ልደቱ ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት
ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር ሆኖ የሥላሴን መንበር ያጠነው ጻድቁ አባት አቡነ ተክለ ሃይማኖት የተወለዱበት ዕለት የተቀደሰች ናት፤ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ለአባታቸው ካህኑ ጸጋ ዘአብና ለእናታቸው ቅድስት እግዚእ ኀረያ ባበሠራቸው መሠረትም በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ልዩ ስሙ ኢቲሳ በሚባል ቦታ በታኅሣሥ ፳፬፤ ፲፪፻፲፪ ዓ.ም ተወለዱ፡፡ በሦስተኛው ቀን እሑድ ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው ‹‹አሐዱ አብ ቅዱስ፤ አሐዱ ወልድ ቅዱስ፤ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ፤ አንዱ አብ ቅዱስ ነው፤ አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው፤ አንዱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነው›› በማለት ሥላሴን አመስግነዋል፡፡