የለንደን ደ/ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እንደገና ተከፍታ አገልግሎት መስጠት ጀመረች
ታኅሣሥ 25 ቀን 2006 ዓ.ም.
ከUK ቀጠና ማዕከል
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትን እና ምእመናንን ባሳዘነ ሁኔታ ከዘጠኝ ወራት በላይ ተዘግታ የቆየችው የለንደን ርእሰ አድባራት ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እሁድ ታኅሣስ ፳ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ እንጦንስ በተገኙበት በይፋ እንደገና ተከፍታ አገልግሎት መስጠት ጀመረች።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን ‹‹የአብነት መምህራንና ተማሪዎችን ጤና ለመጠበቅ›› በሚል ከታኅሣሥ 1 እስከ ጥር 6 ቀን 2006 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ መርሐ ግብር አዘጋጀ፡፡
በማኅበረ ቅዱሳን የኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ክፍል መደበኛና ኢ-መደበኛ አባላት በአገልግሎት ዙሪያ ለመወያየትና ከጽርሐ ጽዮን ዘተዋሕዶ የአንድነት ኑሮ ማኅበር አባላት ጋር የልምድ ልውውጥ ለማድረግ እንዲቻል ከአዲስ አበባ በምዕራብ አቅጣጫ ቡራዩ አካባቢ ወደሚገኘው ጽርሐ ጽዮን ዘተዋሕዶ የአንድነት ኑሮ ማኅበር መንደር ታኅሣሥ 12 ቀን 2006 ዓ.ም. የጉዞ መርሐ ግብር አካሒዷል፡፡
ታኅሣሥ 12 በብፁዕ አባታችን አቡነ ማትያስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የካናዳና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በጸሎት የተከፈተ ሲሆን፤ በመርሐ ግብሩ ላይ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ጠረፋማ አካባቢዎች ከደቡብ ኦሞና ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ወረዳዎች ተጋብዘው የመጡ ከዚህ በፊት በሀገረ ስብከቱና በማኅበረ ቅዱሳን ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ በጋራ ተምረውና ተጠምቀው የነበሩ አገልጋዮችና ምእመናን ተገኝተዋል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ለአምስተኛ ጊዜ ያዘጋጀው የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር በደብረ ዘይት ከተማ ደብረ መድኀኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ታኅሣሥ 6 ቀን 2006 ዓ.ም. ከ6000 በላይ ምእመናን በተገኙበት በድምቀት አካሔደ፡፡
