ኢትፍርሕዎ ለሞት ፍርሕዋ ለኃጢአት፤ቅዱስ ያሬድ
ሞት በብዙ መንገድ ቢተረጎምም ቀጥተኛ ትርጉሙ ግን መለየት ማለት ነው፡፡ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ በሚል መጽሐፋቸው “መሞት፣ መለየት፣ በነፍስ ከሥጋ፣ በሥጋ ከነፍስ መራቅ፣ እየብቻ መኾን፣ መድረቅ፣ መፍረስ፣ መበስበስ፣ መነቀል፣ መፍለስ፣ መጥፋት፣ መታጣት” በማለት ይፈቱታል፡፡ (ኪዳነ ወልድ፣ገጽ፣፭፻፹፩) እንዲሁም አለቃ “ሞት በቁሙ የሥጋዊና የደማዊ ሕይወት ፍጻሜ በአዳም ኃጢአት የመጣ ጠባይዓዊ ዕዳ ባሕርያዊ ፍዳ” በማለት ይፈቱታል፡፡ (ዝኒ ከማሁ)