Entries by Mahibere Kidusan

ለአንዲት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድ ሲኖዶስ

                              ለአንዲት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድ ሲኖዶስ! በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የማኅበራት ኅብረት  በቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል ስለሚካሄደው እርቀ ሰላምና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መግለጫ፡፡       ቅዱስ ሲኖዶስ ከቅዱሳን ሐዋርያት ጀምሮ የሊቃነ ጳጳሳት፤ የጳጳሳት እና የኤጲስ ቆጶሳት […]

 ኀበነ ንኅበር በዘዚአከ መንፈስ ቅዱስ- የአንተ በሆነ መንፈስ ቅዱስ አንድ መሆንን ስጠን!

በዐለም የክርስትና ታሪክ ውስጥ ምእመናን  ከተፈተኑበት ፈተናዎች አንዱ በአንድ በታወቀ መንበር ላይ ከአንድ በላይ ፓትርያርኮች ወይም ፖፖች መሾም ነው፡፡በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ቀድሞ በነበረ ፓትርያርክ ወይም ፖፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ተደርቦ እንደተሾመ የሚነገርለት ቅዱስ አቡሊዲስ ዘሮም ነው፡፡ ቅዱስ አቡሊዲስ (Hippolytus) ተቀናቃኝ ፖፕ የሆነበት መንገድ ከዘመኑ የተነሣ በታሪክ ብዙም ባይገለጽም ተቀናቃኝ ሆኖ የተሾመው ግን ካሊክሰቶስ ቀዳማዊ (Pope Callixtus […]

“በሰላም ማሠሪያ፣ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ» (ኤፌ 4፡3)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ “በሰላም ማሠሪያ፣ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ» (ኤፌ 4፡3) እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ፣ የትዕቢትን ነገር አታስቡ፣ ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ፡፡ ልባሞች የሆናችሁ አይምሰላችሁ፡፡ (ሮሜ.12፡16) ተብሎ እንደተጻፈ፡- የቅድስት ቤተክርስቲያን አገልግሎት፣ ምእመናንን ከማጠንከርና ከማብዛት አንፃር፣ ዘመኑን በዋጀ ሁኔታ መመራት ያለበት በመሆኑ፣ በዘፈቀደ ሳይሆን፣ እግዚአብሔርን አጋዥ አድርጐ በመግባባት፣ […]

የቀዳሜ አድባራት አበራ ጊዮርጊስ የቅኔ ጉባኤ ቤት የእሳት ቃጠሎ ደረሰበት

                                                         ዲ.ን ዘአማኑኤል አንተነህ                በጎንደር ከተማ የሚገኘው የቀዳሜ አድባራት አበራ ጊዮርጊስ ግንቦት 11 ቀን 2010 ዓ.ም ከቀኑ ሰባት ሰዓት የእሳት ቃጠሎ ደረሰበት፡፡ የጉባኤ ቤቱ አለቃ መምህር ናሆም አዝመራው […]

እምቤተ ክህነት ወመንግሥት ዘኀረይዋ ይእቲኬ ማርያም ድንግል

           በዲ/ን ታደለ ሲሳይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትኩረት አድርጋ የምታከብራቸው በርካታ የቅዱሳን በዓላት አሉ፡፡ የእመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም በዓላትም በቤተ ክርስቲያኗ ሰፊ ቦታ ተሰጥተው የሚከበሩ ናቸው፡፡ ለአብነት ያህልም በየዓመቱ ግንቦት አንድ ቀን የሚከበረውን የቅድስት ድንግል ማርያምን የልደት በዓል መመልከት ይቻላል፡፡ ለሃይማኖታችን መሠረት፣ ለክርስትናችን ዋስትና፣ ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ስንቅ የሆኑት […]

ማኅበረ ቅዱሳን 26ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን ሊያከብር ነው

ማኅበሩ ሚያዝያ 28 ቀን 2010 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ከመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም አጠገብ በሚገኘው ሕንጻ፣ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በዓለ ልደትና ማኅበሩ የተመሠረተበትን 26ኛ ዓመት የምሥረታ ቀን በመንፈሳዊ ሥርዓት እንደሚያከብር ከማኅበሩ የሕዝብ ግንኙነትና የትብብር አግልግሎት ማስተባበርያ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ክብረ ቅዱሳን እና ዐሥሩ መዓርጋት

