ጸሎተ ሐሙስ

ጸሎተ ሐሙስ በብሉይ ኪዳን ለፋሲካ ዝግጅት ተደርጎበታል (ማቴ. ፳፮፥፯-፲፫)፡፡ ‹ፋሲካ› ማለት ማለፍ ማለት ነው፡፡ ይኸውም እስራኤላውያን በግብጽ ምድር ሳሉ መልአኩን ልኮ እያንዳንዱ እስራኤላዊ የበግ ጠቦት እንዲያርድና ደሙን በበሩ ወይም በመቃኑ እንዲቀባ ለሙሴ ነገረው፡፡ ሙሴም የታዘዘውን ለሕዝቡ ነገረ፤ ሁሉም እንደ ታዘዙት ፈጸሙ፡፡ በኋላ ከእግዚአብሔር ዘንድ መቅሠፍት ታዞ መልአኩ የደም ምልክት የሌለበትን የግብጻውያንን ቤት በሞተ በኵር ሲመታ፤ የበጉ ደም ምልክት ያለበትን የእስራኤላውያንን ቤት ምልክቱን እያየ አልፏል፡፡ ፋሲካ መባሉም ይህን ምሥጢር ለማስታወስ ነው (ዘፀ. ፲፪፥፩-፳)፡፡

ሆሳዕና

ሆሼዕናህ ከሚል ከዕብራይስጥ ቃል የተገኘው ሆሳዕና ትርጓሜው እባክህ አሁን አድን ማለት ነው፡፡ ይህ ቃል በዘመነ ብሉይ በቀደምት ነቢያት ዘንድ የተለመደ ቃል ነው፡፡ አቤቱ እባክህ አሁን አድን፣ አቤቱ እባክህ አሁን አቅና፣ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው፡፡ (መዝ.፻፲፯፥፳፭-፳፮) የሆሳዕና በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የሚቀድሙትና የሚከተሉት ሕዝብ በተለይም አእሩግና ሕፃናት ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ፣ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፣ ሆሳዕና በአርያም በማለት ጌታችንን በክብር መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል ነው፡፡ በዓሉም ሆሳዕና የሚለውን ስያሜ ያገኘው በዕለቱ ከተዘመረው መዝሙር ነው፡፡

ኒቆዲሞስ

በመዘነ ሥጋዌ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ምደር መምጣትና መሲሕ መባል ያልተቀበሉት በርካታ እስራኤላዊያን እርሱን እስከመስቀል እንደደረሱ ወንጌል አስተምሮናል፡፡ ሆኖም በፍጹም እምነት እስከ መጨረሻው ከተከተሉት ፈሪሳውያን አንዱ ኒቆዲሞስ ለታላቅ ክብር የበቃ ሰው ነው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህን ታላቅ ሰው ለመዘከር የዐቢይን ጾም ሰባተኛ እሑድ በስሙ ሰይማ ታከብረዋለች፤ ተከታዮቿ ምእመናንም የእርሱን አሠረ ፍኖት እንዲከተሉ ትመክራለች፤ ታስተምራለችም፡፡

“እናንተ ኃጢአተኞች እጃችሁን አንጹ፤ እናንተ በሁለት ሀሳብ የምትዋልሉ ልባችሁን አጥሩ” (ያዕቆብ ፬፥፰)

አሁንም ይህ መቅሰፍት የእግዚአብሔር ቁጣ መሆኑን ማመን የማይፈልጉ እና የማያምኑ ሰዎች በርካታ ናቸው፤‹‹ስለዚህ ቍጣዬን አፈሰስሁባቸው፥ በመዓቴም እሳት አጠፋኋቸው፤ መንገዳቸውንም በራሳቸው ላይ መለስሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር›› እንዲል። (ሕዝ. ፳፪፥ ፴፩) እነርሱ ፈውሰ ሥጋም ሆነ ነፍስ እግዚአብሔር መሆኑን ዘንግተውታል፤ ድኀነተ ሥጋም ሆነ ድኅነተ ነፍስ የሚገኘው ግን ከፈጣሪ ዘንድ ነው፡፡

“ከእነዚህ ሥራዎችም ሰውነታችሁን ብትጠብቁ በሰላም ትኖራላችሁ” (ሐዋ.፲፭፥፳፰)

ሐዋርያት በወቅቱ ደቀ መዛሙርቱን የላኳቸው መልእክት እንዲህ የሚል ነበር። “ሥርዓት እንዳናከብድ፤ ሌላም ሸክም እንዳንጨምር መንፈስ ቅዱስ ከእኛ ጋራ ነውና ነገር ግን ይህን በግድ ትተው ዘንድ እናዝዛችኋለን። ለአማልክት የተሠዋውን፣ ሞቶ የተገኘውን፣ ደምንም አትብሉ፤ ከዝሙትም ራቁ፤ በራሳችሁ የምትጠሉትንም በወንድሞቻችሁ ላይ አታድርጉ፤ ከእነዚህ ሥራዎችም ሰውነታችሁን ብትጠብቁ በሰላም ትኖራላችሁ”፡፡(ሐዋ.፲፭፥፳፰-፳፱)፤ሐዋርያት ለሕዝቡ ከመጨነቃቸው የተነሣ “ሥርዓት እንዳናከብድ ሌላም ሸክም እንዳንጨምር መንፈስ ቅዱስ ከእኛ ጋር ነውና” በሚል መልእክቱን ልከዋል፡፡ ዛሬም ቅዱስ ሲኖዶስ የሚያስተላልፈውን መመሪያ መስማት ከምእመናን ይጠበቃል። በምእመናን ላይ ሥርዓት እንዳይከብድ፣ ምእመናኑ በመጣው መዓት እንዳይደናገጡ፣ ባልጸና እምነታቸው የመጣውን መዓት መቋቋም ተስኗቸው ከቤቱ እንዳይወጡ በማዘን ነውና ቃላቸውን ሊሰማ ይገባል።

