የዘወረደ ምንባብ 1 (ዕብ.13÷7-17)
የእግዚአብሔርን ቃል የነገሩአችሁን መምህሮቻችሁን ዐስቡ፤ መልካም ጠባያቸውን አይታችሁ በእምነት ምሰሉአቸው፡፡
This author has not written his bio yet.
But we are proud to say that Mahibere Kidusan contributed 1445 entries already.
የእግዚአብሔርን ቃል የነገሩአችሁን መምህሮቻችሁን ዐስቡ፤ መልካም ጠባያቸውን አይታችሁ በእምነት ምሰሉአቸው፡፡
የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ) ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ ባኡ ቅድሜሁ በተጋንዮ ወውስተ አ|ዕፃዲሁ በስብሐት አምንዎ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ ወንትፋቀር በበይናቲነ እስመ ለዓለም ምሕረቱ አክብሩ ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ እስመ ሰንበትሰ በእንተ ሰብእ ተፈጥረት እስመ ለዓለም ምሕረቱ […]
በፈትለወርቅ ደስታ
የማኅበረ ቅዱሳን ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል ባዘጋጀው ስልጠና ከተለያዩት ቦታዎች የመጡ 27 ሰልጣኞች ለሁለት ሳምንት የቆየ መሠረታዊ የሃይማኖት ትምህርት ሲከታተሉ ቆይተው የካቲት 13 ቀን 2003 ዓ.ም. ተመረቁ፡፡
ዲ/ን ኅብረት የሺጥላ
‘ኪዳን’ የሚባለው ቃል “ቃል” ከሚለው ጋር እየተቀናጀ በብሉይ ኪዳን ለ280 ጊዜ ያህል ሲጠቀስ በአዲስ ኪዳን ደግሞ ከ33 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል፡፡ “ኪዳን” ቃሉ “ተካየደ” ተማማለ፣ ቃል ተገባባ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፡፡
በዲ/ን ዘላለም ቻላቸው
አንድ ሰው ለጉዞ ሲነሣ ወዴት እንደሚሄድ ማወቅ አለበት፡፡ በዐቢይ ጾምም እንዲሁ፡፡ ከሁሉም በላይ ዐቢይ ጾም መንፈሳዊ ጉዞ ነው፤ መድረሻውም ትንሣኤ ነው፡፡ ለእውነተኛው መገለጥ ለፋሲካ መሟላት የሚደረግ ዝግጅት ነው፡፡ ስለዚህ በጣም አስፈላጊ የሆነና ስለ ክርስትና እምነታችንና ሕይወታችን በጣም ወሳኝ የሆነ ነገር ስለሚገልጥልን ይህን በዐቢይ ጾም እና በትንሣኤ መካከል ያለውን ግንኙነት ለመረዳት በመሞከር መጀመር አለብን፡፡
የትንሣኤ በዓል ከበዓላት አንዱ ከመሆን እና የአንድ ያለፈ ክስተት መታሰቢያ ከመሆን በላይ ሊታሰብ ያስፈልገዋል፡፡ አንድ ጊዜም ብቻ እንኳን ቢሆን የትንሣኤን በዓል በሚገባው መልኩ አክብሮ በዚያም ከቀን ይልቅ በሚያበራው ሌሊት የተሳተፈና ያንን ልዩ ደስታ የቀመሰ ማንም ሰው ያውቀዋል፡፡ ያ ደስታ ግን ስለ ምንድን ነው? በትንሣኤ በዓል ዕለት እንደምናደርገው «ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሀጺባ በደመ ክርስቶስ»፤ «ትንሣኤከ ለእለ አመነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ»፣ «ዛሬ ሁሉም ነገር፣ ሰማይም፣ ምድርም፣ ከምድር በታች ያሉ ነገሮችም በብርሃን ተሞሉ» እያልን መዘመር የምንችለው ለምንድነው? «የሞት መሞት፤ የሲኦል መበዝበዝ፣ የአዲስና የዘለዓለማዊ ሕይወት መጀመሪያ…» እያልን ማክበር የምንችለው እንዴት ነው?
በእመቤት ፈለገ
እንደምን ሰነበታችሁ ልጆች ? ዛሬ የምንነግራችሁ በጣም ደስ ስለሚለው ነጭ የበግ ግልገል ነው፡፡
በአንድ ወቅት አብረው ይኖሩ የነበሩ መቶ በጎች ነበሩ፡፡ ከነዚህ በጎች መካከል ሻሼ የተባለ በጣም ደስ የሚል እና ከጓደኞቹ በጎች ጋር መጫወት የሚወድ ነበር፡፡ በጣም የሚወዳቸው እናት እና አባት ነበሩት፡፡ ሌሎቹም እንደራሱ ወንድም እና እህት ነበር የሚያያቸው፡፡
እነዚህ መቶ በጎችን እጅግ በጣም የሚወዳቸው፤ ሌሎች እንስሳት ጉዳት እንዳያደርሱባቸው የሚጠብቃቸው እና ጥሩ ምግብ እና መጠጥ ሊያገኙበት ወደሚችሉት ቦታ የሚወስዳቸው ጎበዝ እረኛ ነበር፡፡ በእየለቱም ከመካከላቸው የጎደለ በግ እንዳይኖር 1፣2፣3፣ …. 1ዐዐ እያለ ይቆጥራቸው ነበር፡፡