በዘንድሮው ዓመት ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ካዘጋጃቸው 18 ሜዳሊያ ዋንጫውን ጨምሮ 14ቱ በግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች የተወሰዱ መሆናቸው ተገለጸ
በማኅበረ ቅዱሳን የባሕር ዳር ማእከል በ7 የተለያዩ ግቢ ጉባኤያት ያስተማራቸውን 1,073 የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎችን ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ.ም የአድባራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የተመራቂ ቤተሰቦች በተገኙበት በፔዳ ግቢ ጉባኤ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ አስመርቋል።
አቶ ብርሃኑ አሳሳ በማኅበረ ቅዱሳን የባሕር ዳር ማእከል ምክትል ሰብሳቢ በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው የማእከሉን የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ለተመራቂዎች እና ለተመራቂ ቤተሰቦቻቸው ያስተላለፉ ሲሆን በመልእክታቸው
“በዚህ ዘመን በዘረኝነት፣ በሥርዓት አልበኝነትና በልዩ ልዩ ፈተናዎች ሀገር እየተፈተነች ቢሆንም በግቢ ጉባኤ ሕይወት ማለፋችሁ እንድትተርፉ አድርጓችኋል” ብለዋል።
በዕለቱ በመልአከ ምሕረት ግሩም አለነ የሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት ሐዋርያዊ አገልግሎት እና ስብከተ ወንጌል መምሪያ ኀላፊ ትምህርተ ወንጌል የሰጡ ሲሆን
ዛሬ ቤተ ክርስቲያን ተሠርታ የተመረቀችበት ቀን በመሆኑ በዚህ ዕለት በመመረቃችሁ ደስታችሁን እጥፍ ድርብ ያደርገዋል“ በማለት የዛሬ ተመራቂዎች በቀጣይ ሕይወታቸው ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል የበረቱ እንዲሆኑ እና ሁሌም ለማወቅና ለመማር መትጋት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
በመርሐ ግብሩ ተሞክሯቸውን ያቀረቡ የከፍተኛ ማእረግ ተመራቂ ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት የማምጣታቸው ምሥጢር በግቢ ጉባኤ ውስጥ መሳተፋቸውና ጊዜያቸውን በአግባቡ መጠቀም በመቻላቸው መሆኑን ገልጸዋል።
በዘንድሮው ዓመት ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ካዘጋጃቸው 18 ሜዳሊያ ዋንጫውን ጨምሮ 14ቱ በግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች የተወሰዱ መሆኑን በማኅበረ ቅዱሳን የባሕር ዳር ማእከል የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ዋና ክፍል ኀላፊ ቀሲስ ምሕረት እንዳለው ገልጸዋል።
መረጃው በማኅበረ ቅዱሳን የባሕር ዳር ማአሰከል ሚዲያ አገልግሎት ክፍል ነው።
👇👇👇👇👇👇👇
የማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች ይቀላቀሉ
ቴሌግራም፡- http://t.me/mkpublicrelation
የማኅበረ ቅዱሳን ሕዝብ ግንኙነት:-https://www.facebook.com/mahiberekidusan.mkusa/
ድረገጽ፡- http://www.eotcmk.org
ዩ ቲዩብ፡- http://www.youtube.com/user/EOTCMK
:- https://www.youtube.com/@-zemawetibebzmk7905
