቹ ቀላቢዎች/ እንደነበሩ ገድለ አቡነ እንድርያስን በመጥቀስ አባቶች ይናገራሉ፡፡

ገዳሙ ከክርስቶስ ልደት በኋላም የአካባቢው ሕዝብ ዘንዶዎቹን በማምለክ የቆየ ሲሆን አቡነ እንድርያስ በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በአቡነ ተክለ ሃይማኖት በደቀመዛሙርትነት ተመርጠው ምድረ እንፍራንዝ /የአሁኑ ሊቦ ከምከም ወረዳ አካባቢ/ ሄደው ክርስትና እንዲያስተምሩ፤ ህዝቡንም እንዲያጠምቁ ተልከዋል፡፡

አቡነ እንድርያስ ተልእኳቸውን ለመፈጸም ወደ አካባቢው ሲመጡ ረድአቸውን አቡነ ቶማስን አስከትለው ስለነበር አካባቢውን እንዲቃኙና ለጸሎት የሚመች ቦታ እንዲፈልጉ ላኳቸው፡፡ ይህ ዋሻ በአቡነ እንድርያስ ረድእ በነበሩት በአቡነ ቶማስ አማካይነት የተገኘ ሲሆን ዘንዶዎቹን ሲመለከቱ በመፍራታቸው ቦታው እንደማይሆናቸውና የዘንዶዎቹን አስፈሪነት ለአቡነ እንድርያስ ይገልጹላቸዋል፡፡ አቡነ እንድርያስም “በእግዚአብሔር ኃይል እናሸንፋቸዋለን” በማለት መጥተው በመስቀላቸው በማማተብ በእግዚአብሔር ስም ይገስጻቸዋል፡፡ በዚህ ቅጽበት አቡነ እንድርያስ የያዙት መስቀል ከመሬት ወድቆ የቀኝ በኩል ክንፉ በመሰበሩ ወደ እግዚአብሔር ቢጸልዩ የእግዚአብሔር መልአክ መጥቶ እንደነበረ አድርጎ ሰጥቷቸዋል፡፡ ከዘንዶዎቹ አንዱ ከአካባቢው ማዶ ተምዘግዝጎ ግራርጌ ጉበያ ማርያም ከሚባል ቦታ ላይ ወድቋል፡፡ አንደኛው ግን እስከ ዛሬ ድረስ የደረሰበት ባይታወቅም ወደ ዋሻው ውስጠኛ ክፍል ገብቶ እንደቀረ ይነገራል፡፡

አቡነ እንድርያስ ገዳሙን አቅንተው የአካባቢው ምእመናንን ክርስትና በማስተማር ታላቅ ተድጋሎ የፈጸሙበት ቅዱስ ስፍራ ነው፡፡ ወደ ገዳሙ በተአምራት አብረዋቸው የመጡ አራት በግምት አንድ ሜትር ቁመት ያላቸውና ከ20 እስከ አሥራ አምስት ሣንቲ ሜትር ስፋት ያላቸው ድንጋዮች መካከል ሁለቱ በደወልነት አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ ሲደወሉ ወፍራምና ቀጭን ድምጽ ስለሚያወጡ የወንድና የሴት ደወሎች ይባላሉ፡፡ በአገልግሎት ወቅት ዋሻው ድምጽ እያስተጋባ ስለሚያስቸግር አቡነ እንድርያስ ገስጸውት እስከ ዛሬ ድረስ ዋሻው ምንም አይነት ድምጽ አያስተጋባም፡፡

በገዳሙ ውስጥ ዜና ማርያም የተባለችው ቅድስት እናት ለ25 ዓመታት በጸሎት ተወስና ቆይታበታለች፡፡ ከእንጨት ተፈልፍሎ በቁመቷ ልክ በተሰራ ገንዳ ውስጥ ገብታ የገንዳውን ግራና ቀኝ በደረቷ አቅጣጫ በመብሳት በጠፍር በማሰር ትጸልይ ነበር፡፡/ ዜና ማርያም ትጸልይበት የነበረው የእንጨት ገንዳ ዛሬም በገዳሙ ውስጥ ይገኛል፡፡/

በገዳሙ ውሰጥ በጥንቃቄ ጉድለት እየተበላሹ የሚገኙት ቅርሶች እንደ አልባሌ እቃዎች ተጥለዋል ማለት ይቻላል፡፡ ዘንዶው እርጎ ይጠጣበት የነበረው ገንዳ፤ የዜና ማርያም መጸለያ ገንዳ፤ በእንጨት የተሰራ የኦሪት መሰዊያ፤ የመስዋእተ በግዕ ስጋ ማስቀመጫ፤ የደሙ ማኖሪያ፡ አፄ ዘርዓያዕቆብ ለገዳሙ ከሰጧቸው 6 ነጋሪቶች መካከል ሁለቱ፤  ብዛት ያላቸው የሰው አጽሞች ይገኛሉ፡፡ ከአጽሞቹ መካከል አንዱ ሙሉ ለሙሉ ሳይፈርስ ከራስ ቅሉ እስከ እግር ጥፍሩ በዘመናዊ ሳጥን ተደርጎ ከላይ በመስታወት ታሽጎ ይታያል፡፡ የአጽሞቹን እድሜ መገመ,ት እንደማይቻልና ቀድሞም እንደነበሩ ቀሲስ ቢራራ በላቸው ይገልጻሉ፡፡

የአቡነ እንደርያስ የእጅ መስቀል በገዳሙ ውስጥ በቅርስነት ተጠብቆ ይኖር እንደነበር፤ ብዛት ያላቸው ምእመናን በመስቀሉ ታሽተው ከያዛቸው ደዌ ይድኑ እንደነበር ቀሲስ ቢራራ በላቸው የአይን ምስክር እንደሆኑ ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን በቅርቡ በአንድ ግለሰብ የአቡነ እንድርያስ መስቀል መዘረፉንና የግለሰቡ ማንነት ታውቆ ክስ ተመስርቶበት በቀጠሮ ላይ እንደሚገኝ የአቡነ እንድርያስን ዋሻ ቆይታችንን አጠናቀን ስንወጣ የገዳሙ አበምኔት የክሱን ሁኔታ ለመከታተል ከሔዱበት ሲመለሱ አግኝተናቸው ነግረውናል፡፡

ገዳሙ ለስርቆት የተጋለጠ በመሆኑ የገዳሙ ጥንታዊ መጻሕፍት ተሰብስበው በአንድ ታማኝ በሆነ ግለሰብ ቤት ውስጥ እንዲቀመጥ መደረጉንም ቅርሶቹን ለማየት በጠየቅንበት ወቅት ከተሰጠን ምላሽ ለማወቅ ችለናል፡፡ የብራና መጻሕፍት ገድለ ሰማእታት፤ ስንክሳር የአመት /2/፤ ጸሎተ እጣን፤ ግንዘትና . . . ሌሎችም ንዋያተ ቅዱሳት በዚሁ ታማኝ ነው በተባለው ሰው እጅ ላይ ይገኛሉ፡፡ በየአመቱም ቆጠራ እንደሚካሔድ በስፍራው ከነበሩት አባቶች ተገልጾልናል፡፡

የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሀብቶችና ቅርሶች እሰከ መቼ በሰዎች እጅ ይቆያሉ? በተለያዩ ምክንያቶች ቢሰወሩ ተጠያቂው ማነው? መፍትሔ ይሻልና ሀገረ ስብከቱም ሆነ ምእመናን ትኩረት ሊሰጡት ይገባል፡፡

ምእመናን ተጠምቀው ከተያዙበት ደዌ የሚፈወሱበት ጸበል ከገዳሙ በስተ ደቡብ ይገኛል፡፡ ጸበሉ በምንጭነት የሚፈልቅ ሲሆን ምንም አይነት ከለላ ስላልተደረገለት ለከብቶችና ለአራዊት የተጋለጠ ነው፡፡

የኢሱስ፤ የቅዱስ ሚካኤልና የአቡነ እንድርያስ ታቦታት፤ እንዱሁም የአቡነ እንድርያስ መቃብር በዚሁ ዋሻ ቤተ መቅደስ ውስጥ ይገኛሉ፡፡

አቡነ እንድርያስ ግንቦት 20 ቀን ወደ ገዳሙ እንደገቡና ጳጉሜ 3 ቀን እንዳረፉ ገድላቸው የሚገልጽ ሲሆን ዓመተ ምሕረቱን ግን አይናገርም፡፡ በዚህም መሠረት ግንቦት 20 ቀን በየዓመቱ በገዳሙ በዓላቸው ይከበራል፡፡

