ዝርወተ አጽሙ ለቅዱስ ጊዮርጊስ
…ከዚህም በኋላ ቅዱሱን ወስደው በጐድጓዳ ብረት ምጣድ ውስጥ አበሰሉት፡፡ አቃጥለው አሳርረውም ሥጋውንና ዐጥንቱን ፈጭተው አመድ አድርገው ከረጅም ተራራ ላይ በተኑት፡፡ ይህም የሆነው ጥር ፲፰ ቀን ነው፡፡…
…ከዚህም በኋላ ቅዱሱን ወስደው በጐድጓዳ ብረት ምጣድ ውስጥ አበሰሉት፡፡ አቃጥለው አሳርረውም ሥጋውንና ዐጥንቱን ፈጭተው አመድ አድርገው ከረጅም ተራራ ላይ በተኑት፡፡ ይህም የሆነው ጥር ፲፰ ቀን ነው፡፡…
በሮም ግዛት በሚገኝ አንጌቤን በሚባል ሀገር በፈሪሃ እግዚአብሔር፣ በክርስትና ሃይማኖት እና በበጎ ምግባር ጸንታ ትኖር የነበረች ኢየሉጣ የተባለች ደግ ሴት ነበርች፡፡ እርሷም ቂርቆስ የተባለ በሥርዓት ያሳደገችው ሕፃን ልጅ ነበራት፡፡ በዚያን ዘመን እለእስክንድሮስን የተበላ አረማዊ መኰንን ነበር፤ ይህችም ቅደስት ከልጇ ጋር ከሮም ወደ ጠርሴስ ተሰደደች፡፡…
የጻድቁ የአቡነ አረጋዊ አባት ይስሐቅ እናቱም እድና ይባላሉ፡፡ ሁለቱም እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚያከብሩ ነበሩ፡፡ እግዚአብሔር አምላክም የተባረከውን ልጅ ሰጣቸው፤ይህም የሆነው በጥር ፲፬ ቀን ነው፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም እና ከቅዱሳን ሐዋርያቱ ጋር በመሆን በገሊላ አውራጃ በቃና መንደር በሠርግ ቤት ተገኝቶ ቤተ ከብካቡን በትምህርቱ በተአምራቱ ባረከ።በጥምቀት በዓል ማግስት ጥር ፲፪ ቀን ይህንኑ ጠብቀን በዓሉን እናከብራለን፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዮርዳኖስን ብርህት ማኅፀን እንድትሆን፣ ምእመናንም ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ፣ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ዳግም ተወልደው መንግሥተ ሰማያት እንዲገቡ እንደዚሁም ሥርዓተ ጥምቀትን ለማስተማርና አብነት ለመሆን በጥር ዐሥራ አንድ ቀን ተጠምቋልና ይህችን የተከበረች ቀን ሕዝበ ክርስቲያን ያከብር ዘንድ ይገባል፡፡
የተከበራችሁ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ? እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ! ልጆች! የጌታችንን የልደት በዓልን እንዴት አሳለፋችሁ? በሰላም እንዳሳለፋችሁ ተስፋችን ነው፤ ትምህርትስ እንዴት ነው? የግማሽ መንፈቀ ዓመት ፈተናም እየደረሰ ነውና በርትታችሁ አጥኑ!
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! ዛሬ ደግሞ ስለ ጥምቀት በዓል እንማማራለን፡፡ ጥምቀት ማለት ‹‹አጥመቀ- አጠመቀ›› ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ‹‹መነከር፣ መድፈቅ፣ በተባረከው ውኃ ጸበል ውስጥ ሦስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ›› ማለት ነው፤ እንግዲህ በዛሬ ትምህርታችን ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት እንመለከታለን፡፡
አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ በኃጢአት የተገነባውን የሰናዖር ግንብ ያፈረሱበት አንድነታቸውንና ሦስትነታቸውን በግልጽ ያሳዩበት ጥር ሰባት ቀን የከበረ በዓል እንደመሆኑ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡ታሪኩ በኦሪት ዘፍጥረት ላይ እንደተጻፈ እንዲህ ይነበባል፡፡…
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ ግዝረት በመግባት የኦሪት ሕግ የሆነውን ግዝረት የፈጸመበት ዕለት ጥር ስድስት ቀን በቤተ ክርስቲያናችን ይከበራል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ጌታ ክርስቶስ በሥጋ ግዝረትን ተቀበለ፣ ለአባቶች የተሰጠውን ቃልኪዳን ይፈጽም ዘንድ›› ብሎ መስክሯል፡፡ (ሮሜ ፲፭፥፰)
የዳሞት አውራጃ ገዚ ሞተለሚ በነበረበት ቡልጋ ደብረ ጽላልሽ በኢቲሳ መንደር ካህኑ ጸጋዘአብና እግዚኀረያ በትዳር ተወስነው ይኖሩ ነበር። ጸጋ ዘአብ በክህነቱ እግዚኀረያ በደግነቷና በምጽዋት ጸንተው በመኖራቸው በሕጉና በሥርዓቱ ለሚኖሩት ቀናዒ በመሆኑ እግዚአብሔር አምላክ ጎበኛቸው። ሃይማኖታቸውን የሚረከብ፣ እንዳባቱ ጸጋዘአብ የሚባርክ የአብራካቸውን ክፋይ ሊሰጣቸው ወደደ።
ብሥራታዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጦ ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ መወለድ ያበሠራት ዕለት ታኅሣሥ ፳፪ ‹‹ብሥራተ ገብርኤል›› ታላቅ በዓል ነው፡፡