[smartslider3 slider=”1″]

ማኅበረ ቅዱሳን



የማኅበሩ ርእይ

“ቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ የመሪነት ሚናዋን ስትወጣ ማየት”




የማኅበሩ ተልእኮ

“ለቤተ ክርስቲያን ተልእኮ መሳካት እና ለሕልውናዋ የሚተጋ፣ የተደራጀ ፣ ምሉዕ ኦርቶዶክሳዊ፤ ርቱዕ ዘመናዊ፤ ሁለገብ መሪ ትውልድ ማፍራት እና ማሰማራት”




እሴቶች




መንፈሳዊነት

ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::




አገልጋይነት

የማኅበሩ አባላት አገልግሎትን የክርስቲያናዊ ሕይወታቸው መገለጫ አድርገው በመቀበል በበጎ ፈቃድ ሰማያዊውን ክብርና ጸጋ በመሻት፣ ምድራዊ ክብርና ውዳሴ ከንቱን ሳይፈልጉ፣ በትሕትና እና በክርስቲያናዊ ፍቅር በታማኝነት ያገለግላሉ::




የሐሳብ መሪነት

ማኅበሩ ለቤተ ክርስቲያን ዘላቂ አገልግሎት የሚያስፈልጉ፣ ኦርቶዶክሳዊ እሳቤን የተከተሉና ዘመኑን የዋጁ የመሪነት ሐሳቦችን በማፍለቅ ከሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ጋር በመመካከር ይሠራል::




ተባባሪነት

ማኅበሩ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሁሉም የቤተ ክርስትያን አካላት የወል ተግባር ነው ብሎ ያምናል:: በመሆኑም እንደየጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ባለ ድርሻ እና አጋር አካላት ጋር በመግባባት፣ በመመካከር እና በቅንነት ለተልእኮ አንድነት ብዝኃ ጸጋን በማክበር አብሮ ይሠራል::




ሙያ አክባሪነት

የማኅበሩ አባላት ባላቸው ልዩ ልዩ ሙያ /ዕውቀት/ ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል የተሰባሰቡ በመሆናቸው፣ በማኅበሩ አሠራሮች ሁሉ ከኦርቶዶክሳዊው ትምህርተ ሃይማኖት ጋር በማይጋጩ በእውነተኛ መረጃ ለሚደገፉ ሙያዊ ምክረ ሐሳቦች ተገቢውን ክብርና ቅድሚያ ይሰጣል:: በቤተ ክርስቲያንም ለመንፈሳዊ እና ለዘመናዊው (አስኳላ) ሙያ ተገቢው ክብር እንዲሰጥ ይሠራል::




ምክንያታዊ ሞጋችነት

ማኅበሩ በእውነተኛ መረጃ ላይ ተመሥርቶ ቤተ ክርስቲያንን ከውስጥም ሆነ ከውጭ የሚፈትኑ አስተሳሰቦችን፣ አሠራሮችን፣ ልማዶችን እና ትርክቶችን በግልጽና በመንፈሳዊ ጥብዓት እና በእውነት እንዲሞገቱና መፍትሔ ላይ እንዲደረስ ይሠራል::




ተጠያቂነት

የማኅበሩ አገልግሎት ግብ ሰማያዊ ዋጋ ማግኘት ስለሆነ ኀላፊነትን በአግባቡ አለመወጣት በእግዚአብሔር እና በሰዎች ዘንድ የሚያስጠይቅ በመሆኑ በየትኛውም እርከን ላይ ያለ አባል እና አመራር በማኅበሩ አሠራር መሠረት በተሰጠው ኀላፊነት ተጠያቂ ይሆናል፡፡




ዓላማዎች

የቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ አስተዳደር፣ የአሠራር ሥርዐትና አስተሳሰብ፣ በቴክኖሎጂ እና በልዩ ልዩ መንገዶች በመደገፍ ዘመኑን ለዋጀ ጠንካራ አገልግሎት ማብቃት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ሙሉ ሰብእናን የሚገነባ ሥርዐተ ትምህርት በማስተማር ዘመኑን የዋጁ ምሉዕ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር የሚያገለግሉ እንዲሁም በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ በፖለቲካዊ እና በሀገር አስተዳደር ጉዳዮች መሪ/ንቁ ተሳታፊ አገልጋዮችን ማፍራት እና ማሠማራት፤

የተተኪውን ትውልድ ምንጭ ለማጎልበት የሰ/ት/ቤቶችን አቅም በማጠናከር የሕጻናት እና የወጣቶችን የተተኪነት ሚና ማሳደግ፤

ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነትን በተግባር የሚገልጽ ቤተሰብ እና አንድነቱን የጠበቀ ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብ በመገንባት የተደራጀ እና የተናበበ አገልግሎት መስጠት፤

በተደራጀ እና ተደራሹን ማእከል ባደረገ መንገድ ስብከተ ወንጌልንና ሐዋርያዊ ተልእኮን ዘርፈ ብዙ በሆኑ መንገዶች በመላው ዓለም ማስፋፋት፤

በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚነዙትን የርእዮተ ዓለም፣ የሐሰት ትርክቶች እና የአጽራረ ቤተ ክርስቲያንን እንቅስቃሴ ጥናት እና ምርምር ላይ ተመርኩዞ መሞገት እና የተሳሳቱትን በማረም፣ በጠንካራ የዕቅበተ እምነት አገልግሎት የቤተ ክርስቲያንን ሕልውና ማስጠበቅ፤

በተመረጡ ገዳማት እና አብነት ትምህርት ቤቶች የልኅቀት ማእከል እና የተለየ ክርስቲያናዊ ተልእኮ የሚፈጽሙ እንዲሆኑ የሚያስችል ሁለገብ የአእምሮ ልማት ድጋፍ ማድረግ፤

ማኅበሩ ዘመኑን የዋጀ ተቋማዊ የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት ተልእኮውን ማሳካት የሚችልበት አቅም መፍጥር ( በአመራር፣ በሰው ኃይል፣ በመንፈሳዊነት፣ በግንኙነት፣ በዕውቀት፣በልማት፣ በፋይናንስ፣ በቴክኖሎጂ)፤

ዓለም አቀፍ ግንኙነትና የትብብር አገልግሎትን መርሕ ያደረገ የኦርቶዶክሳውያን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ማሳደግ፣
የሚሉ ዓላማዎች ያሉት ነው፡፡

ቅዱሳን አባቶች

አቡነ ባስልዮስ
አቡነ ቴዎፍሎስ
አቡነ ተክለ ሃይማኖት
አቡነ መርቆሬዎስ(1)
አቡነ ጳውሎስ

Previous
Next

ሥራህን ሥራ

ጌታ ለእያንዳንዱ ሰው ሥራ ሰጥቶታል ያንን መራት የእሱ ፈንታ ነው። ቢቻለው እሱን ማገድ የዲያብሎስ ሥራ ነዉ።በእርግጥ ሥራውን እግዚአብሔር እንደሰጠህ ያህል ሰይጣን ሊያግድህ ይሞክራል። ሌላ ነገር በበለጠ ደስ የሚያሰኝ ሊያቀርብልህ ይጥራል። በዓለማዊ ተስፋዎች ያባብልሃል የሐሜት ጎርፍ ያስወርድብሃል። ደራሲያን ኦንዲጠይቁህ እጅግ
ስመ ጥሩ ሰዎችም በክፋ እንዲናገሩብህ ይጠቀምባቸዋል። ጲላጦስ፥ሄሮድስ፥ሐናንያ፥ቀያፋ ሁሉም በአንተ ላይ ያድማሉ . . . አንተ ግን በጸና ውሳኔ በማያወላውል ቅናት በመጨረሻ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈፀምኩ ሃይማኖቴንም ጠበቅሁ ለማለት እስክትችል ድረስ የሕይወትህን ዓላማ እና የተፈጠርክበትንም ግብ ተከተል።

አባ ጎርጎርዮስ ካልዕ
የሸዋ ሊቀ ጳጳስ ፩፱፫፪፡፩፱፰፪ ዓ.ም.

አዳዲስ ዜናዎች እና ክንውኖች

ስብከት | ወቅታዊ ትምህርት


‹‹ሐሰትን አትነጋገሩ›› (ሌዋ.፲፱፥፲፩)

ከሁሉም አስቀድሞ ሰዎች ፈጣሪ እግዚአብሔር የእውነት አምላክ እንደሆነ ልንረዳ ይገባናል፡፡ እርሱ እውነተኛና የእውነት መንገድ እንደሆነ ስንናውቅ መንገዳችን በእውነትና ስለ እውነት ይሆናል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ›› በማለት እንደተናገረው በሕይወታችን ውስጥ እውነትን ማሰብ፣ እውነትን መናገር እንዲሁም በእውነተኛው መንገድ መጓዝ የሚቻለን አምላካችን እውነተኛ መሆኑንና ሐሰትን እንደሚጠላ ስናውቅ ነው፡፡…




ስብከት | ወቅታዊ ትምህርት


ነጻነት

ነጻነት ከሰው ልጅ አፈጣጠር ጋር የተያያዘ ግብር መሆኑን ማወቅ እጅጉን ተገቢ ነው። አምላካችን እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው በአርአያውና በአምሳሉ ሲፈጥረው ሙሉ ነጻነት ያለው ፍጥረት አድርጎ ነው፡፡ ይህም ይታወቅ ዘንድ በተሰጠው አእምሮ የወደደውን (ክፉውን ከሻተ ክፉውን፣ መልካሙን ከሻተ መልካሙን) እንዲመርጥ የመምረጥ መብት ተሰጥቶታል።





ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

መልእክት | መግለጫ | ዘገባዎች


ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ





በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከማኅበረ ቅዱሳን ጽሕፈት ቤት የተላለፈ መልእክት