ገዳሙ ምንም ዓይነት የገቢ ምንጭ የሌለው ሲሆን አገልጋዮቹ የራሳቸውን የእርሻ መሬት እያረሱ በሚያገኙት ይተዳደራሉ፡፡

ተሰጣቸው መልስ ከስርዓተ ቤተ ክርስስቲያን ውጪ የሆነና በግለሰቦች በጎ ፈቃድ ላይ ብቻ የተመሰረተ ነበር፡፡ የቤተ ክርስቲያኑ ታሪክ፤ የዜና ማርያም ታሪክና ገድል በምስል ወድምጽ ወይም በፎቶ ግራፍ መውሰድ መልከሉን፤እንዲሁም በባህታዊያንና በአንድ አባት መወገዙን ተነግሯቸዋል፡፡ ለማሳመን ያደረጉት ጥረትም ሳይሳካ ቀረ፡፡ ሳይሳካላቸው መቅረቱ ብቻ ሳይሆን ወደ አዲስ ዘመን እየተመለሱ በረዶ በቀላቀለ ዝናብ መመታታቸው ደግሞ የሚያበሳጭ ነበር፡፡

ወይን ዋሻ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም፡-

Normal 0 false false false EN-US X-NONE X-NONE

አትማረኝ ዋሻ

ሚያዚያ 18 ቀን 2005 ዓ.ም.

በእንዳለ ደምስስ

/ጸበል ጸዲቅ ክፍል አምስት/

“አትማረኝ” እያሉ ስለ ጸለዩ አባት የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት በትምህርታቸው እያነሱ በምሳሌነት ከሚጠቅሷቸው ትምህርቶች አንዱ ነው፡፡ ከጣና ሐይቅ ጉዞ ከቃረምኳቸው መረጃዎቼ መካከል ለዛሬ  በጸበል ጸዲቅ ጽሑፌ አትማረኝ ዋሻንና ታሪኩን በጥቂቱ ላስተዋውቃችሁ፡፡

አትማረኝ ዋሻ በጣና ሐይቅ ደሴቶች መካከል ከሚገኙ ገዳማት መካከል ከማን እንደ አቡነ ያሳይ መድኀኔዓለም አንድነት ገዳም በስተ ምእራብ አቅጣጫ የጣና ሐይቅን ጉዞ ከገታው አንደ ተራራ ሥር የሚገኝ ዋሻ ነው፡፡

ከብርጊዳ ማርያም ገዳም ወደ ማን እንደ አባ ያሳይ መድኀኔዓለም ገዳም በጀልባ እየተጓዝን አብረውን ከነበሩት ደብረ ሲና ማርያም ገዳም መነኮሳት መካከል አንዱ አባት ጣታቸውን ወደ ምእራብ አቅጣጫ ወደ አንድ ዋሻ እያመለከቱ፡፡ “ያ ተራራ ይታያችኋል? ከተራራው ሥር የሚገኘው ዋሻስ?!” አሉን፡፡

ሁላችንም አባታችን በጣታቸው ወደሚጠቁሙት አቅጣጫ ተመለከትን፡፡ በርቀትም ቢሆን ዋሻውን ተመለከትን፡፡ የጋዜጠኝነት ጆሮዎቻችን ተቀሰሩ፡፡ለመስማት ጓጓን፡፡

“በዚህ በምትመለከቱት ዋሻ ውስጥ ለብዙ ዘመናት አንድ አባት የጸሎት በዐት አድርገውት “አትማረኝ” እያሉ የጸለዩበት ቦታ ነው” አሉን፡፡

ይህንን ታሪክ ማን እንደ አባ ያሳይ መድኀኔዓለም ገዳም እንደደረስን ለማጣራት ጥረት ያደረግን ሲሆን የገዳሙ አባቶች የአቡነ ያሳይ ገድልን መሠረት አድርገው የታሪኩ ትክክለኛነት አረጋግጠውልናል፡፡ ታሪኩንም አሳጥሬ ላቅርብላችሁ፡፡

አቡነ ያሳይ ከሰባቱ የአቡነ መድኀኒነ እግዚእ ደቀመዛሙርት መካከል አንዱ ናቸው፡፡ ወደ ጣና ደሴት ከአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ እና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ጋር በመሆን በጸሎት ይተጉ እንደነበር ገድላቸው ይናገራል፡፡ ከእግዚአብሔር በተሰጣቸውም ጸጋ በጣና ሐይቅ ላይ እንደ ጀልባ የሚጓዙበት አንድ ጠፍጣፋ ድንጋይ /ዛሬም ድረስ በገዳማቸው ውስጥ ይገኛል፡፡/ በጣና ደሴት ላይ ለአገልግሎት በመፋጠን ላይ እያሉ ዛሬ አትማረኝ ዋሻ ተብሎ ወደሚጠራው አካባቢ ሲደርሱ አንድ አባት ዋሻው ውስጥ “አትማረኝ – አትማረኝ- አትማረኝ” እያሉ ሲጸልዩ ያገኟቸዋል፡፡

አቡነ ያሳይ በሰውዬው ጸሎት በመገረም ቀርበዋቸው “አባቴ ምን ዓይነት ጸሎት ነው የሚጸልዩት?” አሏቸው፡፡

“አባቴ እንደ እርስዎ ያሉ አባት መጥተው “አትማረኝ” እያልክ ጸልይ ብሎኝ ነው በማለት መለሱላቸው፡፡

“እንዲህ ዓይነት ምክር የሚመክር ጠላት ዲያብሎስ ነው፡፡ ከዛሬ ጀምረው “ማረኝ” እያሉ ይጸልዩ በማለት አቡነ ዘበሰማያትን አሰተምረዋቸው ይሄዳሉ፡፡

አትማረኝ እያሉ ይጸልዩ የነበሩት አባትም “ማረኝ” እያሉ መጸለያቸውን ቢቀጥሉም ብዙ መግፋት ሳይችሉ ጸሎቱ ይጠፋባቸዋል፡፡ ጸሎቱን ያስጠኗቸው አባት አቡነ ያሳይ ርቀው ሳይሄዱባቸውም በውኃ ላይ እየተራመዱ በመከተል ይደርሱባቸዋል፡፡

“አባታችን ያስጠኑኝ ጸሎት ጠፋብኝ፡፡ እባክዎ ያስተምሩኝ” ይሏቸዋል፡፡

አቡነ ያሳይ የእኚህ አባት መብቃት ተመልከተው “አባቴ እግዚአብሔር የልብ ነውና የሚመለከተው እንዳስለመዱት ይጸልዩ የእርስዎ ይበልጣል” ብለዋቸው ይሔዳሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ቦታው አትማረኝ ዋሻ ተብሎ ተጠርቷል፡፡

ይቆየን
 
tana desate

ቤተ ክርስቲያን ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ

ሚያዚያ 15 ቀን 2005 ዓ.ም.

በእንዳለ ደምስስ

ጸበል ጸዲቅ /ክፍል አራት/

tana desateከጎንደር ከተማ በጎርጎራ ወደብ አድርገን ልንቃኛቸው በመረጥናቸው አምስት የጣና ሐይቅ ገዳማትን ለመዘገብ የተነሳነው ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ነው፡፡ የጀልባ ላይ ጉዞ አድርጌ አላውቅም፡፡ ነገር ግን ቅዱሳን አበውን ያፈሩ፤ በጾም በጸሎት፤ በተጋድሎ የጸኑባቸው ገዳማትን በረከት ለማግኘት፤ ታሪካቸውን ለመቃኘት ቸኩያለሁ፡፡ የጋዜጠኞቹ ቡድን በአንድነት ሆነን የ64 ኪሎ ሜትሩን መንገድ ተያያዝነው፡፡

አመሻሽ ላይ ጎርጎራ ወደብ ደረስን፡፡ የጠዋት ጉዟችንን ለማመቻቸት እንዲረዳን ወደቡ ላይ ከሚገኘው የደብረ ሲና ቅድስት ማርያም ገዳም የአባቶችን ፈቃድ በመጠየቅ የምንፈልገውን መረጃ ማሰባሰባችንን ቀጠልን፡፡ በምፈልገው አቅጣጫ ጥያቄዎችን እየጠየቅን፤ ምላሽ ከአባቶች እየተሰጠን አመሸን፡፡ አዳራችንንም እዚያው አደረግን፡፡

በጠዋት ተነስተን አንጋራ ተክለ ሃማኖት ገዳምና ብርጊዳ ቅድስት ማርያም ገዳምን ቃኝተን  ማን እንደ አባ ያሳይ መድኀኔዓለም አንድነት ገዳም ስንደርስ በመምሸቱ አስፈላጊ ናቸው ያልናቸውን መረጃዎች ስናሰባስብ አደርን፡፡ በማግስቱም ደብረ ገሊላ ኢየሱስ ወአቡነ ዘካርያስ ገዳም ዘልቀን እጀበራ ቅድስት ማርያም ገዳም ላይ ከተምን፡፡

