የአዳዲስ ፈጠራ ግኝቶች ማበረታቻ የሽልማት ፕሮጀክት ትግበራ ተጀመረ።
በተ/ሥላሴ ጸጋ ኪሮስ
የሙያ አገልግሎትና አቅም ማጎልበቻ ዋና ክፍል የአዳዲስ ፈጠራ ግኝቶች ማበረታቻ የሽልማት ፕሮጀክት ትግበራ ጀመረ። በፕሮጀክቱ ትውውቅ መርሐ ግብር ላይ ለትግበራ መነሻ ይሆናል የተባለው «መጽሐፈ ብልሃትም» ተገምግሟል። ፕሮጀክቱ ማኅበረ ቅዱሳንና ኢንጅነር ሙሉጌታ ዘርፉ በተፈራረሙት የመግባቢያ ሠነድ መሠረት ፈጠራንና መልካም የሆነውን የቴክኖሎጂ ሽግግር ማበረታት፥ ቤተ ክርስቲያንን፣ ትውልድን ፣ ሀገርን የሚጠቅም አቅም ለማሳደግ አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሆነ በመርሐ ግብሩ ትውውቅ ወቅት የተበተነው ወረቀት ያስረዳል፡፡