ኢትፍርሕዎ ለሞት ፍርሕዋ ለኃጢአት፤ቅዱስ ያሬድ

ይህ ለዓለም ሕዝብ ሥጋት የሆነውን በሽታ ከመጠን በላይ በሆነ ፍርሃትና በአላስፈላጊ ጭንቀት ሳንደናገጥ አስፈላጊ የሆነውን ጥንቃቄ በማድረግ መከላከል ይኖርብናል፡፡ ሙያውን የገለጸው ራሱ እግዚአብሔር ነውና የባለሙያዎችን ምክር ሳናቃልል በተግባር በማዋል በዋናነት ግን ከመቸውም በበለጠ ሃይማኖታችንን በማጽናት እግዚአብሔርን ልንለምነው ይገባል፡፡ በሃይማኖት ጸንተን በጎ ምግባር እየሠራን የምንጋፈጣቸው ችግሮች በስተጀርባቸው በረከት ይዘው ይመጣሉና አደገኛነቱን ብቻ ሳይሆን በሃይማኖት ጸንተን ብንቀበለው በረከት እንዳለውም ማሰብ ይኖርብናል፡፡ እንዲሁ በቸልተኝነት ሳንመለከት ወደ እግዚአብሔር እየጸለይን የሚመጣውን በጸጋ መቀበል በኃጢታችን የመጣም ከሆነ አቤቱ ይቅር በለን በማለት መዓቱን በምሕረት እንዲመልስን መለመን ግድ ይለናል፡፡

ኢትፍርሕዎ ለሞት ፍርሕዋ ለኃጢአት፤ቅዱስ ያሬድ

ሞት በብዙ መንገድ ቢተረጎምም ቀጥተኛ ትርጉሙ ግን መለየት ማለት ነው፡፡ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ በሚል መጽሐፋቸው “መሞት፣ መለየት፣ በነፍስ ከሥጋ፣ በሥጋ ከነፍስ መራቅ፣ እየብቻ መኾን፣ መድረቅ፣ መፍረስ፣ መበስበስ፣ መነቀል፣ መፍለስ፣ መጥፋት፣ መታጣት” በማለት ይፈቱታል፡፡ (ኪዳነ ወልድ፣ገጽ፣፭፻፹፩) እንዲሁም አለቃ “ሞት በቁሙ የሥጋዊና የደማዊ ሕይወት ፍጻሜ በአዳም ኃጢአት የመጣ ጠባይዓዊ ዕዳ ባሕርያዊ ፍዳ” በማለት ይፈቱታል፡፡ (ዝኒ ከማሁ)

“በሕይወት መኖር የሚፈልግ ከክፉ ይሽሽ መልካሙንም ያድርግ”

በዚህ ወቅቱ ዓለም በከባድ እና አስቸጋሪ ፈተና ውስጥ ነው፡፡ ይህን ቸነፈር በሰው ጥንቃቄ ብቻ መቋቋም የሚቻል አይደለም፡፡ ሆኖም በግዴለሽነት እንዳንጓዝ ይልቁንም አስፈላጊውን ሁሉ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባን ቅዱሳት መጻሕፍት ይመክሩናል፡፡ በሃይማኖት ጸንተው በምግባር ቀንተው፣ ጥንቃቄም አድርገው የኖሩ አባቶቻችን በነፍሳቸውም፣ በሥጋቸውም ድነዋል፡፡ እኛም አባቶቻችንን አብነት አድርገን በነፍስም በሥጋም እንድንድን ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል፡፡

‹‹መኑ ውእቱ ገብር ኄር፤ ታማኝ አገልጋይ ማነው?›› (ማቴ.፳፬፥፵፭)

‹‹ገብር ኄር ወምእመን ዘበሁድ ምእምነ ኮንከ ዲበ ብዙህ እሰይመከ ባዕ ውስተ ፍስሐሁ ለእግዚእከ፤ አንተ ታማኝ ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃል፤ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ››

‹‹ስለማስመሰል ርኅራኄው ሰይጣንን ተጠንቀቀው›› ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

የሰይጣን የማስመሰል ርኅራኄው የቱን ያህል አሳሳች እንደሆነ እንኳን አንረዳውም፡፡ ካሳተን በኋላም ያሳተን እርሱ መሆኑን መረዳት እየተሳነን ለውድቀታችን ሰዎችን፣ ዕድልን፣ ሁኔታዎችን እና ጊዜን ሰበብ እንድናደርግ ያደርገናል፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆነው በተለይ በየጠበሉ ‹‹እከሊት ናት መድኃኒት ያደረገችብሽ፤ እከሌ ነው መድኃኒት ያደረገብህ›› እያለ ራሱን ሲያጋልጥ የምንሰማው የሰዎች ታሪክ እማኝ ነው፡፡ ‹‹ሐሰተኛ ነውና፤ የሐሰት አባትም ነው›› እንደተባለው፡፡ (ዮሐ. ፰፥፵፬) በዚህ ሐሰተኛነቱም አንዳንዶችን የአጋንንቱን ምስክርነት አምነው እንዲካሰሱ ባስ ሲል ወደከፋ ነገር እንዲደርሱ ያደርጋቸዋል፡፡