ክርስቲያናዊ አንድነት
ክርስቲያናዊ አንድነት በእምነት አንድነትና በአስተምህሮ ስምምነት የሚገለጥ ነው፡፡ በዚህም በክርስቶስ ክርስቲያን የተባልን ሰዎች የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት በማመን፣ ከሀብተ መንፈስ ቅዱስ በመወለድ፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን በመቀበል በአጠቃላይ ለሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን በመገዛት መኖር ማለት እንደሆነ እንረዳለን፡፡
This author has not written his bio yet.
But we are proud to say that Mahibere Kidusan contributed 1094 entries already.
ክርስቲያናዊ አንድነት በእምነት አንድነትና በአስተምህሮ ስምምነት የሚገለጥ ነው፡፡ በዚህም በክርስቶስ ክርስቲያን የተባልን ሰዎች የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት በማመን፣ ከሀብተ መንፈስ ቅዱስ በመወለድ፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን በመቀበል በአጠቃላይ ለሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን በመገዛት መኖር ማለት እንደሆነ እንረዳለን፡፡
ነቢዩ ሙሴ ዐርባ ቀንና ዐርባ ሌሊት ጸልዮና ጹሞ ዐሥርቱ ቃላት የተጻፈበትን ጽላት ከእግዚአብሔር ከተሰጠው በኋላ የቃል ኪዳኑን ታቦት ‹ታቦተ ጽዮንን› እንደሠራት መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል፡፡ ታቦተ ጽዮን ከማይነቅዝ እንጨት የተሠራችበት ምክንያት የእመቤታችን ድንግል ማርያምን ንጽሕና ለማመልከት ነው፡፡ በውስጥም በውጪም በጥሩ ወርቅ የተለበጠች መሆኗ ደግሞ የእመቤታችን ድንግል ማርያም ቅድስናዋንና በሁለት ወገን ድንግል የመሆኗ ምሳሌ ነው፡፡
ተስፋ ሲኖረን የነገን ለማየት እንናፍቃለን፤ ዛሬ ላይም በርትተን ለመጪው እንተጋለን፤ የመልካም ፍጻሜችንም መድረሻ በተስፋችን ይሰነቃልና፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ ‹‹የሁሉ ዓይን አንተን ተስፋ ያደርጋል፤ አንተም ምግባቸውን በየጊዜው ትሰጣቸዋለህ። ቀኝ እጅህን ትዘረጋለህ፤ በሥርዓትህ ለሚኖሩ እንስሳ ሁሉ ታጠግባለህ፡፡ እግዚአብሔር በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ ነው፤ በሥራውም ሁሉ ቸር ነው። እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ፥ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው። ለሚፈሩት ምኞታቸውን ያደርጋል፥ ልመናቸውንም ይሰማል፥ ያድናቸዋልም። እግዚአብሔር የሚወድዱትን ሁሉ ይጠብቃል፤ ኃጢአተኞችንም ሁሉ ያጠፋል›› በማለት ገልጿል፡፡ (መዝ. ፻፵፬፥፲፭-፳)
በዘመነ ብሉይ ነቢያት እግዚአብሔር ወልድ ከንጽሕተ ንጹሐን፤ ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ለአዳም የገባለትን ቃል ይፈጽም ዘንድ ትንቢት በመናገር ለሕዝቡ የምሥራችን ቃል ያበሥሩ ነበር፡፡… ነቢያቱ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው ሆኖ ዓለምን የሚያድንበትን ዘመነ ሥጋዌ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡ የነቢያት ትንቢትና ጸሎትም በእግዚአብሔር ሰው መሆን ተፈጽሟል፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ይህንን ታሳቢ በማድረግ በዘመነ ማቴዎስ፣ ማርቆስና ሉቃስ፤ ከኅዳር ፲፭ አስከ ታኅሣሥ ፳፱፤ በዘመነ ዮሐንስ ደግሞ እስከ ታኅሣሥ ፳፰ ጾም ታውጃለች፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ኢሬኔጅ የሰርቢያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉ ተገለጸ።
ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ‹ሚካኤል ሥዩም በዲበ ኃይላት፤ በኃይላት ላይ የተሾምክ ሚካኤል› ሲል ያመሰገነው ቅዱስ ሚካኤል በኃይላት መላእክት ላይ የተሾመ ሊቀ መላእክት እንደመሆኑ በዓለ ሢመቱ ኅዳር ፲፪ ቀን በመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ይከበራል፡፡
ሰዎች በሕይወታችን ውስጥ እጅጉን ከሚያስፈልገን ነገር ዋነኛው ሰላም ነው፡፡ ያለ ሰላም መኖር አይቻልንም፡፡ ሰላም የተረበሹትን ያረጋጋል፤ ያዘኑትን ያጽናናል፤ ጦርነትን ወደ ዕርቅ ይለውጣል፡፡
ከሦስት የስደት እና መከራ ዓመታት በኋላ የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ አረጋዊ ዮሴፍንና ሰሎሜን አስከትላ ወደ ግብፅ ስትሰደድ በስተደቡብ የምትገኘው ደብረ ቊስቋም ላይ ያረፉበችበት ኅዳር ፮ ቀን ይከበራል፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋ ከአምስተኛ ባሕርያተ ነፍስ ፈጥሮ በመንፈስ ቅዱስ አክብሮ ሲያኖረው ለሥጋውም ለነፍሱም ምግብ እንዲያስፈልገው አድርጎ ነው፡፡ ለሥጋውም የሚያስፈልገውም ምግብ ልዩ እንደሆነ ሁሉ የሥጋውንና የነፍሱን ባሕርያት የተለያየ ነው፤ ነፍስም እንደ ሥጋ ባሕርያት (ነፋስ፣ እሳት፣ ውኃና መሬት) ባሕርይዋም ሆነ ምግቧም እንደዚያው ይለያል፡፡ የነፍስ ተፈጥሮዋ ረቂቅ ነው፤ በዚህም ለባዊነት፣ ነባቢነትና ሕያውነትም ባሕርይዋ መሆናቸውን ማወቅና መረዳትም ያስፈልጋል፤ ምግቧም የሕይወት ኅብስት ነው፡፡