የዛሬው የጸበል ጸዲቅ ጽሑፌ እንደ ሰሞኑ ታሪክ ላይ ያተኮረ አይደለም፡፡ በጉዟችን የቃኘናቸው የአባቶቻችን አሻራ ያረፈባቸው፤ እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ የስልጣኔ ጫፍ የደረሰ አእምሯቸው ውጤቶች በነበሩ ነገር ግን የተፈቱና ለመፈታት በቋፍ ላይ የሚገኙት ጥንታዊ የጣና ደሴት በረከቶችን እንቃኝ ዘንድ ወደድኩ፡፡ ክፍል አራት ጸበል ጸዲቅን ተቃመሱ፡፡

አንጋራ አቡነ ተክለ ሃማኖት ገዳም፡-
angawa tekelehaymanoteአንጋራ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ለመድረስ ከደብረ ሲና ማርያም ገዳም የ20 ደቂቃ በጀልባ  የጣና ሐይቅን ማቋረጥ ይጠይቃል፡፡ በደብረ ሲና ማርያም ገዳም አገልጋይ የሆኑት ሁለት መነኮሳት አባቶች ወደ ማን እንደ አባ አቡነ ያሳይ መድኀኔዓለም ገዳም ስለሚሔዱ እንድናደርሳቸው ስለጠየቁን አብረን ለመጓዝ ተስማምተን ጸሎት አድርገውልን የጣና ሐይቅ የጀልባ ላይ ጉዞ ተጀመረ፡፡ 

አንጋራ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ስንደርስ ያልጠበቅነው ነገር ገጠመን፡፡ በድንጋያማው ደሴት ላይ ያረፈው ቤተ መቅደስ በዝምታ ተውጧል፡፡ አፍ አውጥቶ “የሰው ያለህ” በማለት የሚጣራ ይመስላል፡፡ በአካባቢው ሰው ዘር ያለ አይመስልም፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ስንጠጋ አንዲት ደሳሳ ጎጆ ቤት ደጃፍ ላይ አንድ አባት እድሜ ተጭኗቸው ኩርምት ብለው ተቀምጠዋል፡፡ ዓይነ ሥውር ናቸው፡፡ ዘጠና ዓመታቸው ሲሆን ወደ አንጋራ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ከመጡ 25 ዓመታታን አስቆጥረዋል፡፡

“አባታችን ስለዚህ ገዳም ታሪክና አሁን ያለበት ሁኔታ የሚነግረን ሰው እናገኝ ይሆን?” የሁላችንም ጥያቄ ነበር፡፡

“የምን ሰው?! ማን አለ ብላችሁ ነው?! ገዳሙ ሊፈታ ምንም አልቀረውም፡፡ እስቲ ወደ ታች ወረድ ብላችሁ ገበዙን ፈልጉት” አሉን፡፡

ውስጤ መረበሽ ጀመረ፡፡ ማንን እንጠይቅ? የኢየሩሳሌምን ጥፋት አታሳየኝ ያለውና እንደ ቃሉም የተፈጸመለት አቤሜሌክን አስታወስኩ፤፤ ከጓደኞቼ ገንጠል ብዬ የሚተናነቀኝን የቁጭት እንባ አፈሰስኩ፡፡ ቤተ መቅደሱ ላይ ዓይኖቼ እንደተተከሉ አባቶችን አሰብኩ፡፡ አባቶቻችን ይህንን ገዳም ሲገድሙት ምን ይመስል ነበር? በገዳማውያን አባቶች ተሞልቶ፤ መላእክትን መስለው እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑበት፤ በጸሎት አጋንንት ድል ሲነሱበት የነበረ፤ ቃል ኪዳን የተቀበሉበት ሥፍራ ምነው ዛሬ ነጠፈ?! ራሴንና ይህንን ትውልድ ተጠያቂ ከማድረግ ሌላ ምን ማለት እችላለሁ? አባቶቻችንን መስለን ያልተገኘን፤ የአባቶቻችን አደራ መሸከምም ሆነ መወጣት ያቃተን ትውልዶች እንደሆንን ተሰማኝ፡፡ ብቻዬን መሆን አማረኝ፡፡ ነገር ግን አልቻልኩም እንደተከፋሁ ከጓደኞቼ ጋር ተቀላቀልኩ፡፡ እንደ እኔው በዝምታ ቆዝመዋል፡፡ 

የቤተ ክርስቲያኑን ገበዝ ከእኛ ጋር ከደብረ ሲና ቅድስት ማርያም ገዳም የመጡት መነኮሳት አባቶች ፈልገው ይዘዋቸው መጡ፡፡ በእርግና እድሜ ላይ ነው የሚገኙት፡፡ ደብዳቤያችንን አሳይተን መረጃ እንዲሰጡን ጠየቅናቸው፡፡ ታሪኩን በተደራጀ መልኩ መናገር ተሳናቸው፡፡ ቅዱሳን አባቶቻችን ቅድስት ቤተ ክርስተቲያንን ለትውልድ ይተላለፍ ዘንድ የከፈሉት መስዋእትነት እንደዋዛ ፈዛዛ ማለፉ ነው፡፡ ገዳሙ የእምነታችን መገለጫ የሆኑትን የአባቶቻችንን ታሪክና ቅርሶችን ታቅፎ ዝምታን መምረጡ ለምን ይሆን? ለመሆኑ ተጠያቂው ማነው? ውስጤን ሰላም ነሳኝ፡፡ 

አገልጋዮቹ ከሦስት አይበልጡም፡፡ ቅዳሴ አይታሰብም፡፡ ከቀናቸው ኪዳን ያደርሳሉ፡፡ ካልሆነም በግል ጸሎት ይተጋሉ፡፡ የሚተካቸው የለም፡፡ ይህ ትውልድ ርቋቸዋል፡፡ አባቶቻችንን መምሰል፤ በቃልኪዳናቸው መጠቀምን ዘንግተን ይሆን? የወደፊት የእኛም ሆነ የተፈቱ ገዳማት እጣ ፈንታ ምን ይሆን? የቃረምነውን መረጃ ቋጥረን፤ በሐዘን አንገታችንን እንደደፋን ወደ ጀልባችን አመራን፡፡ ጉዞ ወደ ብርጊዳ ቅድስት ማርያም ገዳም፡፡

ብርጊዳ ማርያም ገዳም፡-
ወደ ብረጊዳ ማርያም ገዳም እያመራን ደሴት ስንመለከት ይህ ምንድነው ማለታችን አልቀረም፡፡ አብረውን ያሉት አባቶች ከእኛ የተሻለ መረጃ ስላላቸው የሰቀላ ሚካኤልን፤ የቅዱስbergeda mariyame ጊዮርጊስንና የእመቤታችን ማርያም የጥንት ገዳማትን በጣታቸው እያሳዩን አለፍን፡፡ ሦስቱም ገዳማት ተፈትተው ዛሬ ሰው አልባ ሆነዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያኖቹም ፈርሰዋል፡፡ በምሰማው ነገር ታመምኩ፡፡ 

ብርጊዳ ማርያም ገዳምን  ከአንጋራ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ብዙም የተሻለ ነገር አለው ለማለት አያስደፍርም፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ ክብ ሲሆን ዙሪያው ከመሠረቱ ጀምሮ አንድ ሜትር ያህል ከፍታ በድንጋይ ተገንብቷል፡፡ ቀሪው ክፍል በቀጫጭን ሸንበቆ የተሰራ በመሆኑ ለመፍረስ እየቃጣው ነው፡፡ ሕመሜ አገረሸ፡፡ እስኪበቃኝ አለቀስኩ፡፡ ለቅሶዬ ግን መፍትሔ ሰጪ አልነበረም፡፡ የቀድሞው ቤተ ክርስቲያን በመብረቅ ተመትቶ በመቃጠሉ ፍርስራሹ ብቻ ለታሪክ ነጋሪነት ተቀምጧል፡፡ አገልጋዮቹ ከአምስት አይበልጡም፡፡ አነስተኛ የእርሻ መሬት ከደሴቱ ወዲያ ማዶ ስላላቸው እያረሱ ይተዳደራሉ፡፡ ተተኪ ግን የላቸውም፡፡ ያገኘነውን አነስተኛ መረጃ ቋታችን ውስጥ አስገብተን ጉዟችንን ማን እንደ አባ ያሳይ መድኀኔዓለም አንድነት ገዳም ቀጠልን፡፡ አዳራችንንም እዚያው ለማድረግ ተስማማን፡፡ የማን እንደ አባ ገዳምን ሁኔታ ስመለከት ደግሞ ሕመሜ በመጽናናት አስታገስኩት፡፡

