ጾመ ፍልሰታ

አምላክን የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ከዕረፍቷ በኋላ ከእርሳቸው ስለመለየቷ ሐዋርያት ፈጽሞ እያዘኑ ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ተገለጠላቸው፤ እርሷን በሥጋ ያዩ ዘንድ እንዳላቸውም ተስፋ ሰጣቸው፡፡

ወንጌላዊ ዮሐንስም እስያ በሚባል አገር እያስተማረ ሳለ በነሐሴ ወር ዐሥራ ስድተኛ ቀን ተድላ ደስታ ወደአለባት ገነት በመንፈስ ቅዱስ ተነጠቀ፡፡ የክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ካለበት ከዕፀ ሕይወት ዘንድ ተቀምጦ አየው፡፡ የንጽሕት እናቱንም ሥጋ ታወጣ ዘንድ ምድርን እንዲጠሩዋት ሰባቱን የመላእክት አለቆች አዘዛቸው፤ እነርሱም ”የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጪ ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል‘ አሏት፡፡ያን ጊዜም ከዕፀ ሕይወት በታች ካለ መቃብር የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ወጣ፡፡…

‹‹ዑራኤል የተባለ መላእክ ሊረዳኝ መጣ›› (ዕዝ.ሱቱ ፪፥፩)

በመከራ ጊዜ ረዳት የሆነው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ዑራኤል በዘመናት ለነገሡ የሀገራችን ነገሥታት ያደረገው ውለታ እጅግ ብዙ ነው፡፡ ዳግማዊ ቆስጠንጢኖስ የተባለ ንዋየ ማርያም በነገሠበት ዘመነ መንግሥት ቅዱስ ዑራኤል በጸሎቱ በመራዳትና እስከ ግዛቱ ፍጻሜ ባለመለየት ሀገሩን እንዲመራ አድርጓል፡፡…

ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም

ሜሶፖታሚያ በምትገኝ ንጽቢን ከተማ ከዋክብትን ከሚያመልኩ ሰዎች መካከል በ፫፻፮ ዓ.ም ገደማ የተወለደው ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም አባቱ ክርስትናን የሚጠላ ሰው እንደነበር ይነገራል፡፡ እንዲያውም ካህነ ጣዖት ስለመሆኑ መጽሐፈ ስንክሳር ይጠቅሳል፡፡ (ስንክሳር ሐምሌ ፲፭)

ዕረፍተ አባ ኪሮስ

በሀገረ ሮም ከአባቱ ንጉሥ አብያ ከእናቱ አንሰራ ተወለደ፡፡ ደጋግና ቅዱሳን ወላጆቹም እግዚአብሔርን በመፍራት እየኖሩበት በነበረበት ወቅት ይህን የተመረጠ አባት ሰጣቸው፤ አባ ኪሮስ የተወለደው በታኅሣሥ ፰ ቀን ነበር፡፡ ጻድቁ አባት በቅድስና ሕይወትና ትጋት ማዕረግ አባ ኪሮስ ከመባሉ በፊት ‹ዲላሶር› ተብሎ ይጠራ እንደነበር ታሪኩ ይገልጻል፡፡

ሁለቱ የቤተ ክርስቲያን አዕማዶች

ቅዱሳኑ ሐዋርያት ጴጥሮስና ጳውሎስ የእግዚአብሔርን ቃል ለዓለም የሰበኩ፣ ብዙዎችን በክርስትና ጥምቀትና በገቢረ ተአምራት ያዳኑ የቤተ ክርስቲያን አዕማዶች ናቸው፡፡

ልደቱ ለቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ

ከካህን አባቱ ዘካርያስና ከቅድስት እናቱ ኤልሣቤጥ የተወለደው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የስሙ ትርጓሜ ‹‹ፍሥሐ፣ ሐሴት፣ ርኅራኄ›› ነው። የመወለዱም ነገር እንዲህ ነው፤ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል በአምላኩ ትእዛዝ ወደ ዘካርያስ በመምጣት በመጀመሪያ በመሠዊያው በስተቀኝ በኩል ተገልጦ ታየው፡፡ ከዚያም ‹‹ዘካርያስ ሆይ፥ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ፤ ደስታና ተድላም ይሆንልሃል፡፡ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል፡፡ እርሱ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ይሆናልና የወይን ጠጅና የሚያሰክርም መጠጥ ሁሉ አይጠጣም፤ ከእናቱ ማሕፀን ጅምሮም መንፈስ ቅዱስ ይመላበታል፡፡…

