ማኅበረ ቅዱሳን የመኪና ስጦታ ተበረከተለት
ሰኔ 20 ቀን 2004 ዓ.ም. በእንዳለ ደጀኔ ማኅበረ ቅዱሳን የጀመረውን ዓለም አቀፍ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት አጠናክሮ መቀጠል እንዲችል የሚያግዘው የመኪና ስጦታ ተበረከተለት፡፡ መኪናውን ለማኅበሩ ያበረከቱት ዶ/ር አንተነህ ወርቁና ዶ/ር ሰላማዊት እጅጉ ሲሆኑ ያዘጋጁትን ስጦታ በዶ/ር ሰላማዊት ወላጅ አባት በአቶ እጅጉ ኤሬሳ አማካኝነት አበርክተዋል፡፡ የመኪናውን ቁልፍ የተረከቡት የማኅበረ ቅዱሳን ም/ሰብሳቢ አቶ ታደሰ አሰፋ ‹‹ማኅበራችን ማኅበረ ቅዱሳን […]

በዮሴፍ ወልደ ያዕቆብ ዘመን የነበረው ፈርኦንና የመጥምቁ ዮሐንስን አንገት ለዘፋኝ ወሮታ የሰጠው ሄሮድስ የሚያመሳስላቸው አንድ ዓይነት ተግባር ፈጽመዋል:: ይኽውም ሁለቱም ልደታቸውን ያከብሩ እንደነበር በመጽሐፍ ቅዱስ መጠቀሱ ነው:: /ዘፍ.40፥20 ፤ ማቴ.14፥6/:: ታሪካቸውን ስናጠና ደግሞ በርካታ መመሳሰል እንደነበራቸው እንገነዘባለን:: ሁለቱም ነገሥታት ናቸው:: ሁለቱም ንጹሐንን አስረዋል:: ሁለቱም ደም አፍሳሾች ነበሩ:: በልደት በዓላቸውም ነፍስ አጥፍተዋል:: በልደት በዓላቸው ነፍስ ያጠፉ ሰዎች ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ መጻፉ የልደት በዓል ማክበርን ስህተት አያደርገውም:: በጌታችን ልደት መቶ አርባ አራት ሺህ ሕጻናት በሄሮድስ ትእዛዝ ተገድለዋል:: የጌታችንን ልደት ግን እናከብራለን:: መግደል ኃጢአት መሆኑን እንመሰክርበት ካልሆነ በቀር ነፍስ በማጥፋት የሚከበር በዓል የለንም:: የፋሲካን በዓል በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ለማክበር እንገደዳለን እንጂ ዘፋኞች ድግስ ስለሚያዘጋጁበት ማክበሩ ቢቀር ቢባል ሞኝነት ነው:: ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን የቅዱሳንን ልደት በዓል ስታከብር የራሷ ሥርዓትና ባሕል የበዓላት መቁጠሪያ /ሊተርጂካል ካላንደር/ አላት:: የቱ መቼ መከበር እንዳለበትም ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ታስረዳለች:: ጥንታዊት ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን እንደመሆንዋም በርግጥኝነት ዕለታቱን ቆጥራ ትናገራለች:: በነቢይ የአዋጅ ነጋሪ ቃል ተብሎ የተነገረለት የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስን የልደት በዓል የምታከብረው በሰኔ ሠላሳ ቀን ነው::
የጥናትና የውይይት መድረክ ሰኔ 16 ቀን 2004 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም አዲሱ አዳራሽ አዘጋጅቷል፡፡