ዛሬ ስለ ማን እንደ አባ ያሳይ መድኀኔዓለም አንድነት ገዳም የምነግራችሁ አይኖረኝም፡፡ አንድ ነገር ብቻ ጠቁሜያችሁ ልለፍ፡፡ ገዳሙ ለሌሎች ገዳማት ምሳሌ ሊሆን የሚችልና ትክክለኛ የገዳም ገጽታና ሥርዓት የተላበሰ ስለመሆኑ ካየሁትና ከሰማሁት ነገር ተነስቼ መመስከር እችላለሁ፡፡ እግዚአብሔር ቢፈቅድ በሌላ ጊዜ እንመለስበታለን፡፡

በማግስቱ በጠዋት ወደ ደብረ ገሊላ ኢየሱስ ወአቡነ ዘካርያስ አንድነት ገዳም የአንድ ሰዓት የሐይቅ ላይ ጉዞ ተጀመረ፡፡

ደብረ ገሊላ ኢየሱስ ወአቡነ ዘካርያስ አንድነት ገዳም እስካሁን ካየናቸው ገዳማት በተራራማነቱ ለየት ይላል፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ እየወጣን ተግባር ቤት አካባቢ ሁለት ሰዎችን አገኘን፡፡ የመጣንበትን አስረድተን መረጃ እንዲሰጡን ጠየቅናቸው፡፡ አገልጋዮቹ ሁሉም ወደ ሞፈር ቤት መሄዳቸውን ነገሩን፡፡ እነሱም የቤተ ክርስቲያኑን አባቶች የሚራዱ የአካባቢው ገበሬዎች እንደሆኑ ገለጹልን፡፡

ከመካከላቸውም አንዱ አባት ስለቤተ ክርስቲያኑ የሚያውቁትን ታሪክ ያጫወቱን ዘንድ ፈቃዳቸው ሆነ፡፡ ገዳሙ ደርቡሽ ጎንደርን በወረረበት ወቅት ገዳማትን ሲያፈርስ የየገዳማቱ ቅርሶች መሸሸጊያ ሆኗል፡፡ ደርቡሽ ሊደርስባቸው ካልቻላቸው ገዳማት አንዱ ነው፡፡ በገዳሙ በጾምና ጸሎት በመትጋት የዘጉ አባቶች መኖራቸውንና ምግባቸውንም ወደ ባእታቸው እንደሚወስዱላቸው፤ ለማንም እንደማይታዩ፤ አንዳንዴም ለሳምንት ያህል የተወሰደላቸው ምግብ ሳይቀምሱት እንደሚያገኙት ነገሩን፡፡

ያስፈልጋሉ ያልናቸውን መረጃዎች ከመሰብሰብ ወደ ኋላ አላልንም፡፡ እያንዳንዱ ጉዞ ሕመም አለው፡፡ የገዳማት የወደፊት እጣ ፈንታ ምን ይሆን እንድንል አስገድዶናል፡፡ የእያንዳንዳችን ሕሊና በምናያቸውና በምንሰማቸው ነገሮች መታመሙን ቀጥሏል፡፡

እጀበራ ማርያም ገዳም፡-
እጀበራ ቅድስት ማርያም ገዳም ለመሄድ ተነስተናል፡፡ እዚህ ደግሞ ምን ይገጥመን ይሆን?  ፍርሃት ፍርሃት አለኝ፡፡

እጀበራ ቅድስት ማርያም ገዳም ስንደርስ ቤተ ክርስቲያኑ ፈርሶ ግንባታው ተጀምሯል፡፡ ግንበኞች ድንጋይ ይከሰክሳሉ፤ ገሚሶቹ በአቅራቢያው ከሚገኘው አካባቢ በጀልባ ተጭኖ የመጣውን ድንጋይ ያራግፋሉ፡፡

ከአንዲት አነስተኛ ተግባር ቤት ውስጥ አንድ አባት አገኘን፡፡ አንድ ዛፍ ጥላ ሥር ሁላችንም ተሰባሰብን፡፡

ለተወሰኑ ደቂቃዎች ሁላችንም በዝምታ ተዋጥን፡፡ አባታችን ዝምታውን ሰብረው “ለምን መጣችሁ?” አሉን በየተራ እያንዳንዳችንን አየቃኙ፡፡

የመጣንበትን አስረዳን፡፡ ደስ አላላቸውም፡፡

እያለቀሱ የገዳማትን ችግሮች እየዘረዘሩ ይናገራሉ፡፡ በሚናገሯቸው ቃላቶች እያንዳንዳችን እየታመምን ነው፡፡ ማሳረጊያችንም በህመም ሊደመደም ሆነ፡፡

ከሃያ ዓመታት በፊት በዚሁ ገዳም ለሦስት ዓመታት መኖራቸውንና ገዳሙ ሊፈታ እንደሆነ በመስማታቸው ይህንን ለመታደግ ወደ ገዳሙ ከመጡ ገና ሦስት ወራት ብቻ እንደሆናቸው፤ የአቅማቸውን ያህል ጥረት በማድረግ ወደ ቀደመ ክብሩ ለመመለስ እየተፍጨረጨሩ እንደሚገኙ ገለጹልን፡፡ ከገዳሙ አቅራቢያ የሚገኙ ነዋሪዎችን በማስተባበር ቤተ ክርስቲያኑን በማሰራትና አንዳንድ የልማት ሥራዎችን እያስጀመሩ መሆናቸውን አስረዱን፡፡

ገዳሙ ምንም ዓይነት የልማት እንቅስቃሴ አይታይበትም፡፡ እኚህ አባት ወደፊት ከባድ ሥራ እንደሚጠብቃቸው ከሁኔታው መረዳት ይቻላል፡፡

debere gelela eyesuseእነዚህ ገዳማት ወደፊት ምን ይገጥማቸው ይሆን? ይፈልሱ ይሆን ወይስ ወደ ቀደመ ታላቅነታቸው ተመልሰው እናይ ይሆን? ገዳማት ከመፈታታቸው በፊት ልንደርስላቸው ግድ ይለናል፡፡ ይህ የቤት ሥራ ለእያንዳንዳችን የተቀመጠ ኃላፊነት ነው፡፡

ዝምታ እንደነገሰብን ወደ ጀልባችን አመራን፡፡ ጉዞ ወደ ጎርጎራ ወደብ፡፡

በጉዟችን አንድ ነገር አስደስቶናል፡፡ አባቶቻችን ለቅርሶች ያላቸው ግንዛቤና ቅርሶች እንዳይዘረፉ የሚያደርጉት ጥንቃቄ ያስገርማል፡፡ እንኳን ለማሳየት ያለበትንም አይጠቁሙም፡፡ በእያንዳንዱ ገዳም ውሰጥ የገጠመን ተመሳሳይ ጉዳይ ሆኖ አለፈ፡፡ ነገር ግን አብዛኞቹ ገዳማት ስጋት ቢኖርባቸውም በያዝናቸው ደብዳቤዎች እየተረዳን አሰተናግደውናል፡፡ በቅርስ ዙሪያ የሚያደርጉት ጥንቃቄ ሊበረrታ የሚገባው መሠረታዊ ጉዳይ ነው፡፡

የተፈቱና በመፈታት ላይ የሚገኙ ገዳማት ድረሱልን በማለት ላይ ናቸው፡፡ ጥሪያቸውን መስማት ብቻ ሳይሆን የማቅናትም ግዴታ እንሸከም ዘንድ ግድ ይለናል፡፡