መልእክት | ዘገባዎች | የማኅበሩ መልእክት


በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከማኅበረ ቅዱሳን ጽሕፈት ቤት የተላለፈ መልእክት





‹‹ተዝካረ ዕረፍቱ ለቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ››

ስብከት | በዓላት | ዝክረ ቅዱሳን


‹‹ተዝካረ ዕረፍቱ ለቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ››

ዐሥራ ሁለተኛው የቊስጥንጥንያ መንበር የነበረ፣ ከአራቱ የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያን ዐቃቢያነ እምነት ከሆኑት ከቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ፣ ከቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያና ከቅዱስ ባስልዮስ ጋር በግብር የተካከለ፣ በገዳማዊ ሕይወቱ ብሕትው፣ በንጽሕናው ተአማኒ፣ በአእምሮ ምጡቅ፣ በአንደበቱ ርቱዕ፣ በስብከቱ መገሥጽ፣ በፍርዱ ፈታሒ በጽድቅ፣ በመግቦቱ አበ ምንዱባን (የድኆች አባት) በጥብቅናው ድምፀ ግፉዓን፣ በጥቡዕነቱ መገሥጽ፣ በክህነቱ የቤተ ክርስቲያን…




ስብከት | በዓላት | ኪነ ጥበብ


ማይኪራህ

ከሌሊት ወፍ በመዓልቱ: …… እልፍ እንቁላል ሊሰበሰብ፣ የወንዱ ጽንስ እንዲገፋ …… ከበቅሎው ወተት ሊታለብ፤ ከማር ቀፎ የዝንብ መንጋ …… አውሬው ጓዳ ገብቶ እንዲያድር፣ የተፈጥሮ ሕጉን ስቶ …… ያለቦታው እንዲሰደር፤





ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ያሬድ

ምንባባት | ስብከት | በዓላት | ዝክረ ቅዱሳን


ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ያሬድ

ኢትዮጵያዊው ማኅሌታይ፣ የዜማ ደራሲና ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ድንቅ ተጋድሎን ፈጽሞ ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም የገባበት ዕለት ግንቦት ፲፩ የከበረች እንደመሆኗ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ታከብረዋለች፡፡




ስብከት | ወቅታዊ ትምህርት


‹‹ኑ ምሳ ብሉ›› (ዮሐ.፳፩፥፲፪)

ይህን ኃይለ ቃል የተናገረው ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ቃሉን  ደግሞ የሚበላ ፈልገው ዓሣ ለማጥመድ ሌሊቱን ሲደክሙ ለነበሩ ግን የሚፈልጉትን ሳያገኙ በረኀብ ዝለው በፍለጋ ደክመው ለነበሩ ለቅዱሳን ሐዋርያት ነው፡፡ ሞትን በሞቱ ገድሎ፣ በትንሣኤው ትንሣኤያችንን አብሥሮ፣ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሣ በኋላ ለቅዱሳን ሐዋርያት በጥብርያዶስ ባሕር ዳርቻ ተገለጠላቸው፤ ይህ ከትንሣኤው በኋላ…




ስብከት | ክርስቲያናዊ ሕይወትና ሥነ ምግባር


“ትዋደዱ ዘንድ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ” (ዮሐ.፲፫፥፴፬)

መውደድ በሰዎች መካከል የሚኖር ስሜት ነው፤ ያለ መዋደድም በዚህ ምድር ላይ መኖር አይቻለንም፤ መጠኑ ይብዛም ይነስ በሰው ልብ ውስጥ የመዋደድ ስሜት ይፈጠራል፡፡ ሰዎች ተቻችለንና ተሳስብን እንዲሁም ተዛዝነን የምንኖረው ስንዋደድ ነው፡፡ ግን ይህ ስሜት ከምንም ተነሥቶ በውስጣችን ሊፈጠር አይችልምና መውደድ መነሻው ምንድነው? የሚለውን ነገር ብንመረምር መልካም ነው፡፡





”በቤተ ክርስቲያን ያጋጠሙ ችግሮች በዚህ ጥበብ ካልሆነ በቀር በመሳሳብና እልክ በመጋባት የሚፈቱ አይደሉም”

መልእክት | መግለጫ | ርእሰ አንቀጽ | ዘገባዎች


”በቤተ ክርስቲያን ያጋጠሙ ችግሮች በዚህ ጥበብ ካልሆነ በቀር በመሳሳብና እልክ በመጋባት የሚፈቱ አይደሉም”

የቅዱስ ፓትርያርኩ የግንቦት ፳፻፲፭ ዓ.ም ርክበ ካህናት ጉባኤ መክፈቻ ንግግር



በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።


ኦሪት ዘፍጥረት
ምዕራፍ ፩-፩

በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።


የዮሐንስ ወንጌል
ምዕራፍ ፩-፩

ወንህነሰ ንሰብክ ክርስቶስሃ ዘተሰቅለ፣
እኛስ የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን


፩ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች
ምዕራፍ ፩፥፳፫



    በዩቲውብ ይከታተሉን @EOTCMK



    ይቀላቀሉን