Entries by Mahibere Kidusan

የኤማኁስ መንገደኞች

በዓለም ላይ ብዙ መንገዶች አሉ፤ ሰዎችም በመንገድ ይጓዛሉ፤ ሆኖም ለተለያየ ዓላማ ነው፤ ግን ያች የኤማኁስ መንገድ ምን ያህል ዕድለኛ ናት? ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት የሚወራባት፣ ክርስቶስ በእግሩ እየባረከ የነቢያትን ትምህርት የሚተረጉምባት መንገድ፣ የጠወለገ የደከመ የሚበረታባት መንገድ!

በፍቅር ተቀበለኝ!

ኃጢአቴን ደምስሶ ወገኑ ሊያደርገኝ

ኢየሱስ ክርስቶስ በፍቅር ተቀበለኝ

ይህን የዓለም መድኅን የበጐች እረኛ

የድንግል ማርያም ልጅ የእውነት መገኛ

ከአብ የተላከ ለአዳም ዘር ሁሉ እንዲሆን መዳኛ

ተንሥኡ!

በከበረና ድንቅ ሥራው ሰውን ሕያው አድርጎ ሲፈጥረው እግዚአብሔር አምላክ እስትንፋስና ሕይወትን ሰጥቶ ካለመኖር ወደ መኖር ባመጣው ጊዜ የሕይወቱን ዘመናት አሐዱ ብሎ እንደጀመረ መጽሐፈ ኦሪት ያወሳናል፡፡ ወደ አፈር እስኪመለስ ድረስም ሞትን አልቀመሳትም ነበር፡፡ ጊዜው ሆነና ግን ሞተ፤ ተቀበረ፤ አፈርም ሆነ፤ በምድር ላይም ታሪኩ እንጂ ሥጋው አልቀረለትም፤ እናስ መቼ ይሆን የቀደመ ክብሩና ጸጋውን አግኝቶ፣ ሥጋውም ከነፍሱ ጋር ተዋሕዳ በሰማያዊት ቤቱ የሚኖረው?

ነገረ ትንሣኤ

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት ሰነበታችሁ? እንኳን አደረሳችሁ! የትንሣኤ በዓል እንዴት እያከበራችሁ ነው? መልካም! ልጆች! ዛሬ ስለ ጌታችንን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ እንማራለን፡፡ ከዚያ በፊት ግን ከትንሣኤ በዓል ጀምሮ እስከ በዓለ ሃምሣ ድረስ ስንገናኝ የምንለዋወጠውን ሰላምታ እናስቀድም!

ዘመነ ትንሣኤ

የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ከሚከበርበት ዕለተ እሑድ አንሥቶ እስከ የሚቀጥለው እሑድ ያሉት ቀናት ለእያንዳንዳቸው ዕለታት ስያሜ ተሰጥቷቸው ፍቅሩን እያሰብን ውለታውን እያስታወስን እናዘክራቸዋለን፡፡

ብርሃነ ትንሣኤ

ዓለም በጨለማ ተውጣና የሰው ዘር በሙሉ በኃጢአት ቁራኝነት ተይዞ የዲያብሎስ ባሪያ በነበረበት ዘመን ብርሃናተ ዓለም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሞቱ ሞትን አጥፍቶ ብርሃንን ለገለጠበት ለትንሣኤው አድርሶናል ክብር ምስጋና ይገባዋል!!!

“በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ፤ ሕማማችንን ተሸከመ፤ ስለመተላለፋችን ቆሰለ፤ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን” (ኢሳ.፶፫፥፬‐፮)

ሰባት የጾምና የጸሎት ሳምንታትን አሳልፈን፣ “ሆሣዕና በአርያም” ብለን አምላካችን በመቀበል፣ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማሙን፣ መገረፍ መገፈፉን፣ መሰቀልና መሞቱን እንዲሁም የድኅነታችንን ዕለት ትንሣኤን በተስፋ ለምንጠብቅበት ለሰሙነ ሕማማት ደርሰናልና አምላካችን እንኳን ለዚህ አበቃን!

ሆሣዕና በአርያም

የሰላም ንጉሥ መድኃኔዓለም

ስለ ስምህ ተቀኝተናል ሆሣዕና በአርያም!

በዓለ ሆሣዕና

ጌታችን ከተወለደ ፴፫ የምሕረት ዘመናት ተቆጠሩ። ዕለቱ እሑድ፣ ቀኑ መጋቢት ፳፪ ነበር። በምድር የሚመላለስበትን ዘመን ሊጨርስ ጥቂት ቀናት ሲቀሩት ወደ ኢየሩሳሌም ለመግባት ለደብረ ዘይት ትራራ ቅርብ ወደ ሆነችው ቤተ ፋጌና ቢታንያ መንደር ገሰገሰ፡፡ ከደቀ መዛሙርቱም ጴጥሮስና ዮሐንስን እንዲህ አላቸው፤ ‘‘በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፤ ወደ መንደርም በገባችሁ ጊዜ ሰው በላዩ ያልተቀመጠበት የአህያ ውርንጫ ታስሮ ታገኛላችሁ፤ ፍቱና አምጡልኝ፤ ምን ታደርጋላችሁ የሚላችሁ ሰው ቢኖርም ጌታው ይሻዋል በሉ’’ አላቸው፤ (ማር.፲፩፥፪) ሁለቱ ደቀ መዛሙርትም እንደታዘዙት አደርጉ፡፡

የታሰሩትን ሊፈታ መጥቱዋልና የታሰርውን ፍቱልኝ አለ፤ ሰውን ሁሉ ከማዕሰረ ኃጢአት የሚፈታበት ጊዜ እንደደረሰ ሲያጠይቅ ነው። በአህያ ላይ ሁኖ ሲገባም የሚበዙት ሕዝብ ለጌታችን ክብር ለአህያዋ ልብሳቸውን ጎዘጎዙ፤ ልብስ ገላን ይሸፍናልና ከባቴ አበሳ ነህ ሲሉ። በፊት በኋላ ሁነው ‘‘ለወልደ ዳዊት መድኃኒት መባል ይገባዋል’’ እያሉ አመሰገኑ፤ ሆሣዕና ማለት መድኃኒት ማለት ነውና “ሆሣዕና በአርያም” ሲሉ ቀኑን ዋሉ፡፡ በፊቱ ያሉት የሐዋርያት በኋላው ያሉት የነቢያት ምሳሌዎች ናቸው፡፡ በሌላም ትርጉም የብሉያትና የሐዲሳት ምሳሌዎች ሁነዋል። በዚህም የፊተኛውም የኋኛውም ዘመን ጌታ መሆኑ ተገልጧል፡፡

በዓለ ፅንሰቱ ለእግዚእነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ

የዓለም ቤዛ፣ የዓለም መድኃኒት፣ የሰው ልጆች አዳኝ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን ተዋሕዶ ወደ ምድር ይመጣ ዘንድ የድኅነት ግብሩ የተፈጸመበት የምሥራች ቃል የተነገረበት እንዲሁም ከንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም የተፀነሰበት ዕለት መጋቢት ፳፱ ታላቅ በዓል ነው፡፡ የነገረ ድኅነቱ የመፈጸሚያ ጅማሮ ይህ ዕለት የተቀደሰ በመሆኑም ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ትዘክረዋለች፤ ታከብረዋለችም፡፡