ይቆየን፡፡

ቤተ ክርስቲያን ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ
ሚያዚያ 15 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ከጎንደር ከተማ በጎርጎራ ወደብ አድርገን ልንቃኛቸው በመረጥናቸው አምስት የጣና ሐይቅ ገዳማትን ለመዘገብ የተነሳነው ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ነው፡፡ የጀልባ ላይ ጉዞ አድርጌ አላውቅም፡፡ ነገር ግን ቅዱሳን አበውን ያፈሩ፤ በጾም በጸሎት፤ በተጋድሎ የጸኑባቸው ገዳማትን በረከት ለማግኘት፤ ታሪካቸውን ለመቃኘት ቸኩያለሁ፡፡ የጋዜጠኞቹ ቡድን በአንድነት ሆነን የ64 ኪሎ ሜትሩን መንገድ ተያያዝነው፡፡
አመሻሽ ላይ ጎርጎራ ወደብ ደረስን፡፡ የጠዋት ጉዟችንን ለማመቻቸት እንዲረዳን ወደቡ ላይ ከሚገኘው የደብረ ሲና ቅድስት ማርያም ገዳም የአባቶችን ፈቃድ በመጠየቅ የምንፈልገውን መረጃ ማሰባሰባችንን ቀጠልን፡፡ በምፈልገው አቅጣጫ ጥያቄዎችን እየጠየቅን፤ ምላሽ ከአባቶች እየተሰጠን አመሸን፡፡ አዳራችንንም እዚያው አደረግን፡፡
በጠዋት ተነስተን አንጋራ ተክለ ሃማኖት ገዳምና ብርጊዳ ቅድስት ማርያም ገዳምን ቃኝተን  ማን እንደ አባ ያሳይ መድኀኔዓለም አንድነት ገዳም ስንደርስ በመምሸቱ አስፈላጊ ናቸው ያልናቸውን መረጃዎች ስናሰባስብ አደርን፡፡ በማግስቱም ደብረ ገሊላ ኢየሱስ ወአቡነ ዘካርያስ ገዳም ዘልቀን እጀበራ ቅድስት ማርያም ገዳም ላይ ከተምን፡፡
የዛሬው የጸበል ጸዲቅ ጽሑፌ እንደ ሰሞኑ ታሪክ ላይ ያተኮረ አይደለም፡፡ በጉዟችን የቃኘናቸው የአባቶቻችን አሻራ ያረፈባቸው፤ እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ የስልጣኔ ጫፍ የደረሰ አእምሯቸው ውጤቶች በነበሩ ነገር ግን የተፈቱና ለመፈታት በቋፍ ላይ የሚገኙት ጥንታዊ የጣና ደሴት በረከቶችን እንቃኝ ዘንድ ወደድኩ፡፡ ክፍል አራት ጸበል ጸዲቅን ተቃመሱ፡፡
አንጋራ አቡነ ተክለ ሃማኖት ገዳም፡-
አንጋራ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ለመድረስ ከደብረ ሲና ማርያም ገዳም የ20 ደቂቃ በጀልባ  የጣና ሐይቅን ማቋረጥ ይጠይቃል፡፡ በደብረ ሲና ማርያም ገዳም አገልጋይ የሆኑት ሁለት መነኮሳት አባቶች ወደ ማን እንደ አባ አቡነ ያሳይ መድኀኔዓለም ገዳም ስለሚሔዱ እንድናደርሳቸው ስለጠየቁን አብረን ለመጓዝ ተስማምተን ጸሎት አድርገውልን የጣና ሐይቅ የጀልባ ላይ ጉዞ ተጀመረ፡፡
አንጋራ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ስንደርስ ያልጠበቅነው ነገር ገጠመን፡፡ በድንጋያማው ደሴት ላይ ያረፈው ቤተ መቅደስ በዝምታ ተውጧል፡፡ አፍ አውጥቶ “የሰው ያለህ” በማለት የሚጣራ ይመስላል፡፡ በአካባቢው ሰው ዘር ያለ አይመስልም፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ስንጠጋ አንዲት ደሳሳ ጎጆ ቤት ደጃፍ ላይ አንድ አባት እድሜ ተጭኗቸው ኩርምት ብለው ተቀምጠዋል፡፡ ዓይነ ሥውር ናቸው፡፡ ዘጠና ዓመታቸው ሲሆን ወደ አንጋራ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ከመጡ 25 ዓመታታን አስቆጥረዋል፡፡
“አባታችን ስለዚህ ገዳም ታሪክና አሁን ያለበት ሁኔታ የሚነግረን ሰው እናገኝ ይሆን?” የሁላችንም ጥያቄ ነበር፡፡
“የምን ሰው?! ማን አለ ብላችሁ ነው?! ገዳሙ ሊፈታ ምንም አልቀረውም፡፡ እስቲ ወደ ታች ወረድ ብላችሁ ገበዙን ፈልጉት” አሉን፡፡
ውስጤ መረበሽ ጀመረ፡፡ ማንን እንጠይቅ? የኢየሩሳሌምን ጥፋት አታሳየኝ ያለውና እንደ ቃሉም የተፈጸመለት አቤሜሌክን አስታወስኩ፤፤ ከጓደኞቼ ገንጠል ብዬ የሚተናነቀኝን የቁጭት እንባ አፈሰስኩ፡፡ ቤተ መቅደሱ ላይ ዓይኖቼ እንደተተከሉ አባቶችን አሰብኩ፡፡ አባቶቻችን ይህንን ገዳም ሲገድሙት ምን ይመስል ነበር? በገዳማውያን አባቶች ተሞልቶ፤ መላእክትን መስለው እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑበት፤ በጸሎት አጋንንት ድል ሲነሱበት የነበረ፤ ቃል ኪዳን የተቀበሉበት ሥፍራ ምነው ዛሬ ነጠፈ?! ራሴንና ይህንን ትውልድ ተጠያቂ ከማድረግ ሌላ ምን ማለት እችላለሁ? አባቶቻችንን መስለን ያልተገኘን፤ የአባቶቻችን አደራ መሸከምም ሆነ መወጣት ያቃተን ትውልዶች እንደሆንን ተሰማኝ፡፡ ብቻዬን መሆን አማረኝ፡፡ ነገር ግን አልቻልኩም እንደተከፋሁ ከጓደኞቼ ጋር ተቀላቀልኩ፡፡ እንደ እኔው በዝምታ ቆዝመዋል፡፡  
የቤተ ክርስቲያኑን ገበዝ ከእኛ ጋር ከደብረ ሲና ቅድስት ማርያም ገዳም የመጡት መነኮሳት አባቶች ፈልገው ይዘዋቸው መጡ፡፡ በእርግና እድሜ ላይ ነው የሚገኙት፡፡ ደብዳቤያችንን አሳይተን መረጃ እንዲሰጡን ጠየቅናቸው፡፡ ታሪኩን በተደራጀ መልኩ መናገር ተሳናቸው፡፡ ቅዱሳን አባቶቻችን ቅድስት ቤተ ክርስተቲያንን ለትውልድ ይተላለፍ ዘንድ የከፈሉት መስዋእትነት እንደዋዛ ፈዛዛ ማለፉ ነው፡፡ ገዳሙ የእምነታችን መገለጫ የሆኑትን የአባቶቻችንን ታሪክና ቅርሶችን ታቅፎ ዝምታን መምረጡ ለምን ይሆን? ለመሆኑ ተጠያቂው ማነው? ውስጤን ሰላም ነሳኝ፡፡  
አገልጋዮቹ ከሦስት አይበልጡም፡፡ ቅዳሴ አይታሰብም፡፡ ከቀናቸው ኪዳን ያደርሳሉ፡፡ ካልሆነም በግል ጸሎት ይተጋሉ፡፡ የሚተካቸው የለም፡፡ ይህ ትውልድ ርቋቸዋል፡፡ አባቶቻችንን መምሰል፤ በቃልኪዳናቸው መጠቀምን ዘንግተን ይሆን? የወደፊት የእኛም ሆነ የተፈቱ ገዳማት እጣ ፈንታ ምን ይሆን? የቃረምነውን መረጃ ቋጥረን፤ በሐዘን አንገታችንን እንደደፋን ወደ ጀልባችን አመራን፡፡ ጉዞ ወደ ብርጊዳ ቅድስት ማርያም ገዳም፡፡
ብርጊዳ ማርያም ገዳም፡-
ወደ ብረጊዳ ማርያም ገዳም እያመራን ደሴት ስንመለከት ይህ ምንድነው ማለታችን አልቀረም፡፡ አብረውን ያሉት አባቶች ከእኛ የተሻለ መረጃ ስላላቸው የሰቀላ ሚካኤልን፤ የቅዱስ ጊዮርጊስንና የእመቤታችን ማርያም የጥንት ገዳማትን በጣታቸው እያሳዩን አለፍን፡፡ ሦስቱም ገዳማት ተፈትተው ዛሬ ሰው አልባ ሆነዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያኖቹም ፈርሰዋል፡፡ በምሰማው ነገር ታመምኩ፡፡

እነዚህ ገዳማት ወደፊት ምን ይገጥማቸው ይሆን? ይፈልሱ ይሆን ወይስ ወደ ቀደመ ታላቅነታቸው ተመልሰው እናይ ይሆን? ገዳማት ከመፈታታቸው በፊት ልንደርስላቸው ግድ ይለናል፡፡ ይህ የቤት ሥራ ለእያንዳንዳችን የተቀመጠ ኃላፊነት ነው፡፡

kuskuam 01

ጎንደር – የቅዱሳት መካናት ማኅደር

ሚያዚያ 14 ቀን 2005 ዓ.ም.

