ዘመነ መስቀል
መስቀል በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ለዕርቅ የተተከለ ትእምርተ ፍቅር ነው፡፡ በመስቀል የነፍስና የሥጋ መርገም የተሻረበት በመሆኑ ሰው ሁሉ ለችግሩ መጽናኛ ማግኘትና ነፍሱን ማትረፍ የሚችለው መስቀልን በጽናት ተስፋ አድርጎ ሲቆም ነው፡፡
መስቀል በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ለዕርቅ የተተከለ ትእምርተ ፍቅር ነው፡፡ በመስቀል የነፍስና የሥጋ መርገም የተሻረበት በመሆኑ ሰው ሁሉ ለችግሩ መጽናኛ ማግኘትና ነፍሱን ማትረፍ የሚችለው መስቀልን በጽናት ተስፋ አድርጎ ሲቆም ነው፡፡
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁልን? እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም አሸጋገራችሁ! አዲሱን ዓመት ከተቀበልን ሳምንታትን አስቆጥረን ወር ሊሞላን ጥቂት ቀናት ብቻ ቀሩን! አዲሱ የትምህርት ዘመን እንዴት ነው? ትምህርት ጀመራችሁ አይደል? በርቱ!
ታዲያ ልጆች! ቤተ ክርስቲያን በመሄድ መማርንም እንዳንዘነጋ! በሰንበት ሄደን በመማር በሥነ ምግባር ያጌጠ፣ በሃይማኖቱ የጸና ጎበዝ ሆነን ማደግ አለብን፤ መልካም! ለዛሬ ይዘንላችሁ የቀረብነው “የቱን ታስታውሳላችሁ” በሚል ርእስ እስከ ዛሬ ትማሩት ከነበረው የተወሰነ ጥያቄዎችን አዘጋጅተን ነው፤ ምላሽችሁን ደግሞ በድረ ገጽ አድራሻችን “website.amharic@eotcmk.org” እና “https://t.me/Hiwot122716” ትልኩልናላችሁ!
‹‹ተቀጸል ጽጌ›› ማለት ‹‹አበባን ተቀዳጅ›› ማለት ሲሆን በዘመነ አክሱም በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በነበሩት በዐፄ ገብረ መስቀል የተጀመረ በዓል ነው፡፡ ይህ የተቀጸል ጽጌ በዓል የክረምቱን መውጣት መሠረት አድርጎ መስከረም ፳፭ ቀን የሚከበር በዓል ሲሆን ሕዝቡ በክረምቱ ምክንያት፣ በዝናቡ ብዛት፣ በወንዙ ሙላት ተለያይቶ ይከርም ነበርና ለንጉሠ ነገሥቱ የአበባ አክሊል/ጉንጉን/ ሠርቶ በማምጣት የሚያበረክትበት በዓል ስለነበረ ‹‹ተቀጸል ጽጌ ገብረ መስቀል ሐፄጌ፤….ዐፄ ገብረ መስቀል አበባን ተቀዳጅ›› እየተባለ ይዘመር ነበር፡፡
የመስከረም ወር የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ አባት ዕረፍት የሚታሰብበት ወር ነው፡፡ መስከረም ፰ ቀን ደግሞ የበራክዩ ልጅ ካህንና ነቢይ የነበረ ዘካርያስ በሄሮድስ እጅ በሰማዕትነት ያረፈበት ነው፡፡
መስከረም ለሚለው ቃል መነሻ “ከረመ” የሚለው ግስ ነው፤ ትርጓሜውም “ቀዳማይ፣ ለዓለም ሁሉ መጀመሪያ፣ ርእሰ ክራማት፣ መቅድመ አውራኅ” የሚለውን ያመለክታል፡፡ በሌላ በኩል መስከረም የመጀመሪያ ወር ስም፣ ከዘመነ ሥጋዌ በፊትም ለዓለም ሁሉ የመጀመሪያ ወር ማለት ነው፤ “መስ” የሚለው ቃልም መነሻ መስየ የሚለው ግስ ሲሆን “ምሴተ ክረምት (የክረምት ምሽት) በምሥጢር ደግሞ ፀአተ ክረምት (የክረምት መውጫ)፣ የክረምት ጫፍ መካተቻ፣ የመፀው መባቻ” መሆኑን ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመዝገበ ቃላታቸው ይገልጣሉ፤ (ገጽ ፮፻፲፪) እንዲሁም “መቅድመ አውራኅ (የወራት መጀመሪያ) ርእሰ ክራማት” ይሰኛል ይላሉ፡፡
