ሲመቱ ለሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕታት ቅዱስ እስጢፋኖስ

የስሙ ትርጓሜ ‹አክሊል› የሆነው በሕገ ወንጌል የመጀመሪያ ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳማዊ ሰማዕት የተባለ ቅዱስ እስጢፋኖስ ‹‹ሊቀ ዲያቆናት›› ከመባሉ በፊትም በመጀመሪያ ሐዋርያና ካህን ነበር፤ ከዚያም ዲያቆን ሆኖ ተሾሟል፤ ይህም ጥቅምት ፲፯ ቀን ነው፡፡

ዕረፍቱ ለሊቀ ጳጳስ አባ ድሜጥሮስ

ቅዱስ ድሜጥሮስ የእስክንድርያ ዐሥራ ሁለተኛ ጳጳስ ከመሆኑ በፊት የቤተ ክርስቲያን ዕውቀት ያልነበረው በግብርና ሥራ የሚተዳደር ሰው ነበር፡፡አባቱ ደማስቆ ወይም እንድራኒቆስ አጎቱ ደግሞ አርማስቆስ ወይም አስተራኒቆስ ይባላሉ፡፡ ሁለቱም በዘመነ ሰማዕታት ከኢየሩሳሌም ርቀው በባዕድ ሀገር በፋርስ ባቢሎን በስደት ለረጅም ዘመናት ይኖሩ ነበር፡፡ በዚህ የስደት ዘመናቸው ከሁለቱ (ደማስቆና አርማስቆስ) በስተቀር በሀገሩ የሚኖሩት አሕዛብ ነበሩ፡፡…

ክብረ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

በምድረ በዳ እንደመላእክት የኖሩትና በዝቋላ ተራራ ባለው ባሕር ውስጥ ፻ (መቶ) ዓመት ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ሰዎች ምሕረትን የለመኑት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዕረፍታቸው እንዲሁም ቃል ኪዳን የተቀበሉበት ዕለት በሀገራችን ኢትዮጵያ በድምቀት ይከበራል፡፡

ጼዴንያ ማርያም

የሁሉ አምላክን በማኅፀኗ የተሸከመችው ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያምም በሥዕሏ ወዝ ብዙ ሕሙማንን ትፈውሳለች፡፡ ከቅዱሳን ልብስና ጥላ የእርሷ ሥዕል ይከብራልና በየዓመቱም መስከረም ፲ ቀን ቤተ ክርስቲያናችን ከእመቤታችን ፴፫ቱ በዓላት ውስጥ አንዱ አድርጋ በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡

በዓለ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ

…በዚያችም ቀን የቅዱስ ዮሐንስ ራስ ከሄሮድያዳ እጆች ላይ ወደ አየር በረረች።….

ርእሰ ዐውደ ዓመት

በጊዜ ሥጦታ ቀናት ተፈጥራዊ ዑደትን ተከትለውና ወራትን ተክተው ዘመንን ይፈጥራሉ፤ የዘመናት ለውጥም አዲስ ዓመትን ይተካሉ፤ ይህ ሁሉ ግን በእግዚአብሔር አምላክ ቅዱስ ፈቃድ ሆነ፤ እኛም ለአዲሱ ዓመት ዘመነ ማርቆስ እንደ ቸርነቱ ደረስን፡፡…

መልእክት

ክርስቶስ በከበረ ደሙ የዋጃችሁ ሃይማኖታችሁ የቀና የተወደዳችሁ ምእመናን ሆይ ልዑል እግዚአብሔርን ልናመሰግነው ይገባናል። በይቅርታው ገናናነት በጎ የሆኑትን ሁሉ ስለሰጠን የልዕልናውን ምስጋና ጨምረን እጅግ ልናበዛ ይገባናል። እስከዚህች ዕለትና ሰዓት  አድርሶናልና።…

‹‹እኔ ሩፋኤል ነኝ››

በሃያ ሦስቱ የመላእክት ነገደ ሠራዊት ላይ እግዚአብሔር የሾመኝ እኔ ሩፋኤል ነኝ፤ እግዚአብሔር አብን ይቅር ባይ ልጁን አጽናኝና አዳኝ የሆነ መንፈስ ቅዱስን እናመሰግነው ዘንድ፤ በደብረ ጽዮን በሚደረገው የሺህ ዓመት ተድላ ደስታ የክብር ጽዋን በሚሰጣቸው ጊዜ ለቅዱሳኖቹ በጎ ነገርን እንድንሰጣቸው ያዘዘኝ ሩፋኤል እኔ ነኝ፡፡ ደግሞም በዚህች ቀን ከዕፀ ሕይወት ዐጽቅ ወስጄ ለተመረጡ ክርስቲያኖች በእጄ እንድንሰጣቸው እግዚአብሔር ያዘዘኝ ሩፋኤል እኔ ነኝ፡፡የሰማያት መዛግብትም ከእጄ በታች ተጠብቀው የሚኖሩ እኔ ሩፋኤል ነኝ፡፡ እኔም እግዚአብሔር እንዳዘዘኝ እከፍታቸዋለሁ፤ እዘጋቸዋለሁም፡፡

‹‹በእግዚአብሔር ትእዛዝ ሦስት መቶ ሰባ ሁለት ዓመት ተኙ››

….እግዚአብሔር እውነቱን ሊገልጥ እና የሙታን ትንሣኤ በእርግጠኝነት እንደሚከናወን ሰዎችን ለማሳመን ፈለገ፤ እናም እነዚያን ሰባት ቅዱስ ወጣቶች ከእንቅልፉ አነቃቸው።….

‹‹ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል›› (መዝ. ፹፰፥፲፪)

በትንቢት ‹‹ታቦርና አርሞንኤም በስም ደስ ይላቸዋል›› ብሎ ነቢዩ ዳዊት እንደተናገረው ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን፣ ክብረ መንግሥቱን መግለጡን በማሰብ በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን በዓሉ በድምቀት ይከበራል፡፡ (መዝ. ፹፰፥፲፪)