በእንዳለ ደምስስ

ጸበል ጸዲቅ /ክፍል ሦስት/

ጎንደር ገብተናል፡፡ ዞር ዞር እያልኩ ለመቃኘት ጊዜ አልወሰድኩም፡፡ የምችለውን ያህል እግሬ እሰከመራኝ ተጓዝኩ፡፡ ጎንደር ውስጥ አንድ ቤተ ክርስቲያን ለማግኘት አንድ ኪሎ ሜትር መጓዝ አይጠበቅብዎትም፡፡ ቀና ብለው አካባቢውን በዓይንዎ መቃኘት ብቻ ይበቃዎታል፡፡  ከሰሜን ወደ ደቡብ፤ ከምስራቅ ወደ ምዕራብ ቢመለከቱ በእርግጠኝነት የቤተ ክርስቲያን የጉልላት መስቀል እንዳሻዎት ያገኛሉ፡፡ በቃ ወደ ተመለከቱበት አቅጣጫ ማምራት፡፡ 44ቱ ተቦት የሚለው አባባል ቀድሞ በጎንደር 44 ታቦታት ስለነበሩ አይደል?

ወቅቱ የዐብይ ጾም በመሆኑ ከሌሊት ጀምሮ ስብሐተ እግዚአብሔር እንደ ጅረት ውኃ ያለማቋረጥ ከሊቃውንቱ አንደበት ይፈስሳል፡፡ ተኝተውም ይሁን ሥራ ላይ ሆነው አብረው ለማዜም ይገደዳሉ፡፡ ይህንን ዓለም አስረስተው ሰማያዊውን መንግሥት በተመስጦ ያስባሉ፡፡ ነፍስዎ በሚደርሰው ስብሐተ እግዚአብሔር ይለመልማል፡፡

ከጠዋት እስከ ስድስት ሰዓት፤ ከዚያም እስከ 9፡00 ሰዓት ምግብ ቤቶች፤ ሆቴሎችና ሻይ ቤቶች ሳይቀር ወንበሮቻቸውን ታቅፈው የሰው ያለህ ማለታቸው ጎንደር ውስጥ በጾም ወራት የተለመደ ነው፡፡ አንገቱ ላይ ክር ያላሰረ ለማየት ይቸግራል፡፡ ጎንደር ፈካ ደመቅ ማለት የምትጀምረው ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ሥርዓተ ቅዳሴ ከተጠናቀቀ በኋላ ነው፡፡ ጎንደር! የታላላቅ ቅዱሳት መካናት፤  የሊቃውንት ማኅደር፤ የነገሥታት አሻራ ያገዘፋት ከተማ!!

የጋዜጠኞቹ ቡድን ጎንደርን ተከፋፈልናት፡፡ በውስጧ ሸሽጋ ያኖረቻቸውን የአብያተ ክርስቲያናት ታሪክ፤ የሊቃውንቱ የሕይወት ተሞክሮ ለሌሎች ለማቃመስ ቸኩለናል፡፡ ለዛሬ ጎንደር ካቀፈቻቸው ቅዱሳት መካናት መከካል አንዱን ከብዙ በጥቂቱ እንካችሁ ጸበል ጸዲቅ ቅመሱ፡፡

የደብረ ፀሐይ ቁስቋም ማርያም ገዳም
kuskuam 01የደብረ ፀሐይ ቁስቋም ማርያም ገዳም ከጎንደር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በስተ ሰሜን አቅጣጫ ተራራው አናት ላይ በጥንታዊ ስልጣኔ አሻራ ባረፈበት ግንብ አጥር ታቅፎ ለሚያየው ውስጡን ይመረምሩ ዘንድ ይጋብዛል፡፡ ዓይኔም ልቦናዬም አርፎበታልና ስለዚህ ቤተ ክርስቲያንና ቤተ መንግሥት ለማወቅ ጉዞ ጀመርኩ፡፡ አቀበቱን እንደወጣሁ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የአብነት ትምህርት ተማሪዎች ጎጆዎችን አገኘሁ፡፡ ከተማሪዎቹ መካካል አንዱን እንኳን ማግኘት አልቻልኩም፡፡ ወደ ገዳሙ የሚያስገባው መንገድ እየተሠራ በመሆኑ አንዱን ሠራተኛ ጠየቅሁት፡፡ ወደ ጫካ ለቅኔ ቆጠራ ሄደዋል አለኝ፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ መግቢያ ተጠጋሁ፡፡ ከሦስት ሜትር በላይ እርዝመት ያለውና በኢትዮጵያውያን  ጠቢባን በድንጋይ የተገነባ ግንብ ጥንታዊነቱን በሚመሰክር ሁኔታ እርጅና ቢጫጫነውም ጥንካሬው ጎልቶ ይታያል፡፡ አጥሩ በዐፄ ፋሲል ግንብ ዲዛይን የተሠራ ነው፡፡   

ተሳልሜ ደጀ ሰላሙን እንዳለፍኩ አባቶችን ሳፈላልግ የገዳሙ የሙዝየም አስጎብኚና የቅኔ መምህሩ የኔታ ዳንኤል ኃይሉን አገኘሁ፡፡ የመጣሁበትን አስረድቼ፤ የተጻፈልኝን የፈቃድ ደብዳቤ በማሳየት ለምጠይቃቸው ጥያቄ ይመልሱ ዘንድ ፈቃደኛ በመሆናቸው አንድ ጥግ ያዝን፡፡ የነገሩኝን እንዲህ አዘጋጀሁት?!

አመሠራረቱ፡-
የደብረ ጸሐይ ቁስቋም ማርያም ገዳም በ1930ዎቹ ዓ.ም በአፄ በካፋ ባለቤት በእቴጌ ምንትዋብ አማካይነት የተሠራ ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ አመሠራረቱም ዐፄ በካፋ ከሞቱ በኋላ እቴጌ ምንትዋብ ልጃቸውን ኢያሱን አንግሠው ከዐፄ ፋሲል ቤተ መንግሥት ግቢ በመውጣት ይህ ዓለም ይቅርብኝ፡ እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም በስደት በግብፅ በደብረ ቁስቋም ተራራ ላይ እንደተገኘች ሁሉ እኔም ለብቻዬ ልቀመጥ በማለት ቤተ መንግሥታቸውን ጥለው ቤተ ክርስቲያኑን በማሠራት ተቀመጡ፡፡  ከዚሁ ጋር በማያያዝም ቤተ መንግሥታቸውን አሠሩ፡፡ ቤተ ክርስቲያኑንና ቤተ መንግሥቱን ለማሠራት አንድ ሺሕ ግንበኞችና ባለሙያዎች የተሳተፉበት ሲሆን ለሁለት በመክፈል አምስት መቶው ሠራተኞች አንድ ቀን ሲሠሩ ሌሎቹ ደግሞ እያረፉ በየተራ ሠርተውታል፡፡ቤተ ክርስቲያኑንም ስደታቸውን በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስደት ጋር በማያያዝ በደብረ ቁስቋም ሰየሙት፡፡ ከሁለት ሃምሳ በላይ ቀሳውስትና ካህናት አገልጋዮች ነበሩት፡፡

እቴጌ ምንትዋብ ሲያርፉም በቤተ ክርስቲያኑ ምድር ቤት ውስጥ ባሠሩት መቃብር ቤታቸው አስከሬናቸው እንዲያርፍ የተደረገ ሲሆን ልጃቸው ኢያሱና የኢያሱ ልጅ ኢዮአስkuskuam 03 ሲያርፉም አብረው በእቴጌ ምንትዋብ መቃብር ቤት ተቀብረዋል፡፡

በ1881 ዓ.ም. ደርቡሽ ጎንደርን ሲወርር ጎንደር የሚገኙትን ብዙዎቹን ቤተ ክርስቲያናት ስያቀጥልና ሲያወድም ካህናቱ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ታቦት ወደ በለሳ በማሸሽ አስቀመጡት፡፡ ደብረ ቁስቋም ቤተ ክርስቲያንም ሙሉ ለሙሉ ወደመ፡፡ ቤተ መንግሥቱንም ደርቡሽ አፈራረሰው፡፡ አብዛኞቹ ቅርሶችም ተቃጠሉ፡፡ የተረፉትም ቢሆን ተዘርፈው ተወሰዱ፡፡ ካህናቱም ወደተለያዩ ቦታዎች ተበተኑ፡፡