ለዘመኑ ጥንት ፍጻሜ የሌለው ጌታ የጨለማውን ጊዜ ክረምቱን አሳልፎ፣ ዘመንን በዘመን ተክቶ፣ ምድርን በእህል (በሰብል) ሸፍኖ፣ ድርቀቷን በአረንጓዴ ዕፅዋት አስውቦ፣ ብሩህ ተስፋን በሰው ልጆች ልቡና ያሠርፃል፤ አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር ሰዎች በአዲስ መንፈስና ዕቅድ በአዲስ ሰብእና፣ በዕድሜ ላይ በተጨመረው ሌላኛው ዘመን ዕቅዳቸውን ለማሳካት፣ ምኞታቸውን ለማስመር ታትረው ይነሣሉ፤ የወቅቱ መቀየር በራሱ አዲስ ነገር እንዲያስቡ ያነቃቃል፤ በአዲስ ዓመት መግቢያ (በርእሰ ዐውደ ዓመት) የአጽዋማት መግቢያ፣ የበዓላት መከበሪያ ቀንና ዕለት ይታወጁበታል፤ ባለፈው ዓመት ዘመኑን በስሙ ተሰይሞለት የነበረው ወንጌላዊ ለተረኛው ማስረከቡን ይበሠርበታል፡፡
ወርኃ ጳጉሜን በዓመቱ መጨረሻ የምትገኝ በአገራችን ኢትዮጵያ እንደ ዐሥራ ሦስተኛው ወር የምትቆጠር ናት፤ ወርኃ ጳጉሜን አምስት ቀናት ያሏት ስትሆን በአራት ዓመት አንድ ጊዜ በዘመነ ሉቃስ መውጫ በዘመነ ዮሐንስ መግቢያ ያለው ስድስት ቀን ይሆናል፡፡ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመዝገበ ቃላታቸው ጳጉሜን እንዲህ ይተረጉሟታል፤ ጳጉሜን ማለት ጭማሪ ተውሳክ፣ አምስት ቀን፣ ከሩብ፣ ከዐውደ ወር ተርፎ በዓመቱ መጨረሻ የተጨመረ ስለሆነ ትርፍ ተጨማሪ ማለት ነው፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት፣ ገጽ ፱፻፭)
በሰማይና ምድር በሚገኙ ፍጥረታት ሁሉ ምስጉን የሆነ እግዚአብሔር የቤተ ክርስቲያንን ውበት እንድንመለከትባቸውና እግዚአብሔርን ለማመስገን እንድንሰባሰብባቸው ምክንያት አድርጎ ከሰጠን ቅዱሳን አባቶች መካከል ታላቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንዱ ናቸው፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ጸጋዎች ባለቤት ናት፡፡ በብዙ ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ ጸጋዎች የተሞላች ግን ደግሞ በውል ይህን እውነት የማንረዳ ብዙ ዜጎችም ያላት ሀገር ናት፡፡ “አንድ ሰው ጸጋውን የሚያውቀው ሲያጣው ነው” እንደሚባላው መንፈሳዊና ቁሳዊ፣ ተፈጥሯዊና ሰው ሠራሽ ጸጋዎቿን የምንረዳበትና ጠብቀን ተንከባክበን የምንጠቀምበት ዘመን ይመጣ ዘንድ እንመኛለን፡፡
የዚህች ሀገር ልዩ ጸጋዎች ከሆኑት መካከል ወቅቶች አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ ምክንያቱም የዐሥራ ሦስት ወር ጸጋ የታደለች በክረምትና በበጋ፣ በጸደይና በበልግ በዐሥራ ሦስት ወር ወራት የተዋቀረ፣ ለሰው ልጆች ሁሉ ተስማሚ ወቅት ያላት ሀገር በመሆኗ ይህ በብዙዎች ዘንድ የማይገኝ ጸጋ ነው፡፡
ሥራው ግሩም የሆነ አምላካችን እግዚአብሔር ማዳንም መግደልም የሚችል የባሕርይ አምላክ ነው፡፡ (መዝ.፷፭፥፫) በእርሱ የሚታመኑት ቅዱሳን ሰማዕታት የሚደርስባቸውን መከራና ፈተና ሁሉ በጽናት፣ በልበ ሙሉነት የሚያልፉት ለዚህ ነው፡፡…ወርቅና ብር በእሳት ተፈትነው እንደሚጠሩ ቅዱሳን ሰማዕታትም በመከራ ውስጥ ተፈትነው እግዚአብሔርን አስደስተው ለእኛም የጽናት ምልክት ሆነው የክብር አክሊልን በመቀዳጀት ከገቡ መውጣት፣ ካገኙ ማጣት እና መከራ ወደ ሌለበት ዘለዓለማዊ ማረፊያቸው ይሄዳሉ፡፡