ቅዱሳን፣ ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው ጸጋ ሙታንን ማስነሣት፣ ዕውራንን ማብራት፣ በአጠቃላይ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ማድረግ የዘወትር (የዂልጊዜ) ተግባራቸው ነው፡፡ የጸጋና የክብር ባለቤቶች ኾነዋልና በዓለም ላይ ሳሉ የሚመጣባቸውን ፈተና ዂሉ ተቋቁመው የጸጋ መቅረዞች ይኾናሉ፡፡ በዚህ ጸጋቸውም የአናብስቱን አፍ ዘጉ (ዳን. ፯፥፩-፰)፡፡ ውኃውን ወደ ኋላው መለሱ (ዘፀ. ፲፬፥፳፪)፡፡ ዝናም እንዳይሰጥ ሰማይን ለጎሙ (፩ኛ ነገ. ፲፯፥፩፤ ያዕ. ፭፥፲፯)፡፡ ነበልባለ እሳትን አበረዱ (ዳን. ፫፥፩-፲፫)፡፡ የቅዱሳን ወዳጅ እግዚአብሔር አምላካችን ሥጋዊ ሀገረ ተድላን ጥለው፣ ኃላፊ ጠፊ ምድራዊ ምቾታቸውን ንቀው ጸጋውን ከሚጠባበቁት ጋር ዂሉ አብሮ ይኖራል፡፡ ትዕግሥትን የጠዋት ቍርስ፣ የቀን ምሳ፣ የማታ እራት አድርገው የሚመገቧትን ዂሉ ማደሪያ ቤተ መቅደሱ ያደርጋቸዋል፡፡

የጋብቻ ሕይወት እና የሩካቤ ሥርዓት – የመጨረሻ ክፍል

የጽድቅ ሥራ እና የኀጢአት ተግባር በአንድ ልብ አመንጪነት ይፈጸማሉ፡፡ ልዩነቱ ጻድቃን ልቡናቸውን መልካም ነገርን ሲያሳስቡት፤  ኃጥኣን ደግሞ ለክፉ ነገር ማዋላችን ነው፡፡ “ደግ ሰው ከመልካም ልቡ መዝገብ መልካም ነገርን ያወጣል፤ ክፉ ሰው ግን ከክፉ ልቡ መዝብ ክፉ ነገርን ያወጣል፤” እንዲል (ማቴ. ፲፪፥፴፭)፡፡ በዚህ ዓለም እግዚአብሔርን የሚያስረሱን ሥጋውያን ተግባራት ብዙ ቢኾኑም፣ በአንጻሩ ደግሞ ፈቃደ ሥጋችንን በማሸነፍ ሕግጋቱን ጠብቀን ለመኖር የምንችልባቸው አጋጣሚዎችም አሉ፡፡ ጣዖት በሚመለክበት አካባቢ ቤተ ክርስቲያን እናገኛለን፤ ዓለማዊ ጫጫታ በሚበዛበት ቦታ ቅዳሴ እንሰማለን፡፡ እንግዲህ ለሥጋችን ነጻነት፣ ለነፍሳችን ድኅነት የሚጠቅመንን መምረጥ የእኛ ድርሻ ነው፡፡ ስለኾነም “እሺ ብትሉ፣ ለእኔም ብትታዘዙ የምድርን በረከት ትበላላችሁ” እንደ ተባልነው (ኢሳ. ፩፥፲፱) እንደ ዝሙት ያሉ አስነዋሪ ተግባራትን ከሚያስፈጽመን ሰይጣን ሸሽተን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ ልንከተል ይገባናል፡፡

በአጠቃላይ መላው ምእመናን በተለይ እሳታዊ ባሕርይ የሚበረታብን ወጣቶች በምድር በልዩ ልዩ ደዌያት እንዳንያዝ፣ በሰማይም በገሃነመ እሳት እንዳንጣል ከዝሙት ሥራ ዂሉ ራሳችንን በመጠበቅ በተቀደሰው ጋብቻ ልንወሰን ያስፈልገናል፡፡ ከዝሙት ኀጢአት ነጻ ለመኾንም ፈሪሃ እግዚአብሔርን ገንዘብ ማድረግ፤ ሥጋን በጸሎት፣ በጾምና በስግደት እንደዚሁም በሥራ ማድከም፤ በስሜት አለመነዳት፤ ራስን ከስሜታዊነት መጠበቅ፤ ከዚህም ባሻገር ሞተ ወልደ እግዚአብሔርንና የቅዱሳንን ተጋድሎ ማስታወስ ዋነኛ መፍትሔዎች ናቸው፡፡