ቅርሶች፡- ከጦርነቱ በኋላ ታቦቱን ወደነበረበት በመመለስ ቀድሞ እቃ ቤት የነበረውን  ቤት ቤተ መቅደስ በማድረግ በጥቂት ካህናት ብቻ ለሰማኒያ ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ ከቆየ በኋላ በ1960ዎቹ ዓ.ም. ዐፄ ኃይለ ሥላሴ አሁን ያለውን ቤተ ክርስቲያን አሠሩት፡፡ የእቴጌ ምንትዋብና የልጃቸው ኢያሱ፤ እንደሁም የኢያሱ ልጅ ኢዮአስን ዓፅም በአንድ ላይ በመሰብሰብ በሳጥን ውስጥ እዲቀመጥ ተደረገ፡፡ በአሁኑ ወቅትም በሙዝየሙ ውስጥ ከሚጎበኙ ቅርሶች መካከል አንዱ ነው፡፡

በሙዝየሙ ውስጥ የእቴጌ ምንትዋብና የልጆቻቸው በእንጨትና በጠፍር/ቆዳ/ የተሠራ አልጋ፤ በቀርከሃና በቆዳ የተሠሩ የከበሩ ዕቃዎች ማስቀመጫ ሻንጣዎች፤ ሚዛን፤ የደርቡሽ ጦር ካወደማቸው ሃይማኖታዊ የብራና መጻሕፍት የተረፉት ወንጌል ቅዱስ፤ ተአምረ ኢየሱስ፤ ግንዘት፤ ስንክሳር፤ ነገረ ማርያም፤ ሃማኖተ አበው፤ አሥራ አራቱ ቅዳሴያት፤ ግብረ ሕማማት፤ ገድለ ሠማዕታት፤. . . ከበሮ፤ የተለያዩ መጠን ያላቸው መስቀሎች፤ ነጋሪት፤ ከሙዝየሙ ውጪ በሩ አጠገብ የእቴጌ ምንትዋብ የድንጋይ ወፍጮ፤ . . .  ይገኛሉ፡፡

kuskuamቅዱሳት ሥዕላት፡- በሙዝየሙ ውስጥ በቅርስነት ከተያዙት ውስጥ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምስለ ፍቁር ወልዳና የቅዱስ መርቆርዮስ ቅዱሳት ሥዕላት ይገኙበታል፡፡

ቤተ መንግሥት፡- ቤተ መንግሥቱ ሰባት በሮች አሉት፡፡ የእቴጌ ምንትዋብ መኝታ ቤት፤ የገላ መታጠቢያ ቤት፤ ሣሎን፤ በዘመኑ የነበረው ታሪክ ጸሐፊው ጀምስ ብሩስ ይኖርበት የነበረው ክፍል፤ ካህናቱና ቀሳውስቱ የሚመገቡበት የግብር ቤት፤ ቤተ ክርስቲያኑንና ቤተ ክርስቲያኑን ያነጹት ባለሙያዎች ማረፊያ ክፍሎችና ዕቃ ማስቀመጫ ክፍሎች፤ . . . ፈራርሰው ይታያሉ፡፡

ጉባኤ ቤት፡- ጥንት የድጓ፤ የቅኔ፤ የአቋቋም፤ የቅዳሴ ጉባኤ ቤቶች እንደነበሩና ደርቡሽ ቤተ ክርስቲያኑን ካፈረሰ በኋላ ግን ጉባኤ ቤቶቹkuskuam 08 ተፈትተው ለረጅም ዘመናት ሳይተከሉ ኖረዋል፡፡ ጉባኤ ቤቱ በተደራጀ መልኩ ከተተከለ ሃያ ዓመታት ብቻ አስቆጥሯል፡፡ የቅኔ፤ የአቋቋም፤ የድጓና የቅዳሴ ጉባኤ ትምህርት እየተሰጠ ይገኛል፡፡ ከ500 በላይ ተማሪዎች ሲኖሩ 280 የሚደርሱት የቅኔ ተማሪዎች ናቸው፡፡

መረጃዎቻችንን እንዳሰባሰብን ያመራነው ወደ ጉባኤ ቤት ነው፡፡ ከየኔታ ዳንኤል ኃይሉ ጋር ተያይዘን ስንሄድ የቅኔ ተማሪዎቻቸው ከያሉበት ብቅ ብቅ ማለት ጀመሩ፡፡ ሌሊት ዕለቱን በማስመልከት የኔታ ካስረዷቸው በኋላ ለቅኔ ቆጠራ ይሠማራሉ፡፡ የኔታ በተማሪዎቻቸው ተከበቡ፡፡ የነገራ ሰዓት በመሆኑ ለጥቂት ደቂቃዎች እንድታገስ ጠየቁኝ፡፡ አላመነታሁም፡፡ ተማሪዎቹ ወንበር አውጥተው እንዲቀመጡ ካመቻቹላቸው በኋላ በአእምሯቸው ሲያመላልሱት የቆዩበትን ቅኔ ቆጠራ መዝረፍ ጀመሩ፡፡ ሲሳሳቱ እያረሙ፤ ያልተሳካለትን እየገሰጹ ቆዩ፡፡

የተማሪዎቹን የውድድር ስሜትና ለትምህርቱ ያላቸው ፍላጎት እያስገረመኝ ከተማሪዎቹ መካከል አይኖቼ ድንገት በለጋነት እድሜ ክልል የሚገኙ መነኩሲት ላይ አረፉ፡፡ ላነጋግራቸውም ወሰንኩ፡፡

የኔታ ከዚህ በላይ ሊያስቆዩኝ አልፈለጉም፡፡  ጉባኤውን አቋረጡት፡፡ እኔም እማሆይን ለመጠየቅ በመፍጠን ማንነታቸውን፤ ለምን መማር እንደፈጉ ጠየቅኋቸው፡፡

kuskuam 07“እማሆ ወለተ መድኅን እባላለሁ፡፡ ከአክሱም ነው የመጣሁት፡፡ በልጅነት ከመነኮስኩ አይቀር ጉባኤ ቤት መግባት አለብኝ ብዬ ስለወሰንኩ እዚህ እየተማርኩ እገኛለሁ፡፡ ትምህርቱንከጀመርኩ አንድ ዓመት ሆኖኛል፡፡ ጉባኤ ቃና፤ ዘአምላክየ፤ ሚበዝኁ፤ ዋዜማ፤ ሥላሴ፤ ዘይእዜ፤ ክብር ይእቲ፤ እጣነ ሞገርን አልፌ መወድስ ላይ ደርሻለሁ፡፡ እግዘአብሔር ቢፈቅድ ትምህርቴን አጽንቼ በመያዝ እግዚአብሔር ቢፈቅድ እንደ እማሆይ ገላነሽ ለመሆን ነው ምኞቴ” አሉኝ፡፡ ምኞታቸው እንዲሳካ ተመኘሁ፡፡

ከቀደሙት ነገሥታት የሃይማኖት ጽናትንና ቅርስን ለትውልድ ማቆየትን ተማርኩ፡፡ ከጉባኤ ቤቶቹ ደግሞ ቤተ ክርስቲያን የማይነጥፍ የሊቃውንት ምንጭ እንዳላት ተገነዘብኩ፡፡   
የኔታንና ተማሪዎቹን ተሰናብቼ ሌላ መረጃ ልቆፍር ተጓዝኩ፡፡

ይቆየን

tsebele tsedeke 3

ጸበል ጸዲቅ /ክፍል ሁለት/

ሚያዚያ 8 ቀን 2005 ዓ.ም.

