ቅድስት
ቅድስት ማለት ‹የተለየች፣ የነጻች፣ የከበረች› ማለት ነው፡፡ ይኸውም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጾም የጀመረባት፣ ልዩ፣ የተቀደሰች፣ የከበረች፣ ንጹሕ፣ ክቡር በሚሆን በጌታችን የተጾመች መሆኗን ያመላክታል፡፡ ይህች ጾም በማቴዎስ ወንጌል የተገለጠች ስትሆን፣ አምላካችን በገዳመ ቆሮንቶስ ዐርባ መዓልትና ዐርባ ሌሊት በጾመበት ጊዜያት ሦስቱን አርእስተ ኃጣውእ ድል አድርጓል፡፡ (ማቴ.፬፥፪)



