ምዕዳነ አበው
/ምንጭ፦ ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ከግንቦት1-15፣ 2003 ዓ.ም/
ስምዐ ጽድቅ፡- የግንቦቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የርክበ ካህናት ጉባኤ ስለተወያየባቸው አጀንዳዎች ቢገልጹልን?
This author has not written his bio yet.
But we are proud to say that Mahibere Kidusan contributed 1445 entries already.
ስምዐ ጽድቅ፡- የግንቦቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የርክበ ካህናት ጉባኤ ስለተወያየባቸው አጀንዳዎች ቢገልጹልን?
በተ/ሥላሴ ፀጋ ኪሮስ
ሰኔ 15 ቀን 2003 ዓ.ም
ከ6 ወራት በፊት ተዘጋጅቶ እንደነበረው በርካታ ምእመናን የሚሳተፉበት መንፈሳዊ ጉዞ ተዘጋጀ፡፡ ሐዊረ ሕይወት ቁጥር 2 የሚል ስያሜ ያለው ይህ ጉዞ ሰኔ 19 ቀን 2003 ዓ.ም ይከናወናል፡፡
ሰኔ11 ፣2003 ዓ.ም
ዘኪዮስ የሚባል አጭር ሀብታም ሰው ነበረ፡፡ ኢየሱሱ ክርስቶስን ለማየት በጣም ይፈልግ ነበር፡፡ ምክንያቱም ስለ እርሱ ብዙ ነገር ሲነገር ይሰማ ስለነበረ ነው፡፡ ጌታችን በዛሬው ዕለት ኢያሪኮ ወደምትባለው ከተማ ይገባል ብለው ሰዎች ሲያወሩ ዘኪዮስ ሰማ፡፡
በእንዳለ ደጀኔ
ሰኔ 10 ቀን 2003 ዓ.ም
ሰኔ 11 ቀን 2003 ዓ.ም
/ምንጭ፦ ስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ግንቦት፣ 2003 ዓ.ም/
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን “መታደስ አለባት” የሚሉ ድምፆችን የሚያሰሙ አካላት አሳባቸውን በተለያዩ መንገዶች ማሰማት ከጀመሩ ውለው አድረዋል፡፡ እነዚህ አካላት በመጽሔቶች፣ በጋዜጦች፣ በመጻሕፍት፣ በበራሪ ወረቀቶች፣ በዓውደ ምሕረት ስብከቶችና በሚያገኟቸው አጋጣሚዎች ሁሉ ይኸን ጩኸታቸውን ማስተጋባቱን ተያይዘውታል፡፡ እንዲህ እያሉ ያሉትም “ኦርቶዶክሳውያን ነን” እያሉ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ በተለያየ ቦታና ሓላፊነት ላይ ካሉና እንጀራዋን ከሚበሉ፣ ጥቂቶች እንዲሁም ደግሞ በኅቡእና በግልጽ በተለያየ መልክና ቅርጽ ራሳቸውን አደራጅተው ቤተ ክርስቲያኗ ሳትወክላቸው እርሷን ወክለው፣ “እኛም ኦርቶዶክስ ነን” በሚል ካባ ራሳቸውን ደብቀው እምነቷንና ሥርዓቷን “ይህ ሳይሆን ሌላ ነበር” እያሉ ፕሮቴስታንታዊ ትምህርትና መንፈስ የተዋረሳቸው ሰዎች ናቸው፡፡
ከባህር ዳር ማእከል
ሰኔ 9 ቀን 2003 ዓ.ም
በባህር ዳር ከተማ በሚገኘው ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳምን ከ40 ዓመት በላይ በአስተዳዳሪነት ያገለገሉት መልአከ ገነት ኃይለ ማርያም ፋንታሁን በጠና ከታመሙ በኋላ በተወለዱ በ80 ዓመታቸው ግንቦት 30 ቀን 2003 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት አርፈዋል።
ሥርዓተ ቀብራቸው ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልያስና ብፁዕ አቡነ ቶማስ፣ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ እንዲሁም ወዳጅ ዘመድና ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት በፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም በዕለተ ሐሙስ ሰኔ 2 ቀን 2003 ዓ.ም ከቀኑ 5፡30 ተፈጽሟል፡፡
ሰኔ 07 ፣2003 ዓ.ም
በአዜብ ገብሩ
እንደምን ሰነበታችሁ ልጆች? ደህና ናችሁ? እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ በሰላም አደረሳችሁ፡፡
ከትንሣኤ በኋላ ያለው ሃምሳኛው ቀን ጰራቅሊጦስ ይባላል፡፡ ይህ ዕለት ጌታ ለሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ያወረደበት ዕለት ነው፡፡ ልጆች ጌታ ከሞት ከተነሣ በኋላ አስራ ሁለቱ ሐዋርያት በቅዱስ ማርቆስ እናት ቤት ከሰባሁለቱ አርድዕት አና ከሰላሳ ስድስቱ ቅዱሳን አንስት ጋር በመሆን ይጸልዩ ነበር፡፡ ጌታም በተለያየ ጊዜ እየተገለጸ ያስተምራቸው ነበር፡፡ አጽናኝ የሆነውን ቅዱስ መንፈስም እንደሚልክላቸው ይነግራቸው ነበር፡፡
በይበልጣል ሙላት
ሰኔ 6፣2003ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማዕከል የትምህርትና ኪነጥበባት ክፍል የተዘጋጀውና “አሻራ” የሚል ስያሜ የያዘው ተውኔት ይመረቃል፡፡
ተውኔቱ እሑድ ሰኔ 12 ቀን 2003 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 በማኅበረ ቅዱሳን ህንፃ እንደሚመረቅ የተገለጸ ሲሆን ከዚያ በኋላ ለምዕመናን ክፍት ይሆናል ተብሏል፡፡
በዚህም አያቆሙም “ቦርጆ በእኛ መካከል ሲኖር ነበር፣ በቆይታ አንዳንዶች በልባቸው ክፉ አስበው አስቀየሙት፣ ቦርጆን ገረፉት፣ መቱት፣ አቆሰሉት፡፡ እርሱም ከእንግዲህ ‘ከእናንተ ጋር ሆኜ /እየኖርኩ/ የማበላችሁ የማጠጣችሁ አይምሰላችሁ፡፡ ወደ ሰማይ እሄዳለሁ በልባችሁ ግን ለምኑኝ አበላችኋለሁ፣ አጠጣችኋለሁ’ ብሎን ሄዷል፡፡” በማለት ስለ አምላካቸው ያብራራሉ፡፡