በእንዳለ ደምስስ

ደብረ ገነት ሸረት መድኀኔዓለም ገዳም
ሚያዚያ 4 ቀን 2005 ዓ.ም.

tsebele tsedeke 3ከንጋቱ 12፡30 ደምበጫ ከተማ ላይ ካረፍንበት የማኅበረ ቅዱሳን ከራድዮን ምግብ ቤት ተነስተን ከወረዳ ማእከሉ ወንድሞቻችን ጋር ሆነን ወደ ጽርሐ አርያም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በማምራት ጸሎት አደረስን፡፡ በያዝነው እቅድ መሠረት ዲያቆን ቴዎድሮስ ኃይሉና ዲያቆን ዮሴፍ ይኩኖ አምላክ የጽርሐ አርያምን ቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንዲሰሩ እዚያው ትተናቸው የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጁ ቶማስ በየነ፤ የቪዲዮ ካሜራ ባለሙያው ሙሉጌታ፤ ዲያቆን ታደለ ሲሳይና እኔ ሆነን የደብረ ገነት ሸረት መድኀኔዓለም ገዳምን ለመዘገብ ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት ሲሆን እግዚአብሔርን ተስፋ አድረገን በሾፌራችን ነብያት መንግስቴ እየተመራን የ47 ኪሎ ሜትሩን መንገድ ተያያዝነው፡፡

ዋድ የገጠር ከተማን፤ ዋድ ኢየሱስ፤ ዋድ ሥላሴ ቤተ ክርስቲያናትን አልፈን፤ ደግን ወንዝን ተሻግረን፤ ዘለቃን የገጠር ከተማን አልፈን ወደ ገዳሙ መግቢያ ደረስን፡፡ ከተራራው አናት ላይ ሆነው ወደ ገዳሙ ሲመለከቱ እልም ባለ በረሃ ውስጥ ለብቻው ለምልሞ የተገኘ የምድር ገነት ያስመስለዋል፡፡ በገዳሙ ውስጥ እግዚአብሔርን ደጅ በመጥናት በጸሎትና በልማት አገልግሎት ላይ የተጠመዱት መነኮሳትና መነኮሳይያት ማረፊያ ቤቶች፤ የመድኀኔዓለምንና የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያናትን በመክበብ እጅብ ብለው ደምቀው ይታያሉ፡፡  

አርባ ሰባት ኪሎ ሜትሩን ለማገባደድ 2፡30 ሰዓት ፈጅቶብን የደረስነው ከጠዋቱ 3፡00 ላይ ነው፡፡ ከመኪናችን ወርደን በእድሜ ጠገብ ዛፎች፤ ጥላ ተጋርደን የሙዝ፤ የፓፓያ፤ የብርቱካን፤ የአቦካዶ፤ . . . ዘርዝረን በማንጨርሳቸው የፍራፍሬዎችና የሸንኮራ አገዳ ተክሎችን እያለፍን ጸበል መጠመቂያ ሥፍራ ላይ ደረስን፡፡ ከተለያዩ የገዳሙ አቅራቢያ ከተሞችና የገጠር መንደሮች በመጡ ተጠማቂዎች ሕጻናትን ጨምሮ ተሞልቷል፡፡

ከተራራው ሥር የሚፈልቁ ምንጮች መውረጃ ቦይ ተዘጋጅቶላቸው አትክልቶቹን ያለመሰልቸት ያጠጣሉ፡፡ ጸበሉም ተጠማቂዎች ከተጠመቁ በኋላ ወደ አትክልልቶቹ መፍሰሱን ይቀጥላል፡፡ በግዮን፤ ኤፍራጥስና ጤግሮስ ወንዞች የተከበበ እስኪመስል ድረስ የንጹህ ውኃ ጅረቶች ከተለያዩ አቅጣጫዎች በልምላሜ በተሞላው ገዳም ተውጠው ይቀራሉ፡፡ የሚባክን ውሃ የለም፡፡ ድካማችን ሁሉ ከላያችን ላይ ተገፍፎ በብርታት፤ በእርካታና በተመስጦ ተሞልተናል፡፡ የምናያቸው፤ የምንሰማቸው ድምጾች ሁሉ አዳምና ሔዋን የኖሩባንት ገነትን tsebele tsedeke 5በዓይነ ሕሊናችን እንድናስብ አስገድዶናል፡፡ ደብረ ገነት ሽረት መድኀኔዓለም በምድር ላይ ያለች የገነት ተምሳሌት ሆና ታየችን፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ስንገባ በገዳሙ ውስጥ በምናኔና ገዳሙ በሚያከናውናቸው የልማትና የአስተዳደር ሥራዎች አበምኔቱን በማገዝ ላይ የሚገኙት አባ ዳዊትን ከሌሎች መነኮሳት ጋር በመሆን የእለት ተግባራቸውን በማከናወን ላይ እያሉ አገኘናቸው፡፡ ቡራኬ ተቀብለን በገዳሙ ሥርዓት መሠረት አባቶች አደግድገው እግራችንን አጠቡን፡፡

የገዳሙ መሥራችና አበምኔት አባ ገ/ኢየሱስ አካሉ ወደ ገዳሙ የሚያስገባውን ጥርጊያ መንገድ ለማሰራት ዘለቃ ወደሚባለው ከተማ በመሔዳቸው የምንፈልገውን መረጃ አባ ዳዊት ሊሰጡን እንደሚችሉ ተስማማን፡፡

አጭር መረጃ ስለ ገዳሙ፡- tsebele tsedeke 4
የደብረ ገነት ሸረት መድኀኔዓለም ገዳም በአባ ገ/ኢየሱስ አካሉ በ1969 ዓ.ም. ተመሠረተ፡፡ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን በ1973 ዓ.ም. በሣር ክዳን ተተከለች፡፡ ሥፍራው ጥቅጥቅ ያለ ጫካ የነበረ ሲሆን አንበሳ፤ ነብርና ዘንዶ በብዛት ይገኙ እንደነበር አባ ዳዊት ይገልጻሉ፡፡ ቀስ በቀስ ገዳማውያን እየተበራከቱ የልማት ሥራው እየሰፋ ሲሔድ የገዳሙ ይዞታም ሊሰፋ ችሏል፡፡ የክልሉ መንግስት በገዳሙ ውስጥ ከፍተኛ የልማት እንቅስቃሴ ከግምት ውስጥ በማስገባት ሰፊ የእርሻ መሬት ለገዳሙ ተሰጥቷል፡፡ ዳጉሳና በቆሎ እንዲሁም የሸንኮራ አገዳ በስፋት ይመረትበታል፡፡  

በሁለት ቦታዎች ላይ ሞፈር ቤቶች፤ ተራራው ላይ በስተደቡብ አቅጣጫ የአቡነ አረጋዊ ገዳም ቋርፍ ቤት ይገኛል፡፡ በገዳሙ ውስጥ 600 መናንያን ሲኖሩ 320ዎቹ መነኮሳት፤ 280ዎቹ ደግሞ መነኮሳይያት ናቸው፡፡ መነኮሳቱ በወንድ ሊቀ ረድእ፤ መነኮሳይቱ በሴት ለቀ ረድእ ይመራሉ፡፡ የእለት ተእለት ሥራቸውንም በሊቀ ረድኦቻቸው አማካይነት እየተመደቡ ያከናውናሉ፡፡ አረጋውያኑ ደግሞ በጸሎት፤ ቤተ ክርስቲያኑን በመጠበቅ፤ አትክልቶቹን ከአውሬ በመከላከል ገዳሙን ይረዳሉ፡፡ የገዳማውያኑ የጸሎት፤ የሥራና የምግብ ሰዓታትም የተወሰኑ ናቸው፡፡

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፤ የቅዱስ ሚካኤል፤ የአቡነ አረጋዊና የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ታቦት በዚሁ ገዳም ይገኛሉ፡፡ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ጣሪያው በሣር ክዳን የተሸፈነ ሲሆን ሳይፈርስ በቅርስነት እንዲያዝ በመወሰኑ ከመድኀኔዓለም ክርስቲያን በስተምእራብ አቅጣጫ ከተራራው ሥር ከሚገኘው ቋጥኝ ድንጋይ እየተጠረበ ቤተ ክርስቲያኑ በመገንባት ላይ ነው፡፡

የዮርዳኖስ ጸበል፤ የአቡነ አረጋዊ፤ የአቡነ ተክለ ሃይማኖትና የቅዱስ ሚካኤል ጸበል በገዳሙ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ሕሙማን እየተጠመቁ ፈውስ በማግኘት ላይ ናቸው፡፡  የዮርዳኖስ ጸበል አፈሩን ከኢየሩሳሌtsebele tsedeke 6ምና ከዋልድባ ገዳማት እንደመጣም አባ ዳዊት ገዳሙን እያስጎበኙን ነግረውናል፡፡

የአብነት ትምህርት ገዳሙ ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ እየተሰጠ ይገኛል፡፡ ከ1975 ዓ.ም. እስከ 1977 ዓ.ም. በጉባኤ ቤቱ ቅዳሴን ከአባ ገብረ ማርያም ተምረው በማጠናቀቅ አባ ገብረ ማርያም ሌላ ገዳም ለማቅናት በመሄዳቸው ጉባኤውን የተረከቡት መምህር ገብረ ሥላሴ ፈንታ ለ28 ዓመታት የቅዳሴ ትምህርት በማስተማር ላይ ናቸው፡፡ ከሁለት መቶ በላይ ደቀመዛሙርትም እየተማሩ ይገኛሉ፡፡ ታላላቅ ሊቃውንትንም አፍርተዋል፡፡ በገዳሙ ውስጥ በአባ ገብረ ማርያም ከተማሩት አባቶች መካከልም ብፁዕ አቡነ አብርሐም አንዱ ናቸው፡፡

ይቆየን