ነቢዩ ኢያሱ ወልደ ነዌ

የነዌ ልጅ ኢያሱ የታላቁ ነቢይና መስፍን የነቢያት አለቃ የሙሴ ደቀ መዝሙር የነበረ በኋላም እግዚአብሔር የመረጠው ነቢይ ነው፡፡ የስሙ ትርጓሜም‹‹ እግዚአብሔር አዳኝ›› ማለት ነው፤ ‹‹የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ከሞተ በኋላ እግዚአብሔር የሙሴን አገልጋይ የነዌን ልጅ ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው። ባሪያዬ ሙሴ ሞቶአል፤ አሁንም አንተና ይህ ሕዝብ ሁሉ ተነሥታችሁ ለእስራኤል ልጆች ወደምሰጣቸው ምድር ይህን ዮርዳኖስ ተሻገሩ። ለሙሴ እንደ ነገርሁት የእግራችሁ ጫማ የሚረግጠውን ቦታ ሁሉ ለእናንተ ሰጥቼአለሁ።…

ሐዋርያው ይሁዳ

በስመ ይሁዳ የሚጠሩ በርካታ የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ ተጠቃሾች ቢኖሩም በሰኔ ፳፭ ቀን ቤተ ክርስቲያናችን የምታከብረው ሐዋርያው ይሁዳ ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ የሆነው የፀራቢው የዮሴፍ ልጅ እንዲሁም ያዕቆብ ለተባለው ሐዋርያ ወንድም ነው፡፡ አስቀድሞም ስሙ ታዴዎስ ይባል ነበር፡፡ ይህም ሐዋርያ ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ በኋላ ያመነና በብዙ ሀገሮች የሰበከ ነው፤ ከእነርሱም መካከል በአንዲት ዴሰት ገብቶ በማስተማር በዚያ የነበሩትን ሰዎች በጌታችን ስም አሳምኖ ቤተ ክርስቲያን እንደሠራላቸውና በቀናች ሃይማኖትም አጽንቷቸዋል፡፡

‹‹ሙሴ ሆይ፥ እነሆ በውስጥም በውጭም ሁለመናህ ነጭ ሆነ››

ሰዎች ከገድሉ የተነሣ የሚያደንቁት ኢትዮጵያዊው ቅዱስ አባት አባ ሙሴ ጸሊም አስቀድሞ ለሥጋው የሚኖር ወንበዴና አመንዛሪ እንዲሁም ቀማኛ ነበር፡፡ እንዲያውም የሥጋውን መሻት ለመፈጸም ሰዎችን እስከ መግደል የሚደርስ ጨካኝ ሰው እንደነበር ገድሉ ይናገራል፡፡ መብልንና መጠጥንም ከልክ ባለፈ መልኩ ይወስዳል። መጽሐፈ ስንክሳር ላይ እንደተመዘገበው በአንድ ጊዜ አንድ ሙሉ በግ እና አንድ ፊቅን ወይን ጠጅ እንደሚጨርስ እራሱ ይናገር ነበር፡፡

‹‹ከአንተ በፊትም ከአንተ በኋላም የሚመስልህ የለም›› (፩ኛነገ.፫፥፲፪)

የጠቢቡ ሰሎሞን ጥብብ መደነቅና ተሰሚነት በሰዎች ዘንድ ብቻ አልነበረም፤ ‹‹አራዊትና ወፎች ሁሉ ወደ እርሱ ይመጡ፣ ቃሉን ይሰሙ፣ ጥበቡንም ያደንቁ፣ ከእርሱ ጋር ይነገጋሩና ወደ ሥፍራቸው ይመለሱ ነበር፡፡››