የወላይታ ሶዶ ማእከል ለ8 ወራት ያስተማራቸውን 45 የበገና ዘማርያንን አስመረቀ።
በማኅበረ ቅዱሳን ወላይታ ሶዶ ማእከል በልማት ተቋም ሥር ለ8 ወራት ሲያስተምራቸው የቆዩ 45 የበገና ዘማርያንን በወላይታ ሶዶ በኦቶና ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም አስመረቋል።
በመርሐ ግብሩ የወላይታ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሰላም ቀሲስ ቦክቻ ኤንጋ፣ የኦቶና ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ አርያም ዮሐንስ አያሌው የተገኙ ሲሆን የበገና ዝማሬ እና የማኅበረ ቅዱሳንን መልእክት ቀርቧል።
በማኅበረ ቅዱሳን የወላይታ ሶዶ ማእከል ጸሐፊ ዲ/ን እርዳቸው ዮሴፍ በመልእክታቸው ማኅበረ ቅዱሳን በመዝሙርና በዜማ መሣሪያዎች ትኩረት አድርጎ በመሥራት ላለፉት አሥርት ዓመታት የበገናና የመሰንቆ ዘማርያንን አሠልጥኖ ማስመረቁን ጠቅሰው ወላይታ ሶዶ ማእከልም የበኩልን ድርሻ በመወጣት በዕለቱ የተመረቁትን 45 የበገና ዘማርያን ጨምሮ ከ1500 በላይ የበገናና የመሰንቆ ዘማርያንን አስተምሮ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን አበርክቷል ብለዋል።
ጸሐፊው አክለውም የሠለጠኑትን የበገና ዜማ መሣሪያ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ብቻ እንዲያውሉ አጽንኦት በመሥጠት ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
በማኀበረ ቅዱሳን የወላይታ ማከእል ትምህርትና ዜማ አገልግሎት ክፍል ተወካይ ዲ/ን ወደፊት አላቸው ባስተላለፉት መልእክት ላለፉት ስምንት ወራት የበገና ተማሪዎችን ለማስተማር ብቃት ያላቸው መምህራንን መድበው መቆየታቸውን ገልጸው የዜማ ትምህርት ቤቱ ቅርንጫፎቹን አሳድጎ ለብዙዎች ተደራሽ እንደሆነ ገልጸዋል።
የትምህርት እና ዜማ አገልግሎት ክፍል ተጠሪው አክለውም በገና ተምረው የሚመረቁ በርካታ ቢሆኑም ነገር ግን በአገልግሎት ለመጽናት ግን መንፈሳዊነትና ትጋት ይጠይቃል በማለት ሲያስተምሩ የነበሩ መምህራንን እና የአገልግሎት ዘርፍ አስተባባሪዎችን አመስግነዋል።
በመጨረሻም የዜማ እና ኪነ ጥበብ ተመራቂዎቹን በማእከሉ መዝሙር ክፈሉ ውስጥ አባል ሆነው ጠንክረው በአገልግሎት እንዲቀጥሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ዘገባው የማኅበረ ቅዱሳን ወላይታ ሶዶ ማእከል ነው።👇👇👇👇👇👇👇
የማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች ይቀላቀሉ
ቴሌግራም፡- http://t.me/mkpublicrelation
የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት፡- http://www.facebook.com/eotcmkidusan/
ድረገጽ፡- http://www.eotcmk.org
ዩ ቲዩብ፡- http://www.youtube.com/user/EOTCMK
:- https://www.youtube.com/@-zemawetibebzmk7905
